Get Mystery Box with random crypto!

➩የቀኑ ➌ቱ ሐዲሶች ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ክፍል:- 221 1) “ሶላት ላይ—ከኢማም በፊት ቅንጭ | Yasin Muhammed - Official Channel✔

➩የቀኑ ➌ቱ ሐዲሶች
▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬
ክፍል:- 221
1) “ሶላት ላይ—ከኢማም በፊት ቅንጭላቱን ከፍ የሚያደርግ ሰው ራሱን የአህያ ራስ ወይም ቅርጹን ልክ እንደ አህያ ቅርጽ አድርጎ አላህ እንዳያዞረው አይፈራምን?”።
ረሱል(ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም)
ምንጭ:- ቡኻሪ (691)
أَما يَخْشى أحَدُكُمْ- إذا رَفَعَ رَأْسَهُ قَبْلَ الإمامِ، أنْ يَجْعَلَ اللَّهُ رَأْسَهُ رَأْسَ حِمارٍ؟

2) “ከዱኒያ የቀረ ነገር የለም መከራና ፈተና ቢሆን እንጂ”።
ረሱል (ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም)
ምንጭ:- ኢብኑ ማጀህ (3276)
لم يبقَ منَ الدُّنيا إلّا بلاءٌ وفتنةٌ

3) ጅብሪል እንዲህ አለኝ አሉ ረሱል(ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም):- "አንተ ሙሃመድ ሆይ! የፈለከውን ያህል ብትኖር ትሞታለህ። የፈለከውን ብትወድ ትለየዋለህ። የፈለከውን ስራ ዋጋውን ታገኛለህ። እውቅ! የአማኝ ክብሩ የሌሊት ሰላት መስገዱ፤ የበላይነቱም ከሰዎች መብቃቃቱ ነው”።
ምንጭ:- ሲልሲለቱ ሶሒሀህ (831)
قال لِي جبريلُ يا محمدُ عِشْ ما شئتَ فإنك ميِّتٌ، وأحبِبْ ما شئتَ، فإنك مُفارِقُه، واعملْ ما شئتَ فإنك مَجزِيٌّ به، واعلمْ أنَّ شرَفَ المؤمنِ قيامُه بالَّليلِ، وعِزَّه استغناؤه عن الناسِ