Get Mystery Box with random crypto!

ተዋህዶ መሸሸጊያዬ ኦርቶዶክስ መጠለያዬ

የቴሌግራም ቻናል አርማ yaminadabseregela — ተዋህዶ መሸሸጊያዬ ኦርቶዶክስ መጠለያዬ
የቴሌግራም ቻናል አርማ yaminadabseregela — ተዋህዶ መሸሸጊያዬ ኦርቶዶክስ መጠለያዬ
የሰርጥ አድራሻ: @yaminadabseregela
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 846
የሰርጥ መግለጫ

ተዋሕዶ መሸሸጊያዬ
ኦርቶዶክስ መጠለያዬ
ሰላምሽ ከፍ ይበልልኝ
እናቴ ሁሌም ኑሪልኝ🙏
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች 🙌
Join us
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
➫ @yaminadabseregela channel
➬ @dengelmariyam group
➺ @yaminadabseregela_bot for comment

➥ t.me/yaminadabseregela

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-18 14:34:52 አንተ ብቻ ከደብረ ታቦር አትቅር ፣ ካልሞትህ እንደ ኤልያስ ፈጥነህ ና ፣ በበደል ከሞትክም እንደሙሴ ተነሥተህ ና። ብቻ ወደ ደብረ ታቦር ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ለመምጣት ተስፋ አትቁረጥ ፣ እንደ ሙሴ ትሞታለህ እንጂ ምድረ ርስትን አታይም ብትባል ፣ እንደ ኤልያስ ትኖራለህ እንጂ ሞትን አታይም ብትባል ብቻ አንተ ከደብረ ታቦር አትቅር።

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ደብረ ታቦር 2010
ለንደን ፣ ብሪታንያ
639 views11:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 14:34:52 + ከታቦር ተራራ አትቅር +

"አጣቢም በምድር ላይ እንደዚያ ሊያነጣው እስከማይችል በጣም ነጭ ሆነ። "
ማር 9: 3
/ሽራፊ ሃሳቦች ከደብረ ታቦር ንባብ/

የወንጌላውያን ትሕትና ይደንቃል ፣ ማቴዎስ ማርቆስ ሉቃስ ስለ ደብረ ታቦር ሲጽፉ ዮሐንስ አልጻፈም። ዮሐንስ ተመርጦ የተገኘበትን ታሪክ "ተመርጬ" ብሎ አልጻፈም። የቀሩት ወንጌላውያን ደግሞ "እኛ የሌለንበትን ነገር አንጽፍም" አላሉም። አንድ ወንጌል እየሰበኩ የሚፎካከሩ ፣ የአንድ ቤት ጣሪያ እየሠሩ ቆርቆሮ የሚሻሙ የእኛ ዘመን አገልጋዮች አልነበሩምና እነርሱ ያልተመረጡበትን ታሪክ ለመናገር ተሯሯጡ። እኛን የማያካትት ክብር ፣ እኛን የማይጨምር ድግስ ጉዳይ ሲነሣ ለማይጥመን ፣ እኛ የሌለንበትን ፎቶ እንኳን ለማየት የማንፈልግ ፣ በእኛ በኩል ያለፈን ነገር ብቻ የምናራግብ ፣ የሌለንበትን ነገር ጥሩም ቢሆን እንኳን ለምናጣጥል "በእኔ በቀር ባዮች" ትምህርቱ ድንቅ ነው።

ሌላ ማሳያም አለ ማቴዎስ ወንጌላዊው ስለ ራሱ ታሪክ ሲጽፍ "ማቴዎስ የተባለ ቀራጭ በመቅረጫው ተቀምጦ" ብሎ በኃጢአት ከተዘፈቀበት ሥራ ላይ ወደ ክርስትና እንደተጠራ በግልጽ ሲጽፍ ሌሎቹ ወንጌላውያን ግን በሐዋርያት ዝርዝር ላይ ማቴዎስ ያሉትን ሰው ስለ ቀድሞ የቀራጭነት ሥራው ሲጽፉ ግን ሌዊ የሚል ተለዋጭ ስሙን ተጠቅመዋል። ትሑቱ ማቴዎስ ግን በሌሎች ወንጌላውያን የተሸሸገ የቀድሞ የኃጢአት አኗኗሩን ለእግዚአብሔር ይቅር ባይነት ማሳያ እንዲሆን ስለፈለገ ጭራሽ በሐዋርያት የስም ዝርዝር ላይ "ቀራጩ ማቴዎስ" ብሎ ራሱን ጠርቷል።

የሚገርመው ከቀራጭነት ከተጠራ በኋላ በቤቱ ታላቅ ድግስ ደግሶ ጌታችንን ከኃጢአተኞች ጓደኞቹ ጋር የተቀበለ መሆኑን በሌሎች ወንጌላውያን ሲጽፉ ማቴዎስ ግን ቀራጭነቱን አጉልቶ እንዳልጻፈ ሁሉ የግብዣው ነገር ደጋሹ እርሱ መሆኑን አድበስብሶ በመጻፍ አልፎታል።

★ ★ ★

ቅዱስ ጴጥሮስ "ጌታ ሆይ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው" አለ። "ለእኛ" መልካም ነው የሚለው ቃል ድንቅ ነው። በእግዚአብሔር ቤት መኖራችን መልካምነቱና ጥቅሙ ለእኛ ነው እንጂ ለእግዚአብሔር አይደለም። የማንጠቅም ባሪያዎቹ ስሙን በአሕዛብ ዘንድ ከማሰደብ በቀር ለእርሱ ምን እንጠቅመዋለን። ለዚህም ነው ቅዱስ ባስልዮስ "ጌታ ሆይ የአንተ አምላክነት ለእኔ ያስፈልገኛል እንጂ የእኔ ፍጡርነት ለአንተ አያስፈልግህም" ያለው።
ስለዚህ ጴጥሮስ "ለእኛ መልካም ነው" አለ።

"ብትወድስ ሦስት ዳስ እንሥራ" አለ ፣ ጌታ ካልወደደ እንኳን ሦስት አንድ ዳስ መሥራት አይቻልም ፣ እግዚአብሔር ቤትን ካልሠራ ሠራተኞች በከንቱ ይደክማሉ" ስለዚህ "ብትወድስ" አለ።

የዋሁ ጴጥሮስ ለእኔ ልሥራ አላለም ፣ የሐዲስ ኪዳን ሐዋርያ ነኝ ብሎ የብሉይ ኪዳን ነቢያትን ከማክበር ወደ ኋላ አላለም። "አንተ ዓለት ነህ በዚህች ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራታለሁ" በተባለ ማግስት ለነቢያቱ ድንኳን ሊቀልስ የጠየቀ ከጴጥሮስ በቀር ማን አለ?

ከእግዚአብሔር አብ ግን "አትሙት" እስከማለት ለደረሰው ለነጴጥሮስ ንግግር "የምወደው ልጄ ይህ ነው እርሱን ስሙት" የሚል ትእዛዝ መጣ። ሃሳቡ ድንቅ ቢሆንም ቃሉን ሳይሰሙ ዳስ መሥራት መጀመር አይቻልም።

በዚያ ላይ ጌታ የመጣው በደብረ ታቦር ድንኳን አስጥሎ ሊኖር ሳይሆን በቀራንዮ በተሰቀለበት በመስቀሉ ካስማ በደሙ ድንኳን ተክሎ ሊያስጠልለን ነው። ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ "ጴጥሮስ ሆይ ለአንተ የፊቱን ብርሃን እያየህ በዚህ መኖር መልካም ነው ፣ እኛ ግን የምንድነው በተራራው ሲኖር ሳይሆን ወርዶ ፊቱን በጥፊ ሲመታ ነው" ብሎታል።

ጴጥሮስ የዋሁ "በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ" ላለው ለክርስቶስ ድንኳን ሊቀልስ ጠየቀ። በሰማይ "በሰው ሳይሆን በጌታ የተተከለች ድንኳን" ላለችው ሊቀ ካህናት ድንኳን ሊሠራ ለመነ። እዚህ አለ ሲሉት እዚያ ለሚገኘው ፣ በመንፈስ እየተነጠቀ አድራሻውን ለመወሰን ያስቸግር ለነበረው ኤልያስ እንዲቀመጥ ተስፋ አድርጎ ድንኳን ልሥራ አለ። እጅግ የተዋበችና በወርቅ በሐር ያጌጠችን የኦሪት ድንኳን ለሠራው ሙሴ ዓሣ አጥማጁ ጴጥሮስ ድንኳን ልሥራለት አለ። ሐዋርያት ነቢያቱን ሊያስተናግዱ የለመኑባት ደብረ ታቦር ፣ ሐዋርያት ነቢያቱን ለጌታ ቀኝ አዝማች ግራዝማች አድርገው በድንኳን አስቀምጠው እነርሱ እንደ ሎሌ ከደጅ ሊኖሩ የጠየቁ እነ ጴጥሮስ እንደምን ይደንቃሉ? ጴጥሮስ ሆይ አሁን በሰማይ ድንኳኖች ውስጥ እያገለገልህ ይሆንን? ደብረ ታቦርን አይተህ በደስታ "እንኑር" ያልከው ጴጥሮስ ሆይ የገነት ደስታ ስታይ ምን ተሰምቶህ ይሆን?

በእሳት ድንኳን ለመኖር ተስፋ የምናደርግ "በነቢያትና በሐዋርያት መሠረት ላይ ታንጻችኋል" የተባልን እኛስ ምንኛ የታደልን ነን?

★ ★ ★

በታቦር ተራራ ላይ የጌታችን ልብስ እንደ ፀሐይ አበራ ፣ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ "ከፀሐይም በላይ ነው ፣ ፀሐይ አይቶ የወደቀ የለም የጌታችንን ልብስ ሲያዩ ግን የወደቁት ያበራው ከዚያ በላይ ስለሆነ ነው" ይላል።

ከጌታችን በዚያ ተራራ ከሙሴና ኤልያስ ጋር ነበረ። ሙሴ እንደምናውቀው ጽላቱን ተቀብሎ ሲወርድ ሕዝቡ "እባክህን ተሸፈንልን" ብለውት ፊቱን በመጎናጸፊያው ሸፍኖ ነበር። የሙሴ አምላክ ክርስቶስ ግን ደቀ መዛሙርቱ ሲወድቁ አይቶ በልብሱ እንዳይሸፈን ያበራው ፊቱ ብቻ ሳይሆን ልብሱም ነበር።

" አጣቢም በምድር ላይ እንደዚያ ሊያነጣው እስከማይችል በጣም ነጭ ሆነ" ማር 9: 3
የሚለው ቃል ምንኛ የሚደንቅ ነው። በምድር ላይ ያለ አጣቢ ቢፈትግ ቢታገል የዚያን ያህል ሊያነጻው የማይችለው ነጭ እንዴት ያለ ነው? መቼም ሁላችን የምናውቀው ነጭ ነገር ሁሉ በምድር ላይ ባለ አጣቢ የታጠበ ስለሆነ እንዲህ ነው ማለት አንችልም። ብቻ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በምድር ያሉ አጣቢዎች ከሚያነጡት በላይ ልብስን ማንጣት ይችላል።

ይህ ቃል በኃጢአት እድፍ ልብሳችን ላደፈ ሁሉ መጽናኛችን ነው።

መቼም የምድር አጣቢዎች አቅማቸው ውስን ነው።
ቆሽሸን ያዩን ሰዎች ብንታጠብም አያምኑንም ፣ ቢያጥቡልንም በኅሊናቸው የሚያስቀሩብን ቆሻሻ አለ።
በሰው ዓይን አንዴ ቆሽሸህ አትገኝ እንጂ ከተገኘህ መቼም ነጭ አትሆንም። አንተ ግን የደብረ ታቦሩ ብርሃን መድኃኔ ዓለምን ብቻ "እጠበኝ ከበረዶም ይልቅ ነጭ እሆናለሁ" በለው "ኃጢአታችሁ እንደ አለላ ብትሆን እንደ አመዳይ ትነጻለች፤ እንደ ደምም ብትቀላ እንደ ባዘቶ ትጠራለች። " ብሎ በገባው ቃል መሠረት ነጭ ያደርግሃል።

እርሱ ወዳለባት የቅድስት ቤተክርስቲያን ተራራ በንስሓ ከደረስክና በታቦር ያበራውን ብርሃኑን ካበራልህ ነጭ ትሆናለህ። ከዚያ "አጣቢ የማያነጻውን ያህል ትነጻለህ" ከአብ የባሕርይ ልጅ ከብርሃኑ ፀዳል ስትቀርብ አንተም በጥምቀት ያገኘኸው የጸጋ ልጅነትህ ያንጸባርቃል። ነጭ በሆንህ ጊዜ የሚያዩህ ሁሉ "በበጉ ደም ልብስህ መታጠቡን"ና ነጭ መሆኑን አይተው ይደነግጣሉ ፣ ሊሰሙህ ያልወደዱ ሁሉ ለባሕርይ ልጁ "የምወደው ልጄ ይህ ነው እርሱን ስሙት" ብሎ እንዳዘዘለት ለአንተም ጆሮ እንዲሠጡህ ያደርግልሃል።
611 views11:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-13 12:32:23
"ኦ ድንግል አኮ በፍትወተ ደነስ ዘተፀነስኪ አላ በሩካቤ ዘበሕግ እምሐና ወኢያቄም ተወለድኪ!"

"ድንግል ሆይ በኃጢአት ፍትወት የተፀነስሽ አይደለም በሕግ በሆነ ሩካቤ ከሐና ከኢያቄም ተወለድሽ እንጂ!"
ቅዳሴ ማርያም
@dengelmariyam
150 views09:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-25 21:07:07    ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
  ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል
   ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
❖ ሦስት ዓመት ሳይሞላው በሁለት ዓመት ከዘጠኝ ወሩ ታላቅ ሰማዕትነትን የተቀበለው ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ አባቱ ቆዝሞስ (ስምዖን) እናቱ ኢየሉጣ ይባላሉ፤ ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ በሕዳር 15 ቀን የተወለደ ሲሆን ሀገሩ በታችኛው እስያ ልዩ ስሙ ሀንጌቤን ይባላል፡፡
❖ ዘመኑ ዘመነ ሰማዕታት ነበርና መምለኬ ጣዖት የሆነው ንጉሥ እስክንድሮስ ቅድስት ኢየሉጣን ‹‹ለጣዖቴ ስገጂ›› ብሎ አስገደዳት፤ እርሷም ‹‹ሕፃኑ ልጄ መጥቶ ይመስክር›› ብላ ስትናገር ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ ተጠራና ተጠየቀ፤ ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስም ‹‹ለጣዖት አንሰግድም ዘላለማዊ የሆነ የማይሻር አምላክ ስላለ ለእርሱ ነው የምንሰግደው›› ብሎ የአምላኩን ክብር በሕፃን አንደበቱ መሰከረ፡፡
❖ ሕፃኑም ይህንን በመሰከረ ጊዜ ዕድሜው ገና ሁለት ዓመት ከዘጠኝ ወሩ ነበር፤ እንደዚሁ ሁሉ ቅዱስ ቂርቆስም በከሃዲው ንጉሥ ፊት የጌታችንን ክብር በመሰከረ ጊዜ ንጉሡ እጅግ ተቆጥቶ 40 ጋን ውኃ የሚይዝ በርሜል አስጥዶ 40 ቀን ሙሉ እሳት አስነድዶ ቅንጭብ፣ ዘይት፣ ዝፍጥና ሌላም በእጅጉ የሚጎዱ ነገሮችን በውስጡ ጨምሮ ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስንና እናቱን ቅድስት ኢየሉጣን ወደዚያ እቶኑ እሳት እንዲከቷቸው አዘዘ፡፡
❖ ንጉሡ እስክንድሮስ ጭፍሮቹን "ሰም፣ ጨው፣ ባሩድ፣ሙጫ፣ እርሳስ፣ ብረትን፣ ቅንጭብ፣ ቁልቋል ጨምሩበት" ብሎ አዘዛቸው፤ ጭፍሮችም ያዘዛቸውን ከፈጸሙ በኀላ መጥተው "ያዘዝከንን ሁሉ ጨምረንበት ነዶ ፈልቷል" አሉት፤ "ድምፁም እንደ ነጎድጓድ ይሰማል፤ ወላፈኑም እንደ ፀሐይ ያንፀባርቃል፤ የፍላቱም ኃይል 14 ክንድ ያህል እየዘለለ ይወጣል፤ በውስጡ የሚጣሉትን ሰዎች እዘዝ" አሉት፤ ያንጊዜም ህፃን ቂርቆስንና እናቱን ኢየሉጣን ይዘው ከእስር ቤት አወጧቸው፡፡
❖ በክርስቶስ ስም ስላመኑ በእስር ቤት አግብተው አስረዋቸው ነበርና ፍላቱ ወደ ላይ በሚዘል በብረት ጋን ውስጥ ለመጨመር ሲወስዷቸው በዚያን ጊዜም እልፍ ከአንድ ሺህ አራት መቶ ሰዎች እንዲወጡና በፈላው የብረት ጋን ውስጥ የቅዱሳንን አሟሟት እንዲያዩ ሹሙ አዘዘ፡፡
❖ ቅድስት ኢየሉጣም የፍላቱን ግርማ ባየች ጊዜ ተሸበረች፤ ተጠብቆላት ያለውንም ዋጋ ትታ ልትክድ ፈለገች፤ ቅዱስ ቂርቆስም ይህን ባወቀ ጊዜ "እናቴ ሆይ ከብረት ጋን ግርማ የተነሳ አትፍሪ፤ ድንጋፄም አይደርብሽ" እያለ ከብሉይና ከሐዲስ እየጠቀሰ እንድትጸና አስተማራት፤ "ነገር ግን እናቴ ሆይ አናንያንና አዘርያን፣ ሚሳኤልንም እግዚአብሔር ከዕቶን እሳት እንዳወጣቸው እወቂ፤ እኛንም ከዚህ ከብረት ጋን ውስጥ ሊያድነን ይችላል፡፡
❖ እናት ሆይ ከሚያልፈው ከዚህ ዓለም ጭንቅ ልታመልጭ በሚያልፈው በዘለዓለም እሳት ልትቀጭ ትሻለች፤ እናት ሆይ ይህን አትሺ፤ ይቅርብሽ አሁን እግዚአብሔር በመካከላችን አለና ይረዳናል፤ ሶስናን ከኃጢአተኞች እጅ ያዳናት እኛንም ከብረት ጋን ያድነናል፤ ዳንኤልን ከአንበሶች አፍ ያዳነ እርሱ ያድነናል፤ እግዚአብሔር በዚህ ብረት ጋን ውስጥ ግዳጃችን ልንፈፅም ፈቅዶም እንደሆነ የኢዮብን ነፃነት (ትእግስት) ልናገኝ ይገባናል፡፡
❖ እርሱ ልጆቹንና ሚስቱን ያገኘው ገንዘብ ሁሉ አጥቶ በመጨረሻው ሰውነቱን አጥቶ ነበርና ምንም ምንም የቀረበለት አልነበረምና እግዚአብሔርን አመሰግነዋለሁ ከማለት በቀር ያለው ነገር የለም እግዚአብሔር ሰጠ፤ እግዚአብሔርም ወሰደ አለ፤ የእግዚአብሔር ስሙ ለዘለዓለም ይመስገን አለ፤ እኛም ይህንን መከራ ልንታገስና የተጠበቀልንን ልንከተል ይገባናል..." እያለ አብዝቶ መከራት፤ ነገር ግን በዚህም ምክር እናቱን መመለስና ለሰማዕትነት ማዘጋቸት አልቻለም፡፡
❖ ከዚህ በኋላ ቂርቆስ ዓይኖቹን ወደሰማይ አቅንቶ መጸለይ ጀመረ፤ "እግዚአብሔር ሆይ ይህች ባርያህ ከምትክድ ከህይወት መፅሐፍ እኔን ፋቀኝ አለ፤ አቤቱ ይህነን ነገር ልታደርግ አይገባህም፤ አቤቱ እርሻውን ልታቃጥል ፍሬውንም ልትባርክ ትወዳለህን፤ አቤቱ እንጨቱን ቁረጡና አንድዱት ቅጠሉን ጠብቁ ብለህ ልታዝ አይገባህም፡፡
❖ እንጨቱንም ቅጠሉንም ጠብቁ ብለህ እዘዝ እንጂ ይህ አይገባህም ያመነብህ ሁሉ ይህን ያይ ዘንድ፤ ማዳን የሚችል አምላክ ኑሮአቸው ቢሆን ከዚህ ከእሳት ባልሸሹም ነበር ብሎ እንዳይጠራጠር፤ ዲያብሎስ ከባለስልጣኑ ይልቅ እኔ በረታሁ ቅዱሳኑም ድል ነሳኋቸው ብሎ እንዳይመካ፣ ከመንጋውም አንድ በግ ቀማሁ እንዳይል አቤቱ የኃይል መንፈስ ለእናቴ ስጣት አበርታት..." ብሎ ጸለየ፡፡
❖ በዚያን ጊዜ ዲያብሎስ ከእርሷ ሸሽቶ ሄደ፤ ከዚህ በኋላ ቅድስት እናቱ እንዲህ አለች በመንግስተ ሰማያት አባት የሆንከኝ ልጄ ሆይ ጌታህ ኃይል ስጠኝ፤ የሚጠብቀንን ገድላችንን እንፈፅምና ድል እንነሣ" አለችው፡፡
❖ የብረት ጋኑን ሲነድ ሳየው በምንጭ ላይ በዝቶ እንደሚወርድ ጠል ሁኖ አየዋለሁና፤ ቅዱሳንም ይህንን ሲነጋገሩ አንስተው ከብረት ጋኑ ውስጥ ጨመሯቸው፤ በውስጡም አንገትን የሚቆለምም ልብን የሚያጣምም ሆድን የሚሰነጥቅ ሥርንም የሚበጥስ መሣሪያ ነበረበት፤ ወዲያውም የራማው ልዑል ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ገብርኤል እንደ ዐይን ጥቅሻ ፈጥኖ ከሰማይ ወረደና የብረት ጋኑን እሳት ፈጽሞ አበረደው፤ ከቅዱሳንም አንዱን እንኳን ሳይነካው የብረት ጋን ማቃጠሉና መፍላቱ ፀጥ አለ፤ እንደ ውኃም ሆነ።
የራማው ልዑል የሊቀ መላእክት የቅዱስ ገብርኤል ጥበቃው አይለየን፤ ከበዓሉ በረከት ረድኤት ይክፈለን
297 views18:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-25 21:07:05 Send New Post to Subscribers
193 views18:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 19:28:56 ሥላሴ (ሥላሴነት)

ሶስትነት ማለት ነው። ሦስት ሲባል በቁጥር እንደምናውቀው እንደ አብርሃም፣ ይስሐቅ፣ ያዕቆብ ሦስት ማለት አይደለም። ለዚኽም ነው ሥላሴነት ቁጥር ሳይሆን መገናዘብ ነው የሚባለው ።
ቅድስት ሥላሴ ስንል ልዩ ሦስት ማለት ሲሆን ይህንን ልዩ ሦስትነት ለመገንዘብ ከምናውቀው ሦስት የሆነ ነገር ሁሉ መልቀቅ ይኖርብናል። አንድነቱንም ለማወቅ ከምናውቀው አንድ የሆነ ነገር ሁሉ መላቀቅ ይኖርብናል። የሥላሴ ልዩነት ከምናውቀው ሦስት ከምናውቀው አንድ የሆነ ነገር ሁሉ ይለያልና "ልዩ ሦስት" ይባላል። የምናውቀው አንድ የሆነ ነገር ሁሉ መጠቅለል አለበት። የምናውቀው አንድነት ሁሉ ልዩነት አለበት። በመሆኑም ሥላሴ (ሦስትነት) ቁጥር አይደለም የምንለው ለዚህ ነው። የቁጥርን እሳቤ ካልተዉ ምሥጢሩ ሊታየን አይችልም። ለሦስሴ የሚሰጡ ምሳሌዎች ሁሉ ለሰው ለማስረዳት እንጅ ገላጭ አይደሉም። 

#ለሥላሴ መሠረት አብ ነው። መሠረት ማለት መገኛ ማለት ነው። ፈጠረ ማለት አይደለም። ሕልውና ነዋሪነት አኗኗር ማለት ነው (existence)። የወልድና የመንፈስ ቅዱስ መሠረት (Source) መገኛ አብ ብቻ ነው። 

#ለሥላሴ የአካል ስም አብ፣ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሲሆን ወላዲ፣ ተወላዲ፣ ሠራጺ ሲባል የአካል ግብር ስም ነው ። የአንዱ ግብር በሌላው አልያ ወደ ሌላው ግብር አይለወጥም። በዚኽ ግብር ይገናዘባሉ። 

አካል በሕልውና የሚገናዘቡበት የባሕርይ ከዊን ስም ልብ፣ ቃል፣ እስትንፋስ መባል ነው። ይኽም መከፈል መለየት የሌለባት በአንዲት ባሕርይ ያለ የከዊን ሥም ነው። ይኽም ልዩነት ኖሮበት አንድነት፣ አንድነት ኖሮበት ልዩነት ያለበት ነው። ልዩነቱ በከዊን (ሑኔታ) አንድነቱ በሕልውና  መገንዘብ ነው። 


አንዲት የምትሆን ባሕርየ መለኮት ሦስት ከዊን ስላለባት የልብነት ከዊን አብ ነው። አብ በልብነቱ ቃል የተባለ ወልድን እስትንፋስ የተባለ መንፈስ ቅዱስን አስገኝቶ ለራሱና ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ዕውቀት ይሆናል። የቃልነት ከዊን ወልድ ነው። ወልድ በቃልነቱ ከዊን ልብ ከተባለ ከአብ ተወልዶ ለራሱና ለአብ ለመንፈስ ቅዱስ ንባብ ይሆናል። 

የእስትንፋስነቷ ከዊንም መንፈስ ቅዱስ ነው። መንፈስ ቅዱስ በእስትንፋስነቱ ከዊን ልብ ከተባለ ከአብ ሠርጾ (ወጥቶ) ለራሱና ለወልድ ሕይወት መሆን ነው። 


#ሥላሴ በሕልውና አንድ ናቸው ሲባል ቃልና እስትንፋስ ከልብ ቢገኝ ከልብ ሳይለዩ ሕልዋን ሆነው ሲኖሩ ወልድና መንፈስ ቅዱስ በቃልነትና በእስትንፋስነት ከዊን ከአብ (ልብ) ተገኝተው ተከፍሎ ሳይኖርባቸው በአብ ሕልዋን ናቸው።ስንል ነው።

እንኳን አደረሳችሁ
278 views16:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-03 10:48:32 መልካም እለት ሰንበት ይሁንላችሁ ከሰንበት
ረድኤት በረከት ያሳትፈን""
✥✥✥✥
≅ ✥✥#ሰንበት_✥✥ ≅
"""""""""""""""""''"''''"""""""""""""""""""""""""
‹‹ስድስት ቀን ስራ፣ተግባርህም ሁሉ አድርግ በሰባተኛው ቀን ግን ለእግዚአብሔር ለአምላክህ ሰንበት ነው፡፡እግዚአብሔርም በሰባተኛው ቀን አርፏልና ስለዚህ እግዚአብሔር የሰንበትን ቀን ባርኮታል ቀድሶታል፡፡ ›› (ዘጸ20፡10-11)

ሰንበት ማለት ምን ማለት ነው ?
ሰንበትማለትአቆመ፣አረፈማለትነው፡፡ይህቀን የጌታ ዕረፍት የተባረከም ቀን ነው፡፡ከማንኛውም ሥጋዊ ሥራ ተቆጥበን የእግዚአብሔርን ውለታ የምናስብበት ቀን ነው፡፡ ሰው እረፍት ያስፈልገዋል፡፡ የሰንበት ቀንም የተፈጠረው ለዚህ ነው፡፡ (ዘዳ5፡14)፣(ማር2፡38)
ከሳምንቱሰባትቀናትመካከል ለእረፍት የተቀደሰው የተባረከው ዕለት ሰንበት ብቻ ነው፡፡ ስለሌሎች ቀናት የተነገረው ‹‹ ያ መልካም እንደሆነ አየ››የተባለው ብቻ ነው፡፡ ሰንበትን ግን ባርኮታል ቀድሶታል፡፡ (ዘፍ1፡12፣18፡20፣25፡31)
በሐዲስኪዳንለክርስቲያን ሁለት ሰንበት አለ ቀዳሚት ሰንበት (ቅዳሜ)እናሰንበተክርስቲያን (እሑድ)

≅ 1.ቀዳሚትሰንበት(ቅዳሜ)
~~~~~~~~~~~
ጌታያረፈባትለእስራኤል ዘሥጋ የታዘዘው ሰንበት ነው፡፡ ይህ ቀን እስራኤላውያንን እግዚአብሔር አምላክ ከግብፅ ባርነት ወደ እረፍት እንዳወጣቸው ያመለክታል፡፡ዘዳ5-2-16 በእግዚአብሔር እና በህዝቡ መካከል ምልክት ነበረ ሰንበትን አለማክበር ግን ከባድ ቅጣት ያስከትል ነበር፡፡ (ዘጸ3፡17)፣(ሕዝ20፡12)፣(ዘኁ15፡32-36)
ፈሪሳውያንበነበራቸውየተሳሳተ አመለካከት በሰንበት ቀን እንኳን መልካም ሥራን አይሰሩም ነበር፡፡ስለዚህም በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ተወቅሰዋል፡፡ (ማቴ12፡14)፣(ሉቃ4፡16)
በዘመነሐዲስየክርስቲያኖች የቀዳሚት ሰንበት አከባበር እንደ አይሁድ ለሰው የሚከብድ እንዳይሆን በፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 19 ላይ ተገልጿል፡፡

≅ 2.ሰንበተክርስቲያን(እሑድ)
~~~~~~~~~~~
እሑድማለት‹‹አሐደ›› ከሚለው የግእዝ ቃል የወጣ ሲሆን ትርጉሙም የመጀመሪያ ማለት ነው፡፡ ይህቺ ዕለት በመጽሐፍ ቅዱስ ‹‹ከሳምንቱ በፊተኛው ቀን›› በመባል ትታወቃለች፡፡ ዮሐንስም በራዕዩ ‹‹የጌታ ቀን›› ያላት ናት (ራእይ1፤10)፡፡ቅዱስያሬድምበድጓውላይ ‹‹ዕለተ እግዚአብሔር›› የሚላት ዕለተ እሑድ ናት፡፡

ዕለተ እሑድ እንደ ሰንበት የሚከበርበት ምክንያቶች፡-

- እግዚአብሔር ሥራውን የጀመረባት ለሥነፍጥረት መጀመሪያ ዕለተ (ጥንተዕለት)ናትና
- ዕለተ ሥጋዌ ናት፡፡ ጌታ የተፀነሰባትና እርቅ የተወጠነባት የፍሰሐ ቀን፡፡
- ዕለተ ትንሣኤ ናት፡፡ ጌታ ከሙታን ተለይቶ የተነሳባት ዕለት
- የቤተ/ክ የልደት ቅን ናት፡፡መንፈስ ቅዱስ ለሐዋሪያት የወረደባት ኃይልና ፅናትን ያኙባት ዕለት
-ጌታ በክበበ ትስብእት በግርማ መለኮት ዳግም በቅዱሳን መላእክቱ ታጅቦ በጌትነቱ ለፍርድ የሚመጣባት ታላቅ የፍርድ ቀን ናትና
የተለያዩ መንፈሳዊ አገልግሎቶች የሚካሄዱባት ዕለት ናት (1ኛቆሮ16፤1)
-የሐዋሪያትዘመንምበጤሮዓዳ ያሉ ክርስቲያኖች እሑድ ቀን ይሰበሰቡ ነበር (የሐዋ.20፤7)

በቤተክርስቲያንታሪክንጉሥ ቆስጠንጢኖስ ዕለተ እሑድ የክርስቲያኖች ሰንበት ናት በማለት ሥራ እንዳይሰራባት አዋጅ አስነግሮ ነበር፡፡ ምንም እንኳን ይህቺ ዕለት በሐዲስ ኪዳን መከበር የጀመረ ቢሆንም በብሉይ ኪዳን ከፋሲካ በፊት የሰንበት (የቀዳሚት)ማግስትበመባል በኩራት እና ቀዳሚያት የሚያቀርቡበት ቀን ነበር፡፡ (ራዕ1፡10)
በቀዳሚትሰንበትቅዱስ እግዚአብሔር ከሥራው ሁሉ አርፎ ሥጋዊ እረፍትን ለሰው እንዳስተማረ በእሑድ ቀን (በሰንበተክርስቲያን)በጌታችንመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት የተገኘውን የዘላለማዊ የነፍስ ዕረፍት የምናስብበት ነው፡፡ (ዕብ4፡1-10)
ከሰንበትረድኤትበረከት ይክፈለን!አሜንወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን ይቆየን አሜን!!!
186 views07:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-26 15:18:35 Send New Post to Subscribers
149 views12:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-26 15:18:33
134 views12:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-26 15:18:30
129 views12:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ