Get Mystery Box with random crypto!

ሚሽነሪውና መጅሊሱ ... የሚሽነሪውን እንቅስቃሴና የኛን ሚና በተመለከተ አንድ የዘነጋሁት ነገር ስ | የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

ሚሽነሪውና መጅሊሱ
...
የሚሽነሪውን እንቅስቃሴና የኛን ሚና በተመለከተ አንድ የዘነጋሁት ነገር ስላለ እሱን ለመጨመር ልሞክር። በሚሽነሪ እንቅስቃሴ ዙሪያ በግለሰብ ደረጃ አልያም በቡድን ደረጃ ለሚሰሩ የኩፋሩ መንደር ስራዎች የንጽጽር ወንድሞች በግልም በቡድንም እስከማቀው የቻሉትን ስራ እየሰሩ ነው። በተቋም ደረጃ ሚሽነሪው ለሚሰራው ስራ ግን በምካቴ ስራው በኩል ትልቅ ኃላፊነት ያለበት አካል መጅሊሱ ነው። ይህ ግልጽ መሆን አለበት። በተቋም ደረጃ ለሚሰሯቸው ስራዎች በግለሰብና በቡድን ደረጃ የሚሰጥ ግብረ መልስ ያልተመጣጠነ ብቻ ሳይሆን ከሚሰራው ስራ አንጻር እዚህ ግባ የሚባልም አይደለም። እውነት ለመናገር በዚህ በኩል መጅሊሱ ምን እየሰራ እንዳለ መረጃው የለኝም።
...
በገጠሩ አካባቢ ለሚሰሩ የዳዕዋ ስራዎች ዳዒዎችን የማዘጋጀት፣ የማሰልጠንና አቅጣጫ የመስጠት ስራ የሚመለከተው በዋናነት የህዝበ ሙስሊሙን ተቋም ነው። በዚህ በኩል እስከማቀው ድረስ የትኛውም ንጽጽር ላይ የሚሰራ ዱዓት በመጅሊሰ በኩል እገዛ ተጠይቆም "ምን መሰራት ይኖርበታል?" በሚል ተጠይቆም አያውቅም። ስልጠና የሚሰጠውም ሆነ ስራዎችን የሚሰራው በግል አልያም በቡድን በሚደረጉ መሰባሰቦች ጥረት ብቻ ነው። ከዚህ በኃላ በሚኖሩ እንቅስቃሴዎች መጅሊሱ ይህንን ክፍተት የሚደፍን እንቅስቃሴ እንደሚያደርግ ተስፋ አደርጋለሁ።