Get Mystery Box with random crypto!

ምንድን ነው የሚሻለው? መልሱ ቀላል ነው። በየአካባቢው ያለው ሙስሊም ራሱን ማደራጀት፣ ልጆቹን ዲን | የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

ምንድን ነው የሚሻለው? መልሱ ቀላል ነው። በየአካባቢው ያለው ሙስሊም ራሱን ማደራጀት፣ ልጆቹን ዲን ማስተማር፣ ማንቃትና በዙሪያው በኩፍር ውስጥ ያለውን ህዝብ ስለማስለም መወያየት ነው። አሁን ላይ "ሊያከፍሩን ነው" በሚል ስለመከላከል የሚታሰብበት ሰአት አይደለም። "ሀላባን እናከፍራለን" ሲሉ መልሳችንና እቅዳችን መሆን ያለበት "ለከንባታና ሀድያ ዳዕዋን እንዴት በቅጡ እናድርስላቸው?" የሚል ነው። እነሱ "ትልቅ ስራ እየሰሩ ነው" ለሚለው አዎ እየሰሩ ነው። ታዲያ የኛ ግብረ መልስ ምንድን ነው? የነሱን ስራ እየታዘብን መተከዝ? በፍጹም..! "ሀቅ አለን" "በልፋታችን ጀነትን እንመነዳለን" ብሎ የሚያምን ሙስሊም ጥረቱ ከኩፋሩ ሊበልጥ እንጅ ፈጽሞ ሊያንስ አይገባም። ሁላችንም በየፊናችን አካባቢያችን ላይ እንስራ፤ ኢንሻአላህ በኒያችንና በልፋታችን ልክ ደግሞ አሏህ ይረዳናል።