Get Mystery Box with random crypto!

ቀን 30/12/2014 ዓ.ም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች | Addis Ababa Education Bureau

ቀን 30/12/2014 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊዎችና ከሁሉም የመንግስት 1ኛ እና አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ዋና ርዕሳነ መምህራን ጋር ውይይት አካሄደ፡፡
በውይይቱ መክፈቻ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳምሶን መለሰ እንዳስታወቁት በአሁኑ ወቅት አሸባሪው ህውሀት መንግስት ያለቅድመ ሁኔታ ያቀረበለትን የሰላም ጥሪ ወደ ጎን በመተው በሀገራችን ላይ ለሶስተኛ ዙር ወረራ መፈጸሙን ጠቁመው የትምህርት አመራሮች መንግስት የሽብር ቡድኑ የፈጸመውን ወረራ ለመቀልበስ እየወሰደ የሚገኘውን ሉአላዊነት የማስከበር ዘመቻ ከመደገፍ ባሻገር በትምህርት ቤቶች ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደትን ለማስፈን በሚያደረገው እንቅስቃሴ የሚጠበቅባቸውን ከፍተኛ ኃላፊነት ሊወጡ እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡
የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ አድማሱ ደቻሳ በበኩላቸው አሸባሪው ቡድንና ተላላኪዎቹ ኢትዮጵያን ለማፍረስ የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን ሲያደርጉ መቆየታቸውን ገልጸው የትምህርት ማህበረሰቡ ቀደም ብሎ በሽብር ቡድኑ የተፈጸመውን ወረራ ለመመከት ከግንባር ጀምሮ በተለያዩ የደጀንነት ተግባራት ተሳትፎ ሲያደርግ መቆየቱን በመጥቀስ ትምህርት ቤቶች ለተለያዩ የጸጥታ ስጋቶች ተጋላጭ እንዳይሆኑ የትምህርት አመራሩ በአከባቢው ከሚገኙ የጸጥታ አካላት ጋር ተቀናጅቶ መስራት እንደሚጠበቅበት አስረድተዋል፡፡