Get Mystery Box with random crypto!

ቀን 20/12/2014 ዓ.ም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2014ዓ.ም የትምህር | Addis Ababa Education Bureau

ቀን 20/12/2014 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2014ዓ.ም የትምህርት ዘመን እቅድ አፈጻጸም እና በ2015ዓ.ም ዕቅድ ዙሪያ በየደረጃው ከሚገኙ የትምህርት አመራሮች ጋር ላለፉት ሶስት ቀናት ሲያካሂድ የቆየውን ውይይት አጠናቀቀ።

በማጠቃለያ መርሀ ግብሩ የውይይቱ ተሳታፊዎች ያነሱዋቸው ሀሳቦች ለመድረክ ቀርበው ምላሽ የተሰጠ ሲሆን በዋናነትም አዲሱ ስርአተ ትምህርት በአግባቡ ተግባራዊ እንዲሆን የቅድመ ዝግጅት ስራው ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ፣ለተማሪዎች የሚሰራጩ ዩኒፎርምን ጨምሮ ሌሎች የመማሪያ ቁሳቁሶች በፍጥነት ተደራሽ ቢሆኑ፣በትምህርት ቤቶች አከባቢ የሚገኙ አዋኪ ጉዳዮች በተማሪዎች ስነ ምግባር ላይ ተጽእኖ እያሳደሩ ስለሆነ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ ችግሩን መቅረፍ ቢቻል፣በማስፋፊያ አከባቢዎች ያሉ የመማሪያ ክፍል እጥረቶችን መፍታት ቢቻል፣ የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል መስራት እንደሚገባ እንዲሁም የትምህርት አመራሩን ሙያዊ ብቃት ማሻሻል የሚያስችሉ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠናዎች ቢሰጡ የሚሉ ሀሳቦች ተነስተው በቢሮው ኃላፊና ምክትል ቢሮ ኃላፊዎች ምላሽ ተሰቷል።

በውይይቱ ማጠቃለያ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ባስተላለፉት መልዕክት ውይይቱ የመማር ማስተማር ሂደቱን ውጤታማ ማድረግ የሚያስችሉ ሀሳቦች የተነሱበትና የታለመለትን አላማ ያሳከ እንደነበረ ገልጸው ቢሮው በውይይቱ የተነሱ ሀሳቦችን መሰረት በማድረግ የሚመለከታቸውን ባለድርሻ አካላት አስተባብሮ እንደሚሰራ አስታውቀዋል ።