Get Mystery Box with random crypto!

በ2017 የትምህርት ዘመን በተማሪዎች የደንብ ልብስ ዝግጅት ጥራት ማረጋገጫ ዝርዝርን/Specific | Addis Ababa Education Bureau

በ2017 የትምህርት ዘመን በተማሪዎች የደንብ ልብስ ዝግጅት ጥራት ማረጋገጫ ዝርዝርን/Specification/ አስመልክቶ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተካሄደ።

(ቀን ጥር 9/2016 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ2017 የትምህርት ዘመን በተማሪዎች የደንብ ልብስ ዝግጅት የጥራት ደረጃ ማረጋገጫ ዝርዝር ላይ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሄዳል፡፡

በውይይቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ፣ የቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ ወንድሙ ኡመር ፣ የአዲስ አበባ ምገባ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሽታዩ መሀመድ ፣ ፋይናንስ ቢሮ ፣ የመንግስት ግዢ ኤጀንሲ ፣ ምገባ ኤጀንሲ፣ ጨርቃጨርቅ ኢንስቲትዩት ፣ ቴክኒክና ሙያ ፣ አምራች ድርጅቶች እንዲሁም ጉዳዩ የሚመለከታቸው ሌሎች አካላት ተሳታፊ ሆነዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ለ2017 የትምህርት ዘመን የሚዘጋጀውን የተማሪዎች የደንብ ልብስ በተሻለ የጥራት ደረጃ ለማዘጋጀት በተዘጋጀው የጥራት ማረጋገጫ ዝርዝር (specification) ላይ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ውይይት ለማድረግ መድረኩ መጠራቱን በመጥቀስ በቀጣይ ውጤታማ ስራ ለመስራት ውይይቱ ፋይዳው የጎላ ነው ብለዋል፡፡