Get Mystery Box with random crypto!

የተማሪዎች ጥያቄና መልስ ውድድር መካሄዱ በስርአተ ትምህርት አተገባበር የሚታዪ ጉድለቶችን በማረም | Addis Ababa Education Bureau

የተማሪዎች ጥያቄና መልስ ውድድር መካሄዱ በስርአተ ትምህርት አተገባበር የሚታዪ ጉድለቶችን በማረም የተማሪዎች ውጤት ለማሻሻል ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ተገለፀ።


(ቀን ታህሳስ 20/2016 ዓ.ም) በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ትምህርት ፅ/ቤት አስተባባሪነት በሁሉም የመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች መካከል ሲካሄድ የቆየው የተማሪዎች ጥያቄና መልስ ውድድር በዛሬው እለት በአየር ጤና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የማጠቃለያው መርሀ ግብር ተካሂዳል።


በማጠቃለያው መርሀ ግብር ተገኝተው መልእክት ያሰተላለፋት የክፍለ ከተማው ትምህርት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ገነነ ዘውዴ የተማሪዎች ጥያቄና መልስ ውድድር ዋና ዓላማ በአንድ በኩል ተማሪዎቻችን እስከ ዛሬ የነበራቸውን እውቀትና ስነ ምግባር የምንለካበት ሲሆን በሌላ መልኩ ደግሞ በስርአተ ትምህርቱ አተገባበር የሚታዪ ጉድለቶችን በማረም የተማሪዎች ውጤት ለማሻሻል ከፍተኛ መነሳሳት የምንፈጥርበት ነው ብለዋል።


በእለቱም 6ኛ እና 8ኛ ክፍል በአማርኛ እና በአፋን ኦሮሞ፣ 12ኛ ክፍል በማህበራዊ እና በተፈጥሮ ሳይነስ ትምህርት መስኮች ጥያቄዎች ለተወዳዳሪዎች ቀርበው ከ1ኛ እስከ 3ኛ ደረጃ የወጡ አሸናፊ ተማሪዎች፣ ትምህርት ቤቶችና ተቋማት የሰርተፊኬትና የዋንጫ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።



መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728
TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunicatio