Get Mystery Box with random crypto!

በትምህርት አዋኪ ጉዳዮች ዙሪያ ላይ ውይይት ተካሄደ፡፡ (ቀን ታህሳስ 17/2016 ዓ.ም) የል | Addis Ababa Education Bureau

በትምህርት አዋኪ ጉዳዮች ዙሪያ ላይ ውይይት ተካሄደ፡፡


(ቀን ታህሳስ 17/2016 ዓ.ም) የልደታ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽፈት ቤት በአደንዛዥ እፅና በሌሎች የትምህርት አዋኪ ጉዳዮች ዙሪያ ለመንግስትና ለግል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰጠ።


በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የክፍለ ከተማው ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሪት እጅግአየሁ አድማሱ እንደተናገሩት ተማሪዎች የወጣትነት እድሚያቸውን በጎ ነገር በመስራትና ትምህርታቸው ላይ በማተኮር ሊያሳልፉ ይገባል ብለው ሰላማዊ የመማር ማስተማር እንዲሰፍንና የተማሪዎች ውጤትና ስነ-መግባር እንዲሻሻል ሁሉም የየበኩሉን መወጣት አለበት ብለዋል።


የክፍለ ከተማው የሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደረጀ ድሪብሳ በበኩላቸው ተማሪዎች እርስ በእርስ በመደጋገፍ ውጤታማ መሆን እንዳለባቸዉ በማስታወስ የመማር ማስተማሩን ስራ ሊያስተጓጉሉ ከሚችሉ ነገሮች መራቅ እንደሚገባቸው አሳስበዋል፡፡




መረጃዎችን ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728
TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: - aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/