Get Mystery Box with random crypto!

በትምህርት ቤቶች አቅራቢያ ከ200 ሜትር ራዲየስ በታች የቤትንግ ስፖርት ውርርድ በሚያጫውቱ ፣ በማ | Addis Ababa Education Bureau

በትምህርት ቤቶች አቅራቢያ ከ200 ሜትር ራዲየስ በታች የቤትንግ ስፖርት ውርርድ በሚያጫውቱ ፣ በማጫወቻ ቦታዎች ጫት፣ ሺሻ እና አልኮል እንዲሁም ተመሳሳይ ነገሮችን በሚያስጠቅሙ አካላት ላይ እርምጃ መውሰድ ተጀመረ።


(አዲስ አበባ ታህሳስ 8/2016 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የህግ አግባብን ተከትለው በማይሰሩ የቤቲንግ እስፖርት አጫዋች ድርጅቶች ላይ የከተማ አስተዳደሩ ስለ ወሰደው ህግን የማስከበር እርምጃ በሚመለከት በዛሬው እለት ለሚዲያ አካላት ዝርዝር ማብራሪያ ሰጥተዋል።


ወ/ሮ ሊዲያ በመግለጫቸው በትምህርት ቤቶች አቅራቢያ ከ200 ሜትር ራዲየስ በታች የቤትንግ እስፖርት ውርርድ ማጫወት፣ በማጫወቻ ቦታዎች ጫት፣ ሺሻ እና አልኮል እንዲሁም ተመሳሳይ ነገሮችን ማስጠቀም፤ ካለህጋዊ ፈቃድ እስፖርታዊ ውርርዱን ማካሄድ ፤ በስፍራው የሚደረጉ የእርስ በርስ ግጭቶች ፤ የቡድን ፀብ፤ ከ21 ዓመት በታች የሆኑ ተማሪዎችና ታዳጊዎችን ማወራረድን ጨምሮ የቤቲንግ ቤቶቹ የተላለፏቸው ህጎች መሆናቸውን ጠቁመው ይህም ከህብረተሰቡ ከደረሰ ጥቆማ በተጨማሪ ቢሮው ከፀጥታ አካላት ጋር በመሆን በቂ ጥናት አድርጓል ህዝቡንም አወያይቷል ብለዋል።


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ የቤቲንግ እስፖርት ውርርድ የሚካሄድባቸው ስፍራዎች ልዩ ልዩ ወንጀሎች የሚፈጸሙባቸው ዋነኛ ማዕከላት እየሆኑ መምጣታቸውን ጨምሮ በህብረተሰቡ ላይ እየፈጠሩ ያሉትን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች በዝርዝር ከሚመለከታቸው የፀጥታ ተቋማት ጋር በጥናት በመለየት የተቀናጀ እርምጃ መውሰድ መጀመሩን ወ/ሮ ሊዲያ በመግለጫቸው ወቅት አስታውቀዋል።