Get Mystery Box with random crypto!

#በመላው_ዓለም_የምትገኙ_ውድ_አድማጮቻችን ... በውሃልክ ሚዲያ እና ኮሚዩኒኬሽን እየተዘጋጀ በ | Wuhalek Ethiopian Construction Talk Show. 0941431700

#በመላው_ዓለም_የምትገኙ_ውድ_አድማጮቻችን ...

በውሃልክ ሚዲያ እና ኮሚዩኒኬሽን እየተዘጋጀ በኢትዮጵያውያን ቤተ-ሬዲዮ ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የዓየር ሞገድ ላይ በዛሬው ዕለት ቅዳሜ ነሐሴ 21/2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 2 እስከ 3 ሰዓት በቀጥታ ስርጭት በተመደመጠው ውሃልክ የኮንስትራክሽን ፕሮግራማችሁ....

የውሃልክ የኮንስትራክሽን ሬዲዮ ፕሮግራም መሥራች እና ዋና አዘጋጅ ብሎም በምህንድስና የሞያ ዘርፍ በካበተ እውቀት፣ ተግባር ተኮር በሆነ የመስክ ልምድ እና ተሞክርዎ ከሃያ አራት [24] ዓመታት በላይ በማገልገል ላይ ከሚገኘው አቶ አሠለፈ ቦጋለ ሙሉ ጋር በ"ግንባታ ፈቃድ አሠጣጥ እና ተያያዥ ችግሮች" ዙሪያ እንደተለመደው በልክ እና በቁም-ነገር ተጨዋውተናል።

በተለያዩ ግለ ምክንያቶች፤ ይኸው ፕሮግራም ያመለጣችሁ የውሃልክ ቤተኞች፤ የፕሮግራሙን ጥቅል ፍሬ-ነገር ዳግም ታደምጡልን ዘንድ ስናጋብዛችሁ፤ እንደወትሮው ሁሉ ደስ እያለን ነው።

ውድ_አድማጮች... በልዩነት ከምታደርሱን መካር አስተያየት እና ጥቆማ ባለፍ ሁሌም ቢሆን የማድመጥ ሚናችሁ አይለየን።

#የውሃልክ_ሕንፀት በውሃልክ መሠረት!
#ሕይወትን_በኮንስትራክሽን እንገንባ!
ውሃልክ ሚዲያ እና ኮሚዩኒኬሽን።