Get Mystery Box with random crypto!

ያንተ ሲሳይ..!         በአንድ ካንፓኒ ውስጥ ተቀጥሮ  በሚያገኘው ገቢ እናቱን ሚስቱን እና | ውብ ታሪኮች ®

ያንተ ሲሳይ..!

        በአንድ ካንፓኒ ውስጥ ተቀጥሮ  በሚያገኘው ገቢ እናቱን ሚስቱን እና ልጆቹን ያስተዳድራል ዘውትር ስራውን በአግባብ እና በእምነት ለአለቃው ይሰራል እናም አንድ ቀን ስራ ሳይገባ ቀረ። የካንፓኒው ባለቤትም፦"በርግጠኝነት ክፍያ አንሶት ነው የቀረው ስለዚህ ነገ ሲመጣ ክፍያ እጨምርለታለሁ።" ብሎ ይወስናል።

በነጋታው ይህ ሰው ስራ ቦታ ከመግባቱ ክፍያውን ከነ ጭማሪው ሰጠው። ሰውየው ግን ስለጭማሪው ምንም አልደነቀውም ለምን ክፍያ እንደተጨመረለትም አለቃውን አልጠየቀም። ዝም ብሎ ስራውን ቀጠለ። ለተወሰኑ ቀናት እንደበፊቱ ስራውን በአግባብ ሰራ'ና አሁንም አንድ ቀን ስራ ሳይገባ ቀረ። አለቃው በጣም ተቆጣ የጨመረለትንም ደሞዝ መልሶ ቀነሰበት።

ስራውን ጨርሶ ክፍያ ሲቀበለው የጨመረለትን እንደቀነሰ አወቀ አሁንም ምንም ሳይል ትቶ ወጣ። በሰራተኛው ሁኔታ የተገረመው አለቃው፦"ባለፈው ክፍያ ስጨምርልህ ምንም አላልክም ዛሬም ስቀንስብህ ምንም አይነት ጥያቄ አላቀረብክም ለምንድነው?" ብሎ ጠየቀው።

እሱም፦"የመጀመሪያ ግዜ ስራ የቀረሁት የዛን ቀን ሚስቴ ወልዳ ነው ያን ቀን ደሞዝ ስትጨምርልኝ ስለጭማሪው ያልጠየቅኩህ የደሞዙ ጭማሪ ያ አዲስ ለተወለደው ህፃን አላህ የመደበለት ሪዝቅ እንደሆነ ስላወቅኩ ነው። ትናንት ስራ የቀረሁት እናቴ ሞታ ነው። አሁን ደሞ ደሞዝ ስትቀንስብኝ ዝም ያልኩት ያ ከዚህ በፊት ትበላው የነበረው የእናቴ ሪዝቅ በሷ መሞት ምክንያት አላህ አቋርጦት እንደሆነ ስላወቅኩ ነው።"ብሎ መለሰለት።

@WubTarikoch