Get Mystery Box with random crypto!

ለፈገግታ..! አንዱ ነው አሉ ሚስቱ አልታዘዝም ብላ አስቸገረችው። ከዛ ገርፎ ሊያስተካክላት አስቦ | ውብ ታሪኮች ®

ለፈገግታ..!

አንዱ ነው አሉ ሚስቱ አልታዘዝም ብላ አስቸገረችው። ከዛ ገርፎ ሊያስተካክላት አስቦ ጩኀቷ ከቤት ውጪ እንዳይሰማ ብሎ የቤቱን በር ቆለፈባት አሉ።

ከዛ ሊመታት እጁን ሲሰነዝርባት እጁን ያዝ አድርጋ አንስታ ጣለችው። ከዛ ከላይ ቁጭ ብላበት ቀጠቀጠችው ሰውዬው " ተጋደልን" እያለ መጮህ ጀመረ። በጣም ስትበረታበት "ገደለችኝ" ብሎ መጮህ ጀመረ።

ከዛ ሰዎች ሊገላግሉ መጡ በሩን እንደምንም ሰብረው ልክ ሲገቡ፣ ሚስትየው ፈጠን ብላ ገልበጥ አድርጋ ባሏን ከላዩዋ ላይ አስቀምጣ ከስሩ ገባች። ከዛ እሱም እሷን መምታት ጀመረ።

የገቡት ሰዎች አረ ገደልካት ብለው ሊዙት ሲሉ "ተውኝ አዲስ ተገልባጭ ነኝ " አለቸው ይባላል ።

Fouad Oumer | @WubTarikoch