Get Mystery Box with random crypto!

ታይሚንግ..! በውሃ የተሞላ ድስት ውስጥ እንቁራሪት አስገብተን ውሃውን ማሞቅ ብንጀምር፤ የውሀው | ውብ ታሪኮች ®

ታይሚንግ..!

በውሃ የተሞላ ድስት ውስጥ እንቁራሪት አስገብተን ውሃውን ማሞቅ ብንጀምር፤ የውሀው ሙቀት በሚጨምርበት ጊዜ እንቁራሪቱ የሰውነት ሙቀቱን ከውሃው ሙቀት ጋር ማስተካከል ይጀምራል። እንቁራሪቱ  የውሃ ሙቀት መጠን እየጨመረ ሲመጣ የሰውነቱን የሙቀት መጠን በውሃው ሙቀት ልክ ማስተካከል ይጀምራል። ውሃው የመፍያ ነጥብ ላይ ሊደርስ ሲል እንቁራሪቱ ከውሃው ሙቀት ጋር ማስተካከል አይቻለውም። በዚህ ጊዜ እንቁራሪቱ ከፈላው ውሃ ለመዝለል ይወስናል። እንቁራሪቱ ለመዝለል ይሞክራል ነገር ግን ይህን ማድረግ አይቻለውም ምክንያቱም እየጨመረ ካለው የውሃ ሙቀት ጋር ለማስተካከል በሚያደርገው ጥረት ሁሉንም ጥንካሬውን አጥቷል። ከተወሰነ ጊዜ በኋላ እንቁራሪቱ ይሞታል።

እንቁራሪቱን ምን ገደለው? አስቡበት!

ብዙዎቻችን የፈላ ውሃን እንደምንል አውቃለሁ። ነገርግን እንቁራሪቱን የገደለው እየሞቀ ካለው ውሃ ውስጥ መቼ መዝለል እንዳለበት መወሰን አለመቻሉ ነው። ሁላችንም ከሰዎችና ከሁኔታዎች ጋር ነገሮችን ማስተካከል ሊኖርብን ይችላል፤ ነገር ግን እስከ መቼ ማስተካከል እንዳለብን እና መቼ መሄድ እንዳለብን እርግጠኛ መሆን አለብን። ሁኔታዎችን መጋፈጥ እና ተገቢውን እርምጃ መውሰድ ያለብን ጊዜዎች አሉ። ሰዎች አካላችንን፣ ስሜታችንን፣ ገንዘባችንን፣ መንፈሳችንን አልያም አእምሯችንን እንዲበዘብዙ ከፈቀድን ማድረጋቸውን ይቀጥላሉ። መቼ መዝለል እንዳለብን እንወስን! ብርታትና ጥንካሬ እያለን እንዝለል!

Fouad Oumer | @WubTarikoch