Get Mystery Box with random crypto!

ባሻ ስለ ቄሱ..! አንዱ በውስጥ መሥመር መጥቶ 'እሁድ እሁድ ፓስተሮችን እየተሳደብክ ትጽፋለህ። | ውብ ታሪኮች ®

ባሻ ስለ ቄሱ..!

አንዱ በውስጥ መሥመር መጥቶ "እሁድ እሁድ ፓስተሮችን እየተሳደብክ ትጽፋለህ። ወንድ ከሆንክ ስለ ኦርቶዶክስ ቄሶች ጻፍ እስቲ!'' አለኝ፡፡ ባሻዬ! እኔ የምጽፈው ስለማውቀው ዕምነት እንጂ ስለማላውቀው አልዘላብድም። የግድ ፃፍ ካልከኝ ደሞ ይኸውልህ።

ባልና ሚስት ሰውየው ማታ ቤት ገብቶ ገና ቁጭ ከማለቱ እስኪተኛ ድረስ ይጨቃጨቃሉ፣ ይጣላሉ፣ አንዳንዴም ይደባደባሉ። ሴትየዋ ከባሏ ጋር ያላት ጥል እየበዛባት ሲመጣ የንስሃ አባቷን አማከረቻቸው።
...
ቄሱ ነገሩን ካዳመጡ በኋላ ፀበል በትልቅ ጠርሙስ አምጥተው ሰጧትና እንዲህ አሏት ''ይህንን ፀበል ባልሽ ቤት ሲገባ ጠጪውና ሳትውጪው አፍሽ ውስጥ ያዥው። ባልሽ እንቅልፍ ሲወስደው አይተሽ ዋጪው። ጠርሙሱ ባዶ እስኪሆን ድረስ በየቀኑ ተጠቀሚው" ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ቤቱ ሰላም ሆነ።

ባሻዬ! ሴቶች ዝም ቢሉ ዓለም ሰላም ትሆናለች። አንተም በውስጥ መስመር እየመጣህ ካልጨቀጨቅከኝ እኔም ሰላም እሆናለሁ።

Tesfaye H.mariam | @WubTarikoch