Get Mystery Box with random crypto!

★ አለም አቀፍ የኢትዮጲያ ሙስሊሞች ድምፅ ★

የቴሌግራም ቻናል አርማ worldwideethiopianmuslimchannel — ★ አለም አቀፍ የኢትዮጲያ ሙስሊሞች ድምፅ ★
የቴሌግራም ቻናል አርማ worldwideethiopianmuslimchannel — ★ አለም አቀፍ የኢትዮጲያ ሙስሊሞች ድምፅ ★
የሰርጥ አድራሻ: @worldwideethiopianmuslimchannel
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 328
የሰርጥ መግለጫ

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
ውድ የዲን ወንድሞችና እህቶች ይህ ቻናል አለም አቀፍ የኢትዮጲያ ሙስሊሞች ጠቃሚ መረጃ እና ዲናዊ እውቀት መለዋወጫ ሜዲያ ነው ‼
ለአስተያየት @Worldmuslimbot
አዳዲስ መረጃ ወቅቱን ጠብቆ ካሉበት ቦታ እንዲደርስዎ ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊንክ join ያድረጉ!!
https://t.me/worldwideethiopianmuslimchannel

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-05 10:28:40 ««ለከንቱ አልተፈጠርንም»»

"«ሰው ወደ ጌታው ተመላሽና በዱኒያ ሐያቱ ውስጥ ያሳለፋቸውን ነገሮች ሁሉ ክፋትም ይሁን ኢሕሳን ከጌታው ፊት ተከማችተው ለፍርድ እንደሚቀርብና ያለ ማንም ጠበቃ ተሟጋች ያስቀደማቸውን ሥራዎች አጋዥ ከሆኑት አካሎቹም ጋር ጭምር ሙግትና አስረጂነት እንደሚያቀርቡበት የእውነት ባረጋገጠ ጊዜ ለእሱ መልካም ሥራዎችን መስራትና ለኸይራት መሽቀዳደም መጥፎ ተግባራትን ደግሞ መተውና መራቅ እጅግ ይገሩለታል።

«ይህ ግን የእውነት የቂን በተገኘ ጊዜ ነው የቂን ከሌለ ግን አሕዋሉ ከዚህ አክስ ተቃራኒው ይሆናል።

«በዚህ ቀን ከሚገጥሙህ ክስተቶች ሁሉ በእርግጥ በዝንጋቴ ውስጥ ነበርክ፡፡ ዛሬማ (በዱኒያ አለም ሳለህ ተጋርደውብህ እውነት ያልመሰሉህ ክስተቶችን ሁሉ በገሃድ ትመለከት ዘንድ) ሺፋንህንም ካንተ ላይ ገለጥንልህ፡፡ ስለዚህ ዛሬ ዓይንህ ስለታም ሁሉን ተመልካች ነው» ይባላል፡፡ (50/ 22)

«የፈጠርናችሁ ለከንቱ እንደሆነና እናንተም ወደኛ የማትመለሱ መኾናችሁን ጠረጠራችሁን» ለከንቱ የፈጠርናችሁ መሰላችሁን? (ለከንቱ አልፈጠርናችሁም ወደኛ ትመለሳላችሁ) (23/115)
136 viewsedited  07:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 22:10:35 የቄለም ወለጋው ጥቃት

" ... ጥቃት አድራሾቹ እጅግ በጣም የታጠቁ እና የተደራጁ ናቸው።

እዛ ያለው ማህበረሰብ ምስኪን ገበሬ ነው የዕለት ጉርሱን ዳፋ ቀና ብሎ የሚያገኝ ነው።

መብራት እንኳን በቅጡ የሌለው አካባቢ ነው። ከቦቀሎ እና ማሽላ እንጀራ በዘለለ የማይበላ ፤ በኑሮው የተጎሳቆለ ማህበረሰብ ነው እንኳን ጥይት እና ገጀራ ሊገባው ! እጅግ ምስኪን ማህበረሰብ ነው ።

ሰው ወዳድ ናቸው ፤ እንግዳም ተቀባይ ናቸው ፤ ያላቸውን አውጥተው የሚያስተናግዱ ናቸው። ፍርድ ከላይ ነው ፤ ፍርድ ከአላህ ነው ለዛ ማህበረሰብ ይሄ አይገባውም ነበር።

በሚያሳዝን ሁኔታን የማህበረሰቡን ሮሮ፣ ጩኸት ማን እንደሚሰማው አናውቅም። ጥቃት አድራሾቹን ማን ሃይ እንደሚላቸውም አናቅም።

ለማን አቤት እንደምንል ግራ የሚገባ ነው። ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑ ነው ባለፈው ከፍ ብሎ ጊምቢ አካባቢ በጣም ብዙ ሰው በተሰመሳሳይ ሁኔታ ተጨፍጭፏል።

ዘር እየተመረጠ ሰው የሚጨፈጨፍበት ጊዜ ላይ ደረስን ፤ ለማን አቤት እንደምንል አናውቅም "
#allah_allah
135 views19:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 18:12:28 ሁሌ ውስጣችንን ቢዚ የሚያደርገን ምንድን ነው?

እውነት በውስጣችን ሌላን የዱኒያ ጉዳይ እንደምናስበው ያክል አላህን እናወሳልን?

የዱኒያ ጉዳይ አሳስቡ እንደሚያስጨንቀን ሁሉ የቀብራችን የነገ አኼራችን ጉዳይ ያስጨንቀናልን?

ኢማሙ ኢብኑልቀይም ረሒመሁሏህ እንድህ ይላሉ

«(ከጌታህ ጋር) በመለያየት የወረደብህን አደጋና (ከጌታህ) የጋረደህን የውረደት ሂጃብ(ግርዶ) ማወቅ ከፈለግክ: ቀልብህ ለማን ባሪያ፣ አካልህ ለማን አገልጋይ እንደሆነ ተመልከት ውስጥህ በምን ጉዳይ ቢዚ እንደሆነ የመተኛ ቦታህን የያዝክ (ለመተኛት በጎንህ ጋደም ባልክ) ጊዜ ቀልብህ የት እንደሚያድር ከእንቅልፍህ ስነቃ ቀልብህ ወደየት እንደሚበር ተመልከት? ያ(እንድህ ውስጥህ ቢዚ የሆነለት ነገር) ነው (በትክክል) አምላክህ።
የቂያማ እለት ሁሉም (በዱኒያ ላይ) ሲያመልክ የነበረውን ይከተል መባልን በሰማህ ጊዜ (ይህ ውስጥህን እንድህ ቢዚ ያደረገው ነገር) የሆነውም ቢሆን ከእርሱ ጋር አብረኽ ትሄዳለህ። [መዳሪጅ ሳሊኪን (3/308)]

ሐቂቃ ይህ በጣም ያስደነግጣል የሁሌ ጭንቀታችን ሀሳባችን የነገ አኼራ ወይንስ እች ርካሿ ዱኒያ? ሁላችንም ቆም ብለን እራሳችንን እንፈትሽ?
_
قال الإمام ابن القيم رحمه الله

إِذَا أَرَدْتَ أَنْ تَعْرِفَ مَا حَلَّ بِكَ مِنْ بَلَاءِ الِانْفِصَالِ، وَذُلِّ الْحِجَابِ، فَانْظُرْ لِمَنِ اسْتَعْبَدَ قَلْبَكَ، وَاسْتَخْدَمَ جَوَارِحَكَ، وَبِمَنْ شَغَلَ سِرَّكَ، وَأَيْنَ يَبِيتُ قَلْبُكَ إِذَا أَخَذْتَ مَضْجَعَكَ؟ وَإِلَى أَيْنَ يَطِيرُ إِذَا اسْتَيْقَظْتَ مِنْ مَنَامِكَ؟ فَذَلِكَ هُوَ مَعْبُودُكَ وَإِلَهُكَ، فَإِذَا سَمِعْتَ النِّدَاءَ يَوْمَ الْقِيَامَةِ: لِيَنْطَلِقَ كُلُّ وَاحِدٍ مَعَ مَنْ كَانَ يَعْبُدُهُ، انْطَلَقْتَ مَعَهُ كَائِنًا مَنْ كَانَ. [مدارج السالكين (٣/ ٣٠٨)]

ኢብኑ ሙሐመድዘይን
​ ┈•⊰✿◇✿⊱•┈
160 views15:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-01 06:45:07 ክፍል ሶስት


በጋብቻ ስም የሚሰሩ የሃራም መንገዶችና ሌሎች የማናስታውላቸው ወደ ሃራም የሚወስዱን መንገዶች።


በጣም ወሳኝ ማስታወሻ ሁሉም እህቶቻችን ማወቅ ያለባቸው እሳት ውስጥ ከመግባታቸው በፊት።
ሃቅን ፈላጊ ለሆናችሁ እህቶቻችን ማስታወሻው ይጠቅማችኋል ብየ ተስፋ አደርጋለሁ። እያወቁ ለሚያጠፉትም አላህ ሰበብ ያድርግላቸው።

የሃራም መንገዱን /መፍትሄውን /እና ምክር


ክፍል ሶስት

የሚገርመው ይሄን መንገድ ኒቃቢስቶች ሳይቀሩ እየተሸወዱበትና መጨረሻው ወደ ሃራም እየወሰዳቸው ነው ሚገኘው።

አንዳንድ ወንዶች አንዲትን ሴት አይተው ቁጥብ መሆኗን በተለያየ መንገድ ያውቃሉ በአላባበሷ ሊሆን ይችላል ወይም መስጅድ ስትመላለስ ሊሆን ይችላል እናም ወንዱ ቁጥብ መሆኗን ሲያውቅ በሃራም ለማግኜት መንገዱን ይጀምራል ከዛም ስልኳን ፈልጎ ወይም ከሷም በሆነ መንገድ ተቀብሎ እሷን የሚያሳምንበት የውሸት ሰበቦችን ይደረድራል። በዲኔ ደካማ ነኝ እንዳንቺ አይነት ጠንካራ እህት ያስፈልገኛል ፣ቤተሰብም የለኝም ፣ ሰዎችም አይወዱኝም እያለ በቃ የተለያየ ምክንያት በማቅረብ እንደማንም አሳዝኖ ከልጅቷጋ በፁሁፍ ማውራት ይጀምራል ከዛም በቃ እንደ እህትና ወንድም እንሁን ሌላ ምንም አልፈልግም ይላታል እሷም እውነት መስሏት እሽ ትለዋለች ከዛም መጀመሪያ ላይ ስለዲን ያወራታል ከዛ እየቆየ ወሬው ሁሉ ይቀየራል እሷም መቅረብ ካለባት በላይ ድምበር አልፋ ትቀርበዋለች አጅ ነብይ መሆኑንም ትረሳዋለች በዛ መሃል ልጅቱ በልጁ ትሳባለች ማለትም በፊት ሲያወራት በነሩት የውሸት የእዝነት ቃላቶች ተፅእኖ ይፈጥርባታል ከዛም ልጁ የሚፈልገውን ሃራም ነገር ካልሰጠችው እንደሚርቃት ይነግራታል ከዛም ልጁን ከማጣው ብላ ወደ ሃራም ግኑኝት ተገባለች። ከዛ መጨረሻው ዚና ይሆንና ህይወቷን አበላሽቶ ይርቃታል።
በተለይ ወንዶች አንዴ ዚና ካደረጉ ወዲያው ነው ከልጅቱ ላይ ያለው ፍቅራቸው የሚወጣባቸው ከዛም ልጅቱን እንደ ወሲብ እቃ በማየት ለስሜቱ ማራገፊያ ነው ሚጠቀማት ልጅቱም የሚወዳት እየመሰላት ህይወቷን መከራ ውስጥ ትከተዋለች መጨረሻውም መለያየት ነው ሚሆነው ምክያቱም አላህን አስከፍተን መቸም ጥሩ ነገር አናገኝም። በዚህ ምንገድ አልፈው ብንጋባ እንኳ ትዳራችን በፈተና የተሞላና የሚያስጠላ ነው ሚሆንው ምክንያትም ቤት ውስጥ በፊት የነበረውን ነገር ነው ሚያደርጉት ከዛም መሰለቻቸት ይመጣል ትዳር ማለት ደግሞ አብሮ መተኛት ብቻ አይደለም።

አያችሁ ሸይጧን ትንሽ ክፍትት ብቻ ነው ሚፈልገው!
ስህተቶችን ቶሎ ማረም ካልቻክን ወደ መጥፎ መዘዝ ነው የሚያስገባን።

ውድ እህቴ ወንድሜ ብለሽ ስለቀረብሽው የስጋ ወንድምሽኮ አይሆንም ወይም አጅ ነብይነቱ ሊጠፋ አይችክም ይሄ ትልቅ የሆነ ስህተት ነው ቁርዓን የሚያቀራሽ ቢሆን እንኳ ልቅ ሁነሽ ልትቀርቢው አይገባም አጅ ነብይሽ ነው እናም አላህን እንፍራ በዚህ ምንገድ በጣም በርካታ ሰዎች አሉ እና ድምበር አንለፍ ሃቁን እያወቅነው ስሜታችንን አንከተል። መጨረሻው ፀፀት ነው።

አንደኛ ልጁ በዲኔ ደካማ ነኝ ካለሽ መስጅድ ሂደህ ቅራ በይውም ከዛ ውጭ ደግሞ ከቻልሽ አንዳንድ የሱና ቻናል ላኪለትና ልጁን ብሎክ አድርጊው ከዛ ውጭ እንደ ቀላል አይተሻቸው አንዳንድ ነገር ምታወሩ ከሆነ አንደኛ ይሄ የሃራም ምንገድ ነው ሁለተኛ ወደ መጥፎ መንገድ እየሄድሽ መሆኑ ልትረሽው አይገባም በሃራም ምንገድ በሃራስ መተማመን ሚባል ነገር የለም።

እና ውድ እህቴ እንደዚህ ልቅ ሁነሽ ቀርበሽው እንዴት ከወንድምና ከእህትነት ውጭ የሆነ ነገር አይፈጠርም ብለሽ ታስቢያለሽ? ይሄ ራስን ማታለል ነው አንዳንዶች ራሳቸውን ለመሸወድ ሲፈልጉ እኔ ከወንድምነት ወይም ከእህትነት ውጭ አልፈልግም ይሉና አቀራረባቸው ግን ልክ እንደ ባልና ሚስት ነው እናም ራሳችሁን አትሸውዱ ግንኙነታችሁ ወደ መጥፎ ነገር ከመቀየሩ በፊት ሁኔታችሁን አስተካክሉ።
በዛ ምንገድ ተቀራርባችሁ ወደ ትዳር መቀየር ፈልጋችሁም ከሆነ ቶሎ ወደ ትዳር ቀይሩት ከዛ ውጭ በዛ ስሜት ላይ ሁናችሁ ከቀጠላችሁ መጨረሻው እራስን እሳት ውስጥ መጣል እንደሆነ ምንም ጥርጥር የለውም አላህን እንፍራ ወደ አላህ እንመለስ

አንዳንዶች ደግሞ እንደ እህት እንቀራረብ ይሉና ልጅቱን ወጥመድ ውስጥ ማስገባት ፈልገው ከግዜ በኋላ ወድጄሻለሁ ፍቅረኛ እንሁን ይላታል እሷም በማውራት ብዛት ልጁን ትወደውና እንዳይለያት በማሰብ አላህን አስከፍታ ግኑኝነታቸው ወደ ሃራም ይቀየራል ይሄ አንዱ የወንዶች ማጥመጃ ዘዴያቸው ነው። እንንቃባቸው

ሌላው እንደዚሁ እንደ እህት እንቀራረብ ብለው ከግዜ በኋላ አፈቅርሻለው ፍቅረኛ እንሁን ይላታል እሷም እንደ ወንድም ስለቀረበችው እኔ ከወንድምነት ውጭ አስቤህ ስለማታውቅ እንደዛ መሆን አንችልም ስትለው እሱም እሽ በቃ ትቸዋለሁ እንደ እህት እንቀጥል ይላታል እሷም እሽ ብላ እንደበፊቱ ትቀጥላለች። ውድ እህቴ እንዴት ብሎ ነው ፍቅር ይዞት ከነበረ ወደ እህትነት ሊቀየር የሚችለው? ይሄ ውሸት ነው እንደ በፊቱ እንቀጥል የሚልሽ አንቺን ወጥመድ ውስጥ ለመጣል ወይም ፍቅር አስይዛለሁ ብሎ ያልሆነ ነገር አደርጋለሁ ብሎ ስለሚያስብ ነው እናም ከዚህ የሸይጧን መንገድ ቶሎ እንራቅ


በዚህ ምንገድ በጣም ብዙ እህቶች ስህተት ይሰራሉ እየተሸወዱም ነው ከነሱ ትምህርት እንውሰድ!
እንደወንድም ተቀራርባችሁም ይሁን ድምበር ያለፋችሁ ካላችሁ ከዚህ ምንገድ ራሳችንን እናውጣ ገና እየገባንበትም ከሆነ ከዚህ ምንገድ እንራቅ። ካልገባንበትም ራሳችንን እንጠብቅ።
ቁጥብ መሆን ለራስ ነው ሚጠቅው።!

(አላህ የላቀና ይበልጥ አዋቂ ነው)


ክ ፍ ል አራት ይ ቀ ጥ ላ ል
170 views03:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-29 13:59:50 ​​╔═══════════════╗
በታሪክ እና በእውነታው መካከል
╚═══════════════╝

ጌታዬ ሆይ!
ብዕሬን እንደ ኻሊድ ኢብኑል ወሊድ ሠይፍ የሰላ አድርግልኝ


ኢስላም ኃያል ሆኖ አህጉራትን በሚያስተዳድርበት ጊዜ ህፃናት በጂሃድ መስክ ላይ ወጥተው እንዳይዘምቱ ሲከለከሉ በእጅጉ አምርረው ያነባሉ። አንድ የቀስት ፍላጻ ኢላማውን ስቶ ሲወድቅ ያለቅሳሉ። ወላጆቻቸው በጂሃድ ምክንያት ልጆቻቸውን ለማሰልጠን ጊዜ ስላልነበራቸው የጦር ልምምድ ባለማድረጋቸው ተንሰቅስቀው ያነባሉ።

የዛሬ ልጆች አባቶቻቸው አሻንጉሊት ወይም ስልክ ስላልገዙላቸው ያነባሉ። ተከታታይ ፊልም እያዩ በስሜታዊ ትዕይንቱ ያለቅሳሉ። የዘፈን ውድድር ሲያሸንፉ ወይም ሲሸነፉ ይንሰቀሰቃሉ። የሚወዱት የእግር ኳስ ቡድን በመሸነፉ ከዓይኖቻቸው የዕንባ ዘለላዎች ይረግፋሉ።

ለአላህ ሲሉ በጂሃድ መስክ ላይ ፀጉራቸው በአቧራ የተሸፈኑ፣ ደማቸው ከአፈር ጋር የተላወሰ ጀግኖችን ከእኛ ትውልድ ጋር ማነፃፀር የነሱን ክብር ዝቅ እንደማድረግ ይቆጠርብኛል ብዬ ሰጋሁ። በመሆኑም ልጆቻቸውን ብቻ ለነፅፅር አቀረብኩ።

በዚያ ኃይልነታችን ጊዜ ሙስሊም ልጆች ቁርአንን አስውበው በመቅራት ይሽቀዳደማሉ። ከልጅ እስከአዋቂው በኢማናቸው ያበቡ በኢስላማዊ አኽላቃቸው ያሸበረቁ ነበሩ። ዓለም ተሰብስቦ በድፍረት ከፊታቸው መቆም ይሳነዋል። ከልዕለ ኃያልነታቸው አያስቆማቸውም። ዛሬ ግን ያ የኃያልነት ዘመናችን ተዘንግቶ የእናቶቻቸውን ጡት በአግባቡ ያልጨረሱ ህፃናት በይነመረብን ማሰስ፣ ጨዋታዎችን በስልክ ማውረድ፣ ዘፈኖችን ማዳመጥ፣ በሙሀረማት ላይ መግበስበስና በወላጆቻቸው ጭብጨባ ታጅበው በመደነስ ላይ ናቸው።

እንዲህ አድጎ ስለ እስልምና ከፍታ የሚታገል ትውልድ ይፈጠራል ብላችሁ ትጠብቃላችሁን?
ልጆች ችላ እስከተባሉ፣ ኢስላማዊ ተርቢያና አኽላቅ እስከተዘነጋ ድረስ ከዚህም የከፋ ነገር ይከሰታል።

ለሌሎችም ሼር በማድረግ ተደራሽነቱን እናስፋ


═════════════════
#ኢኽላስ_ታማኝነት_ትጋት_ስኬት
╚═══════════════╝
Mahi mahisho
138 viewsedited  10:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-29 13:44:18 «ኡድሂያ ለማረድ ካቀዱ ከወዲሁ ጥፍርና ጸጉርዎን ከመቁረጥ ይቆጠቡ!
-------------------
☞ እንድ ሙስሊም ሀጅ የማያደርግ ከሆነና በዒድ አል አድሀ እለት ኡድሂያን ለማረድ ካሰበ የዙልሂጃ ወር ከገባበት የምጀመሪያዉ ቀን ጀምሮ ጥፍሩንና ጸጉሩን አይቆርጥም፤ ቆዳውንም አይቀርፍም። ይህም ተከታዩን የኡሙሰለማ ሀዲስ መሰረት ያደረገ ነው።

ከኡሙ ሰለማ በተላለፈ ሀዲስ የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ብለዋል፤ «የዙልሂጃ ወርን ጨረቃ ካያችሁና ከናንተ መካከል አንዱ ኡድሂያ ለማረድን ካቀደ፤ ፀጉሩንና ጥፍሩን ከመቁረጥ ይቆጠብ» አል ኢማም አህመድ ዘግበውታል። በሌላም ዘገባም «ኡድሂያውን እስኪያርድ ድረስ ከፀጉሩና ከጥፍሩ ምንንም አይቁረጥ» ብለዋል። እንደዚሁ፤ «ከሰውነቱ ቆዳ ወይም ከፀጉሩ ምንንም አይቁረጥ» ብለዋል።

ይህ ማንኛውም ሙስሊም እራሱን በሀጅ ላይ ካሉ ሰዎች ጋር የሚያመሳስልበት እና የተወሰኑ የኢህራም ክልከላዎችን ከነሱ ጋር የሚጋራበት ዲናዊ ስርአትና ነብያዊ ትዕዛዝ ነው።

☞ ጸጉርንና ጥፍርን ከመቁረጥ የሚከለከለው ለራሱ ወይም ለሰው በራሱ ገንዘብ የሚያርድ ሰው ብቻ ነው። ህጉ የሚመለከተው የሚያርደዉን ሰው ብቻ ነው ሲባል፤ በወኪልነት ለሌላ ስው የሚያርድን ሰው አይጨምርም።

☞ እያወቀ ጥፍሩን ወይም ጸጉሩን የቆረጠ ወንጀል ፈጽሟልና ወደ አላህ በተውበት ሊመለስ ይገባዋል፤ ኡድሂያው ግን አይበላሽም ማካካሻ ከፋራም የለበትም። አንዳንዶች እንደሚያስቡት ሳይሆን ወንጀሉን ቢፈፅምም ኡድሂያ ማረዱን መተው የለበትም።

☞ በስህተት ወይም በመርሳት ፀጉሩን ወይም ጥፍሩን የቆረጠ ሰው ምንም ወንጀል የለበትም። በተመሳሳይ መልኩ በጣም አስፈላጊ ሲሆን ቢቆርጥ ችግር የለውም። ለምሳሌ የተጎዳን የሰውነት ቆዳ ለማከም ወይም የተሰበረ ጥፍሩን ለማስተካከል መቁረጥ ይፈቀድለታል።

፠ ስለ ኡድሂያ ጥቂት ተጨማሪ ነጥቦች

1 - በዙልሂጃ አስር ቀናት ከተወደዱ ተግባሮች መካከል ኡድሂያን በማረድ ወደ አላህ መቃረብ አንዱ ነው።

2- ኡድሂያ በጣም ከጠነከሩ የነብዩ صلى الله عليه وسلم ሱናዎች መካከል ነው። ኡድሂያ የነብዩ ኢብራሂምን ሱና ህያው ከማድረግ በተጨማሪ ለድሆች እና ችግረኞች መድረስ ነው።

3- ኡድሂያን በተመለከተ አላህ ከኛ የሚፈልገው ለእርሱ ያለንን ፍራቻ ተቅዋና ታዛዥነት ግልጽ ማድረጋችንን ብቻ ነው። አላህ እንዲህ ብሏል፤

{ﻟَﻦ ﻳَﻨَﺎﻝَ اﻟﻠَّﻪَ ﻟُﺤُﻮﻣُﻬَﺎ ﻭَﻻَ ﺩِﻣَﺎﺅُﻫَﺎ ﻭَﻟَٰﻜِﻦ ﻳَﻨَﺎﻟُﻪُ اﻟﺘَّﻘْﻮَﻯٰ ﻣِﻨﻜُﻢْ ۚ ﻛَﺬَٰﻟِﻚَ ﺳَﺨَّﺮَﻫَﺎ ﻟَﻜُﻢْ ﻟِﺘُﻜَﺒِّﺮُﻭا اﻟﻠَّﻪَ ﻋَﻠَﻰٰ ﻣَﺎ ﻫَﺪَاﻛُﻢْ ۗ ﻭَﺑَﺸِّﺮِ اﻟْﻤُﺤْﺴِﻨِﻴﻦَ} الحج 37

አላህን ሥጋዎቿም ደሞቿም ፈጽሞ አይደርሰውም፡፡ ግን ከእናንተ የሆነው ፍራቻ ይደርሰዋል፡፡ እንደዚሁ አላህን በመራችሁ ላይ ልታከብሩት ለእናንተ ገራት፡፡ በጎ ሠሪዎችንም አብስር፡፡» አል ሐጅ 37

4- ኡድሂያ የሚታረደው ከዒድ ሰላት በኋላ ነው። የአላህ መልዕክተኛ صلى الله عليه وسلم ከኢድ ሰላት በፊት ያረደ ሰው እንዲደግም አዘዋል።

5- ሚዛን በሚደፋው የኡለማዎች አቋም መሰረት የዒድ ሰላት ከተጠናቀቀበት ጊዜ ጀምሮ የሶስተኛው ቀን ጸሀይ እስክትጠልቅ ድረስ ኡድሂያን ማረድ ይቻላል።

6- ወንድም ይሁን ሴት ግመል፣ የቀንድ ከብቶች፣ በግና ፍየል ለኡድሂያ ይታረዱሉ።

7- የአላህ መልዕክተኛ صلى الله عليه وسلم እንከን ያለባቸውን እንስሳት እንዳናርድ ከልክለዋል። አንድ አይኑ የታወረ፣ ስብራት ያለበት፣ የከሳና የደከመ ወይም የታመመ እንስሳ ለኡድሂያ አይሆንም።

8- ኡድሂያን ለብቻ ማረድ እንደሚቻለው ሁሉ ለሰባት ሆኖ አንድን ወይፈን ወይም በሬ መጋራትም ይቻላል።

9- አንድ ሰው ኡድሂያ ሲያርድ ለራሱ እና በህይወት ላሉም ይሁን በህይወት ለሌሉ ቤተሰቦቹ አስቦ ሊያርድ ይችላል።

10- የኡድሂያውን ስጋ፣ ለቤት፣ ለስጦታ እና ለሰደቃ አድርጎ ሶስት ቦታ መከፋፈሉ ሱና ነው። ይህ ማለት ግን እንደ አስፈላጊነቱ ለሶስቱም ያውለዋል ማለት እንጂ ሶስት እኩል ቦታዎች ይከፋፍለዋል ማለት አይደለም።»

: አቡ ጁነይድ ሳላሕ አሕመድ
114 views10:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-28 21:48:16 ﻓﻔﻲ ﺍﻟﺼﺤﻴﺤﻴﻦ ﻋﻦ ﺳﻬﻞ ﺑﻦ ﺳﻌﺪ ﺭﺿﻲ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻨﻪ ﻗﺎﻝ : ﻗﺎﻝ ﺭﺳﻮﻝ ﺍﻟﻠﻪ ﷺ : ﺭﺑﺎﻁ ﻳﻮﻡ ﻓﻲ ﺳﺒﻴﻞ ﺍﻟﻠﻪ ﺧﻴﺮ ﻣﻦ ﺍﻟﺪﻧﻴﺎ ﻭﻣﺎ ﻋﻠﻴﻬﺎ ﻭﻣﻮﺿﻊ ﺳﻮﻁ ﺃﺣﺪﻛﻢ ﻣﻦ ﺍﻟﺠﻨﺔ ﺧﻴﺮ ﻣﻦ ﺍﻟﺪﻧﻴﺎ ﻭﻣﺎ ﻋﻠﻴﻬﺎ ﻭﺍﻟﺮﻭﺣﺔ ﻳﺮﻭﺣﻬﺎ ﺍﻟﻌﺒﺪ ﻓﻲ ﺳﺒﻴﻞ ﺍﻟﻠﻪ ﺃﻭ ﺍﻟﻐﺪﻭﺓ ﺧﻴﺮ ﻣﻦ ﺍﻟﺪﻧﻴﺎ ﻭﻣﺎ ﻋﻠﻴﻬﺎ،

ﻭﻋﻦ ﺃﺑﻲ ﻫﺮﻳﺮﺓ - ﺭﺿﻲ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻨﻪ - ﻗﺎﻝ : ﻗﺎﻝ ﺭﺳﻮﻝ ﺍﻟﻠﻪ ﷺ :- ﻣﺜﻞ ﺍﻟﻤﺠﺎﻫﺪ ﻓﻲ ﺳﺒﻴﻞ ﺍﻟﻠﻪ - ﻭﺍﻟﻠﻪ ﺃﻋﻠﻢ ﺑﻤﻦ ﻳﺠﺎﻫﺪ ﻓﻲ ﺳﺒﻴﻠﻪ - ﻛﻤﺜﻞ ﺍﻟﺼﺎﺋﻢ ﺍﻟﻘﺎﺋﻢ، ﻭﺗﻜﻔﻞ ﺍﻟﻠﻪ ﻟﻠﻤﺠﺎﻫﺪ ﻓﻲ ﺳﺒﻴﻠﻪ ﺇﻥ ﺗﻮﻓﺎﻩ ﺃﻥ ﻳﺪﺧﻠﻪ ﺍﻟﺠﻨﺔ ﺃﻭ ﻳﺮﺟﻌﻪ ﺳﺎﻟﻤﺎ ﻣﻊ ﺃﺟﺮ ﺃﻭ ﻏﻨﻴﻤﺔ ﺃﺧﺮﺟﻪ ﻣﺴﻠﻢ ﻓﻲ ﺻﺤﻴﺤﻪ، ﻭﻓﻲ ﻟﻔﻂ ﻟﻪ ﺗﻀﻤﻦ ﺍﻟﻠﻪ ﻟﻤﻦ ﺧﺮﺝ ﻓﻲ ﺳﺒﻴﻠﻪ ﻻ ﻳﺨﺮﺟﻪ ﺇﻻ ﺟﻬﺎﺩ ﻓﻲ ﺳﺒﻴﻠﻲ ﻭﺇﻳﻤﺎﻥ ﺑﻲ ﻭﺗﺼﺪﻳﻖ ﺑﺮﺳﻠﻲ ﻓﻬﻮ ﻋﻠﻲ ﺿﺎﻣﻦ ﺃﻥ ﺃﺩﺧﻠﻪ ﺍﻟﺠﻨﺔ ﺃﻭﻭ ﺃﺭﺟﻌﻪ ﺇﻟﻰ ﻣﺴﻜﻨﻪ ﺍﻟﺬﻱ ﺧﺮﺝ ﻣﻨﻪ ﻧﺎﺋﻼ ﻣﺎ ﻧﺎﻝ ﻣﻦ ﺃﺟﺮ ﺃﻭ ﻏﻨﻴﻤﺔ
120 views18:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-28 21:24:46 ﺍﻟﺠﻬﺎﺩ ﻓﻲ ﺳﺒﻴﻞ ﺍﻟﻠﻪ

Bhjjjkkljhjhhbbbnnnnbbn

ﺍﻟﺠﻬﺎﺩ ﻓﻲ ﺳﺒﻴﻞ ﺍﻟﻠﻪ ﻣﻦ ﺃﻓﻀﻞ ﺍﻟﻘﺮﺑﺎﺕ، ﻭﻣﻦ ﺃﻋﻈﻢﺍﻟﻄﺎﻋﺎﺕ، ﺑﻞ ﻫﻮ ﺃﻓﻀﻞ ﻣﺎ ﺗﻘﺮﺏ ﺑﻪ ﺍﻟﻤﺘﻘﺮﺑﻮﻥ ﻭﺗﻨﺎﻓﺲ ﻓﻴﻪ ﺍﻟﻤﺘﻨﺎﻓﺴﻮﻥ ﺑﻌﺪ
ﺍﻟﻔﺮﺍﺋﺾ،

ﻭﻣﺎ ﺫﺍﻙ ﺇﻻ ﻟﻤﺎ ﻳﺘﺮﺗﺐ ﻋﻠﻴﻪ ﻣﻦ ﻧﺼﺮ ﺍﻟﻤﺆﻣﻨﻴﻦ ﻭﺇﻋﻼﺀ ﻛﻠﻤﺔ ﺍﻟﺪﻳﻦ، ﻭﻗﻤﻊ ﺍﻟﻜﺎﻓﺮﻳﻦ ﻭﺍﻟﻤﻨﺎﻓﻘﻴﻦ ﻭﺗﺴﻬﻴﻞ ﺍﻧﺘﺸﺎﺭ ﺍﻟﺪﻋﻮﺓ ﺍﻹﺳﻼﻣﻴﺔ ﺑﻴﻦ ﺍﻟﻌﺎﻟﻤﻴﻦ، ﻭﺇﺧﺮﺍﺝ ﺍﻟﻌﺒﺎﺩ ﻣﻦ ﺍﻟﻈﻠﻤﺎﺕ ﺇﻟﻰ ﺍﻟﻨﻮﺭ، ﻭﻧﺸﺮ ﻣﺤﺎﺳﻦ ﺍﻹﺳﻼﻡ ﻭﺃﺣﻜﺎﻣﻪ ﺍﻟﻌﺎﺩﻟﺔ ﺑﻴﻦ ﺍﻟﺨﻠﻖ ﺃﺟﻤﻌﻴﻦ، ﻭﻏﻴﺮ ﺫﻟﻚ ﻣﻦ ﺍﻟﻤﺼﺎﻟﺢ ﺍﻟﻜﺜﻴﺮﺓ ﻭﺍﻟﻌﻮﺍﻗﺐ ﺍﻟﺤﻤﻴﺪﺓ ﻟﻠﻤﺴﻠﻤﻴﻦ،

ﻭﻗﺪ ﻭﺭﺩ ﻓﻲ ﻓﻀﻠﻪ ﻭﻓﻀﻞ ﺍﻟﻤﺠﺎﻫﺪﻳﻦ ﻣﻦ ﺍﻵﻳﺎﺕ ﺍﻟﻘﺮﺁﻧﻴﺔ ﻭﺍﻷﺣﺎﺩﻳﺚ ﺍﻟﻨﺒﻮﻳﺔ ﻣﺎ ﻳﺤﻔﺰ ﺍﻟﻬﻤﻢ ﺍﻟﻌﺎﻟﻴﺔ، ﻭﻳﺤﺮﻙ ﻛﻮﺍﻣﻦ ﺍﻟﻨﻔﻮﺱ ﺇﻟﻰ ﺍﻟﻤﺸﺎﺭﻛﺔ ﻓﻲ ﻫﺬﺍ ﺍﻟﺴﺒﻴﻞ، ﻭﺍﻟﺼﺪﻕ ﻓﻲ ﺟﻬﺎﺩ ﺃﻋﺪﺍﺀ ﺭﺏ ﺍﻟﻌﺎﻟﻤﻴﻦ،

ﻭﻫﻮ ﻓﺮﺽ ﻛﻔﺎﻳﺔ ﻋﻠﻰ ﺍﻟﻤﺴﻠﻤﻴﻦ ﺇﺫﺍ ﻗﺎﻡ ﺑﻪ ﻣﻦ ﻳﻜﻔﻲ ﺳﻘﻂ ﻋﻦ ﺍﻟﺒﺎﻗﻴﻦ،

ﻭﻗﺪ ﻳﻜﻮﻥ ﻓﻲ ﺑﻌﺾ ﺍﻷﺣﻴﺎﻥ ﻣﻦ ﺍﻟﻔﺮﺍﺋﺾ ﺍﻟﻌﻴﻨﻴﺔ ﺍﻟﺘﻲ ﻻ ﻳﺠﻮﺯ ﻟﻠﻤﺴﻠﻢ ﺍﻟﺘﺨﻠﻒ ﻋﻨﻬﺎ ﺇﻻ ﺑﻌﺬﺭ ﺷﺮﻋﻲ، ﻛﻤﺎ ﻟﻮ ﺍﺳﺘﻨﻔﺮﻩ ﺍﻹﻣﺎﻡ ﺃﻭ ﺣﺼﺮ ﺑﻠﺪﻩ ﺍﻟﻌﺪﻭ ﺃﻭ ﻛﺎﻥ ﺣﺎﺿﺮﺍ ﺑﻴﻦ ﺍﻟﺼﻔﻴﻦ.
124 views18:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ