Get Mystery Box with random crypto!

በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ለሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ምህንድስናና ሂሳብ (STEM) ፕሮግራም ሰልጣኝ ለሆኑት | Wolkite University Students' Union

በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ለሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ምህንድስናና ሂሳብ (STEM) ፕሮግራም ሰልጣኝ ለሆኑት ተማሪዎች በእንኳን ደህና መጣችሁ ፕሮግራም አቀባበል ተደረገላቸው።
***********************************************

በክረምቱ መርሀ ግብር ፕሮግራም በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ምህንድስናና ሂሳብ (STEM) ፕሮግራም ላይ ለመሳተፍ የመጡት ተማሪዎች በቁጥር 153 ሲሆኑ በጉራጌ ዞን ከሚገኙ ከ7ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ካሉት ተማሪዎች መካከል የተውጣጡና የተሻለ ውጤት ያስመዘገቡ ጎበዝ ተማሪዎች መሆናቸውን የዩኒቨርሲቲው የህዝብና አለም አቀፍ ዳይሬክቶሬት በማህበራዊ ትስስር ገፁ አሳውቋል፡፡

በፕሮግራሙ መክፈቻ ላይ የማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክተር የሆኑት ረዳት ፕሮፌሰር ክፍሌ ሌንቲሮ እንደገለጹት ዩኒቨርሲቲው ለተማሪዎች ስልጠናውን ከመስጠት ባሻገር በማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት፣ በፕሮግራሙ አስተባባሪና በዩኒቨርሲቲው የኢንዱስትሪ ትስስር ዳይሬክቶሬት አማካይነት ለተማሪዎቹ ተገቢ የሆነ ክትትልና ድጋፍ እንደሚያደረግላቸው ገልፀዋል፡፡

ዶክተር ዮሀንስ ገብሩ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት በበኩላቸው እንደገለፁት ተማሪዎች በቆይታቸው የዩኒቨርሲቲ ህይወት ምን እንደሚመስል በመረዳት በተለይም ተገቢውን ዕውቀት እንደሚገበዩና ተግባር ተኮር ስልጠናን መሰረት ያደረገ ትምህርት እንደሚሰጣቸው ገልፀዋል፡፡

ዶክተር ሀብቴ ዱላ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት በበኩላቸው እንደገለጹት ተማሪዎች ለምን እንደመጡ መገንዘብ እንደሚገባቸው፣ በአግባቡ የትምህርት ጊዜያቸውን ሳይሸራርፉ መጠቀም እንዳለባቸው በመግለፅ መልካም የስልጠና ጊዜ እንዲሆንላቸው ምኞታቸውን ገልፀዋል፡፡

ተማሪዎቹ በቆይታቸው በመምህራን አማካይነት ተገቢው ተግባር ተኮር ስልጠና እንደሚሰጣቸው፣ በሚመለከታቸው አካላት አማካይነት በቅርብ ለሚያጋጥሟቸው ችግሮች ሁሉ መፍትሄ እንደሚሰጣቸውና የምግብና የመኝታ አገልግሎትም በዩኒቨርሲቲው በኩል እንደሚያገኙ ለማወቅ ተችሏል፡፡


የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ህብረት
"OUR REWARD IS STUDENT'S HAPPINESS!!!"

የተለያዩ መረጃዎችን ለማግኘት ከእኛ ጋር ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook
https://www.facebook.com/WKUStudentUnion
Telegram @WkUSU
Website https://wkusu.com

ለየትኛውም አስተያየት እና ጥያቄ
EMAIL
student.union@wku.edu.et
ለአብሮነቶ ከልብ እናመሰግናለን