2021-07-02 09:06:35
እጃችሁ ላይ ገንዘብ ከሌላችሁ . . .
በዚህ ምድር ላይ ስትኖሩ ከገንዘብ ውጪ ምንም ነገር ማድረግ እስከማትችሉ ድረስ የገንዘብ አስፈላጊነት እጅግ የጎላ ነው፡፡ ይህንን አባባል ሲሰሙ፣ አንዳንድ ወጣቶች፣ “እኔ እኮ ከገንዘብ ውጪ እየኖርኩ ነው” ብለው ያስባሉ፡፡ እንደዚያ የሚሉት ግን እነሱ ራሳቸው ገንዘብ ባያወጡም ለመጠለያ ጣሪያ፣ ለአካላቸው ልብስና ለሆዳቸው ምግብ እያቀረበ ያለ አንድ ሰው እንዳለ በመዘንጋት ነው፡፡ ስለዚህ ለመኖር ወይ እኛው ገንዘብ እናወጣለን ወይም ደግሞ ሌላውን ሰው ገንዘብ እናስወጣለን፡፡
ምንም እንኳን ከገንዘብ ጋር ባንወለድም አንዳንድ ሰዎች ግን ከቤተሰብ ውርስ ወይም ከሌሎች “እድሎች” የተነሳ ሳይለፉ ገንዘብ እጃቸው ላይ ይገባል፡፡ ነገር ግን፣ እኛ የዚህ አይነቱ ገንዘብን የማግኘት እድሉ የሌለን ምን እናድረግ?፡፡ ይህ ወሳኝ ጥያቄ ነው፡፡
እውነት እንነጋገር ብንል፣ በአሁን ሰዓት ያላችሁን ጥያቄዎች በሚገባ ብትመለከቷቸው ምናልባት አብዛኛዎቹ ከገንዘብ ጋር ተገናኝተው ታገኟቸዋላችሁ ብዬ አስባለሁ፡፡ ለአሁኑ ይህ እንዳልሆነ ካሰባችሁ ደግሞ አንዳንድ የግል ሕይወት አቅጣጫዎችን ለመከተል ሙከራ ማድረግ ስትጀምሩ እውነታውን ስለምትደርሱበት ለአሁኑ ችግር የለውም፡፡
በኑሮ ለማደግና የራሳችሁን ሕይወት ለመመስረት እጃችሁ ላይ ገንዘብ ከሌላችሁ ወደዚያ ደረጃ ለማደግ የሚከተሉትን ነጥቦች ለማስታወስ ሞክሩ . . .
1. ጠንካራ ዓላማ (ራእይ) ይኑራችሁ
አንድን ነገር ለማከናወን ጽኑ የሆነ ፍላጎት ሊኖረን ይገባል፡፡ ያንን ጽኑ ፍላጎት የሚሰጠን ደግሞ ወደፊት እንዲሆንልን የምንመኘውና የምንጓጓለት አንድ ነገር ሲኖረን ነው፡፡ ስለሆነም ገንዘብ ብናገኝ ልንደርስበት የምንፈልገውን ጠንካራ ዓላማ ስንይዝ በዚህም በዚያም ብለን መንገድን እንድንፈልግ የማይበርድን መነሳሳት ይሰጠናል፡፡
2.7K viewsሳሙኤል, 06:06