Get Mystery Box with random crypto!

ወሸባ

የቴሌግራም ቻናል አርማ wesheba — ወሸባ
የቴሌግራም ቻናል አርማ wesheba — ወሸባ
የሰርጥ አድራሻ: @wesheba
ምድቦች: ስነ-ጽሁፍ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.23K

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-05-09 16:06:40 Channel photo removed
13:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-21 15:41:47 https://shopify.com/referrals/friend?utm_term=74226041135&utm_content=merchant-referral&utm_campaign=100_m2m&utm_source=open_home&utm_medium=web
32 viewsሳሙኤል, 12:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-10 11:39:02 https://t.me/EthioBooksclub
280 viewsሳሙኤል, 08:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-01 17:26:40

206 viewsሳሙኤል, 14:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-09 08:19:26
የህፃኗን ህይወት እናድን እኔ የምችለውን ተወጥቻለሁ እናንተስ?

ህፃን ሰበነማርያም ትባላለች ገና የ1 አመት ከስድስት ወር ህፃን ስትሆን በዚህ ዕድሜዋ በልብ ህመም እየተሰቃየች ትገኛለች።

የተለያዩ ህክምና ተከታትላለች ነገር ግን ዉጭ ሀገር ሂዳ ካልታከመች ህይወቷ አደጋ ላይ እንደሆነ በኢትዮጵያ የልብ ህሙማን መርጃ ማዕከል ተገልጿል።

ስለሆነም እያንዳንዳችን ቢያንስ ተርፎን ለአንደ ቀን መዝናኛ የምናወጣውን ወጭ ለዚች ታዳጊ ህይወት ብንረዳ ከፈጣሪ በረከትን የምናገኝ ይሆናል።

የህፃኗ አባት ማስተር አበራ ለብዙ የጎንደር ታዳጊ ህፃናት እና ወጣቶች ከሱስ የፀዳ ማህበረሰብ ለመፍጠር በሚደረገው ጥረት ትልቅ አስተዋፅኦ እያደረገ የሚገኝ ወጣት ነው ።

መልካም ስራ አልፎ ይጠብቃልና እኛም የዚህን ወጣት ልጅ ህይወት ለማዳን በተቻለ መጠን የምንችለውን እንደግፍ መርዳት ለምትፈልጉ፦

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ➺1000450728946
አቢሲኒያ ባንክ➺41993995
አዋሽ ባንክ➺01347564797700
እናት ባንክ➺0371122231034001 ድጋፍ እናድርግ።

መርዳትና አቅም የሌላችሁ ወገኖቸ ደግሞ ሌሎች እንዲረዷት ሼር በማድረግ ፈጣሪ ይማርሽ እንበላት።
1.4K viewsሳሙኤል, 05:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-07 14:45:32
2.4K viewsሳሙኤል, 11:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-07 14:45:30 የመሪነት ብቃቶች (Leaders Quality)
~~~
አንድ መሪ የሚተሉትን የመሪነት ብቃቶች ብቃቶች ሊያውቃቸውና ሊተገብራቸው ይገባል። እነርሱም፦
1/ ሙሉ ስብእና (Integrity) ያላቸው፡ መሪው የሚናገረውና የሚሠራው የማይጣረስ፣ ከራሱ አቅም በተረፈ የድርጅቱን ወይም ሓላፊነት የጣለበትን ማኅበረሰብ ጥቅም የሚያስቀድም ታማኝ እና ቅን አገልጋይ ሊሆን ይገባል።
.
2/ የለውጥ ሐዋርያ (Change Agents) መሪዎች ጠቃሚ ፋይዳ የማያስገኙ ልማዶች እና አስተሳሰቦች (Belief System) የሚያስወግዱ እና በየጊዜው ለራሳቸዉም እንዲሁም ለሌሎችም ለውጥን የሚያፋጥኑ እና ከፍተኛ ግለሰባዊ እና ተቋሟዊ ለውጦችን የሚያመጡ ናቸዉ።
.
3/ የቡድን ተጫዋች (Team Players)፡ በተናጥል ከመሥራት ይልቅ በቡድን መሥራትንና ሰዎችን በጋራ እንዲሠሩ የማስተባበር ብቃትና ክህሎት ያላቸው፤ የድርጅታቸዉን ወይንም ሓላፊነት የጣለባቸውን ማኅበረሰብ ዓላማ የማሳካት ከወሳኝ አጋሮችና ቁልፍ ግለሰቦች ጋር መረብ የሚዘረጉ እና ግንኙነቱም ዘለቄታዊ እንዲሆኑ የሚያስችሉ ናቸው።
.
4/ ፋናወጊ (Take Initiative)፡ በማንኛውም ሁኔታ ቀድመው የሚገኙ አስቸጋሪ በሆኑ ሁኔታዎች እና ጉዳዮች ተስፋ የማይቆርጡ የቡድን ስሜት እንዳይሰበር እና ያጋጠማቸውን እንቅፋት በቁርጠኝነት የሚወጡ ናቸው።
.
5/ ሰዎችን ያስቀድማሉ (People Centered)፡ ሁልጊዜ ለሰዎች ፍላጎት የሚጠነቀቁ አንድን ነገር በትእዛዝ ከማሠራት ይልቅ ሰዎች ፈልገው ሓላፊነት ተሰምቷቸዉ እንዲሠሩ የሚያደርጉ ናቸው።
.
6/ ውጤታማ መሪነት እራስን ዝቅ በማድረግ (Professionalism with humility)፣ ዉጤታማ መሪዎች ሁልጊዜ እራሳቸዉን ዝቅ የሚያደርጉ እና ከኔ ይልቅ በኔ ስር ያሉት ሁል ጊዜ ትክክል ናቸው (The subordinate is always right) ብለው የሚያምኑ ናቸው።
.
7/ ሥልጣን በአግባቡ የሚጠቀሙ ( Responsibility of using power ) መሪዎች የተሰጣቸውን ስልጣን በአግባቡ የሚጠቀሙ እና በሥልጣናቸዉ ለራሳቸዉ ጥቅም የማይሠሩ ሥልጣንን ከመጠቅለል (Power monger) ይልቅ ለሚመሩዋቸዉ ሥልጣንን የሚያጋሩ እና ሁል ጊዜም ተጠያቂነትን (Accountability) የሚያስቀድሙ ናቸው።
.
8/ ለራሳቸውና ለጤናቸዉ ጊዜ የሚሰጡ (Health-Conscious) መሪዎች እራሳቸውን አስፈላጊ የሥራ ጫና ውስጥ የሚከቱ አይደሉም። ይልቁንም ሥራ እና ሓላፊነትን ለሌሎች በአግባቡ በማጋራት ስልታዊ በሆኑ ነገሮች ላይ የሚያተኩሩ እና ለራሳቸው ጊዜ የሚሰጡ ጤናቸውንም በአግባቡ የሚጠብቁ እንዲሁም ከምንም በላይ የነሱ መልካም ጤና መኖሩ ሥራቸውን በተገቢው ፍጥነት እና በሙሉ አቅም በመወጣት ወሳኝ መሆኑን የሚረዱ እንዲሁም ጤናቸው ከሚጎዳና መልካም ሰብእናቸዉን ከሚጓደል ከአላስፈላጊ ሱሶች እራሳቸውን የሚጠብቁ ናቸው።
.
9/ ተተኪን ማፈራት የሚችሉ (Effective in succession leadership) መሪዎች ሁልጊዜ ራሳቸውን ለድርጅቱ ወይንም ሓላፊነት ለሰጣቸው ማኅበር ብቸኛ አስፈላጊ ሰው አድርገው አይቆጥሩም እኔ ሳልፍ ድርጅቱ /ማኅበሩ ሊቀጥል ይገባል ለዚህም እንደ እኔ ወይንም ከኔ የሚበልጡ መሪዎችን መፍጠር ይቻላል ብለው የሚያምኑ የሚፈጥሩ ሁልጊዜ ለሌሎች ውጤታማ መሪዎች እና አዳዲስ ዐሳቦች እራሳቸውን ክፍት የሚያደርጉ ናቸው።
ሠላም ለሁላችን!!
2.2K viewsሳሙኤል, 11:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-07 14:02:22
የአመለካከትን ለውጥ ለማምጣት የሚረዱ ስምንት ደረጃዎች
~~~
#አትኩረትን መቀየር፣ በጎ ነገሮችን መፈለግ
#አሁኑኑ ተግባራዊ የማድግ ልምድ ማዳበር
#አመስጋኝ የመሆን ልምድን ማዳበር
#ሁሌም በተከታታይነት ለመማር መትጋት
#ለራስ ከፍተኛ ግምት የመስጠት ልምድን ማጎልበት
#ከፀለምተኛ አስተሳሰብ መራቅ
#መሠራት ያለባቸውን ነገሮች በውዴታ መስራትን መማር
#ቀኑን በበጎ ነገር መጀመር
.
Ref. ለአሸናፊነት መገዛት
1.5K viewsሳሙኤል, 11:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-05 07:38:43
#Update

ከ6 ሰዓታት በላይ ተቋርጠው የቆዩት ፌስቡክ ፣ ዋትስአፕ ፣ ኢንስታግራም እንዲሁም ሜሴንጀር ወደ አገልግሎት ተመልሰዋል።

ፌስቡክ ለተፈጠረው ችግር ይቅርታ ከመጠየቅ ውጭ እስካሁን ችግሩ በምን ምክንያት እንደተፈጠረ ማብራሪያ አልሰጠም።

እንደብሉምበርግ ዘገባ ከሆነ በፌስቡክ መቋረጥ በ5 ሰዓታት ውስጥ ብቻ የማርክ ዙከርበርግ የግል ሃብት በ7 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ዝቅ ብሏል።
1.5K viewsሳሙኤል, 04:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-04 20:35:25
የአማረኛ ትርጉም!!

የአፍሪካ መሪዎች በመንግስት ምስረታ በአል ላይ ስለኢትዮጵያ ከተናገሩት ውስጥ
.
የኬኒያው ፕሬዝዳንት
ኢትዮጵያ እናታችን ናት እናት ከሌለች ቤተሰብ ይበተናል ኢትዮጵያ የአፍሪካ ነፃነት እናት ናት ኢትዮጵያ የፖን አፍሪካኒዝምን መሰረት የጣለች በቅኝ ግዛት ስር ያልወደቀች ሐገር ናት።
_

የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት
ኢትዮጵያ ታላቋ እናታችን ናት፤ ደቡብ ሱዳን ያለ ኢትዮጵያ ድጋፍ እዚህ አትደርስም ነበር፤
ምንጊዜም ከጎናችሁ ነን፤ የትም መሄድ ብትፈልጉ አብረናችሁ እንጓዛለን፤

_
የዩጋንዳ ፕሬዝደንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ
የማንነት(የብሔርና የሐይማኖት) ፖለቲካን ገተን የጥቅም (interest) ፖለቲካን ስንተካ ዩጋንዳን ማዳን ችለናል፡፡ ለኢትዮጵያውያንም የምንመክረው ይህንኑ ነው።"

_
የጅቡቲ ፕሬዝደንት እስማኤል ኦማር ጉሌህ
ኢትዮጵያ ጥንታዊት አፍሪካዊት ሃገር ናት። ኢትዮጵያውያን ችግራቸውን በራሳቸው እንደሚፈቱ አምናለሁ። ኢትዮጵያ በበርካታ ፈተናዎች ባለፈች ጊዜ ሁሉ ሁሌም ጠንክራ እንደምትወጣ እናቃለን።
_
የሴኔጋል ፕሬዝዳንት ማኪ ሳል
የአፍሪካ አንድነት መስራችና የአፍሪቃዊነት ምሳሌ ኢትዮጵያ ናት።
_

የናይጄርያ ፕሬዝዳንት መሀመዱ ቡሀሪ
የሰኔው ምርጫ ኢትዮጵያውያን ለዲሞክራሲ ያላቸውን ቁርጠኝነት ያሳዩበት ነው። ናይጄርያ የኢትዮጵያን የወሰን አንድነትና ሰላም ሁሌም ትደግፋለች።
_
የሱማሊያ ፕሬዝዳንት መሀመድ አብዱላሂ ፎርማጆ፦ ኢትዮጵያውያን ዲሞክራሲን ለማጠናከር ላደረጉት ጥረት እንኳን ደስ አላችሁ እላለሁ። ሱማሊያ ለምስራቅ አፍሪካ እድገት ሁሌም ከኢትዮጵያ ጋር ትሰራለች
_
የዲሞክራቲክ ኮንጎ ጠ/ሚ ጄን-ሚሼል ልኮ
የአፍሪካ አንድነትና ብልፅግና ለማጠናከር ሀገሬ ከኢትዮጵያ ጋር ትሰራለች።
1.4K viewsሳሙኤል, 17:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ