Get Mystery Box with random crypto!

የመሪነት ብቃቶች (Leaders Quality) ~~~ አንድ መሪ የሚተሉትን የመሪነት ብቃቶች ብቃቶች | ወሸባ

የመሪነት ብቃቶች (Leaders Quality)
~~~
አንድ መሪ የሚተሉትን የመሪነት ብቃቶች ብቃቶች ሊያውቃቸውና ሊተገብራቸው ይገባል። እነርሱም፦
1/ ሙሉ ስብእና (Integrity) ያላቸው፡ መሪው የሚናገረውና የሚሠራው የማይጣረስ፣ ከራሱ አቅም በተረፈ የድርጅቱን ወይም ሓላፊነት የጣለበትን ማኅበረሰብ ጥቅም የሚያስቀድም ታማኝ እና ቅን አገልጋይ ሊሆን ይገባል።
.
2/ የለውጥ ሐዋርያ (Change Agents) መሪዎች ጠቃሚ ፋይዳ የማያስገኙ ልማዶች እና አስተሳሰቦች (Belief System) የሚያስወግዱ እና በየጊዜው ለራሳቸዉም እንዲሁም ለሌሎችም ለውጥን የሚያፋጥኑ እና ከፍተኛ ግለሰባዊ እና ተቋሟዊ ለውጦችን የሚያመጡ ናቸዉ።
.
3/ የቡድን ተጫዋች (Team Players)፡ በተናጥል ከመሥራት ይልቅ በቡድን መሥራትንና ሰዎችን በጋራ እንዲሠሩ የማስተባበር ብቃትና ክህሎት ያላቸው፤ የድርጅታቸዉን ወይንም ሓላፊነት የጣለባቸውን ማኅበረሰብ ዓላማ የማሳካት ከወሳኝ አጋሮችና ቁልፍ ግለሰቦች ጋር መረብ የሚዘረጉ እና ግንኙነቱም ዘለቄታዊ እንዲሆኑ የሚያስችሉ ናቸው።
.
4/ ፋናወጊ (Take Initiative)፡ በማንኛውም ሁኔታ ቀድመው የሚገኙ አስቸጋሪ በሆኑ ሁኔታዎች እና ጉዳዮች ተስፋ የማይቆርጡ የቡድን ስሜት እንዳይሰበር እና ያጋጠማቸውን እንቅፋት በቁርጠኝነት የሚወጡ ናቸው።
.
5/ ሰዎችን ያስቀድማሉ (People Centered)፡ ሁልጊዜ ለሰዎች ፍላጎት የሚጠነቀቁ አንድን ነገር በትእዛዝ ከማሠራት ይልቅ ሰዎች ፈልገው ሓላፊነት ተሰምቷቸዉ እንዲሠሩ የሚያደርጉ ናቸው።
.
6/ ውጤታማ መሪነት እራስን ዝቅ በማድረግ (Professionalism with humility)፣ ዉጤታማ መሪዎች ሁልጊዜ እራሳቸዉን ዝቅ የሚያደርጉ እና ከኔ ይልቅ በኔ ስር ያሉት ሁል ጊዜ ትክክል ናቸው (The subordinate is always right) ብለው የሚያምኑ ናቸው።
.
7/ ሥልጣን በአግባቡ የሚጠቀሙ ( Responsibility of using power ) መሪዎች የተሰጣቸውን ስልጣን በአግባቡ የሚጠቀሙ እና በሥልጣናቸዉ ለራሳቸዉ ጥቅም የማይሠሩ ሥልጣንን ከመጠቅለል (Power monger) ይልቅ ለሚመሩዋቸዉ ሥልጣንን የሚያጋሩ እና ሁል ጊዜም ተጠያቂነትን (Accountability) የሚያስቀድሙ ናቸው።
.
8/ ለራሳቸውና ለጤናቸዉ ጊዜ የሚሰጡ (Health-Conscious) መሪዎች እራሳቸውን አስፈላጊ የሥራ ጫና ውስጥ የሚከቱ አይደሉም። ይልቁንም ሥራ እና ሓላፊነትን ለሌሎች በአግባቡ በማጋራት ስልታዊ በሆኑ ነገሮች ላይ የሚያተኩሩ እና ለራሳቸው ጊዜ የሚሰጡ ጤናቸውንም በአግባቡ የሚጠብቁ እንዲሁም ከምንም በላይ የነሱ መልካም ጤና መኖሩ ሥራቸውን በተገቢው ፍጥነት እና በሙሉ አቅም በመወጣት ወሳኝ መሆኑን የሚረዱ እንዲሁም ጤናቸው ከሚጎዳና መልካም ሰብእናቸዉን ከሚጓደል ከአላስፈላጊ ሱሶች እራሳቸውን የሚጠብቁ ናቸው።
.
9/ ተተኪን ማፈራት የሚችሉ (Effective in succession leadership) መሪዎች ሁልጊዜ ራሳቸውን ለድርጅቱ ወይንም ሓላፊነት ለሰጣቸው ማኅበር ብቸኛ አስፈላጊ ሰው አድርገው አይቆጥሩም እኔ ሳልፍ ድርጅቱ /ማኅበሩ ሊቀጥል ይገባል ለዚህም እንደ እኔ ወይንም ከኔ የሚበልጡ መሪዎችን መፍጠር ይቻላል ብለው የሚያምኑ የሚፈጥሩ ሁልጊዜ ለሌሎች ውጤታማ መሪዎች እና አዳዲስ ዐሳቦች እራሳቸውን ክፍት የሚያደርጉ ናቸው።
ሠላም ለሁላችን!!