Get Mystery Box with random crypto!

የአማረኛ ትርጉም!! የአፍሪካ መሪዎች በመንግስት ምስረታ በአል ላይ ስለኢትዮጵያ ከተናገሩት ውስጥ | ወሸባ

የአማረኛ ትርጉም!!

የአፍሪካ መሪዎች በመንግስት ምስረታ በአል ላይ ስለኢትዮጵያ ከተናገሩት ውስጥ
.
የኬኒያው ፕሬዝዳንት
ኢትዮጵያ እናታችን ናት እናት ከሌለች ቤተሰብ ይበተናል ኢትዮጵያ የአፍሪካ ነፃነት እናት ናት ኢትዮጵያ የፖን አፍሪካኒዝምን መሰረት የጣለች በቅኝ ግዛት ስር ያልወደቀች ሐገር ናት።
_

የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት
ኢትዮጵያ ታላቋ እናታችን ናት፤ ደቡብ ሱዳን ያለ ኢትዮጵያ ድጋፍ እዚህ አትደርስም ነበር፤
ምንጊዜም ከጎናችሁ ነን፤ የትም መሄድ ብትፈልጉ አብረናችሁ እንጓዛለን፤

_
የዩጋንዳ ፕሬዝደንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ
የማንነት(የብሔርና የሐይማኖት) ፖለቲካን ገተን የጥቅም (interest) ፖለቲካን ስንተካ ዩጋንዳን ማዳን ችለናል፡፡ ለኢትዮጵያውያንም የምንመክረው ይህንኑ ነው።"

_
የጅቡቲ ፕሬዝደንት እስማኤል ኦማር ጉሌህ
ኢትዮጵያ ጥንታዊት አፍሪካዊት ሃገር ናት። ኢትዮጵያውያን ችግራቸውን በራሳቸው እንደሚፈቱ አምናለሁ። ኢትዮጵያ በበርካታ ፈተናዎች ባለፈች ጊዜ ሁሉ ሁሌም ጠንክራ እንደምትወጣ እናቃለን።
_
የሴኔጋል ፕሬዝዳንት ማኪ ሳል
የአፍሪካ አንድነት መስራችና የአፍሪቃዊነት ምሳሌ ኢትዮጵያ ናት።
_

የናይጄርያ ፕሬዝዳንት መሀመዱ ቡሀሪ
የሰኔው ምርጫ ኢትዮጵያውያን ለዲሞክራሲ ያላቸውን ቁርጠኝነት ያሳዩበት ነው። ናይጄርያ የኢትዮጵያን የወሰን አንድነትና ሰላም ሁሌም ትደግፋለች።
_
የሱማሊያ ፕሬዝዳንት መሀመድ አብዱላሂ ፎርማጆ፦ ኢትዮጵያውያን ዲሞክራሲን ለማጠናከር ላደረጉት ጥረት እንኳን ደስ አላችሁ እላለሁ። ሱማሊያ ለምስራቅ አፍሪካ እድገት ሁሌም ከኢትዮጵያ ጋር ትሰራለች
_
የዲሞክራቲክ ኮንጎ ጠ/ሚ ጄን-ሚሼል ልኮ
የአፍሪካ አንድነትና ብልፅግና ለማጠናከር ሀገሬ ከኢትዮጵያ ጋር ትሰራለች።