Get Mystery Box with random crypto!

ወቅታዊ NEWS

የቴሌግራም ቻናል አርማ wektawinews — ወቅታዊ NEWS
የቴሌግራም ቻናል አርማ wektawinews — ወቅታዊ NEWS
የሰርጥ አድራሻ: @wektawinews
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 248
የሰርጥ መግለጫ

We adress you the most important but ወቅታዊ news. We are in this together. We are here for each other.
@Wektawinews

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2020-08-02 14:47:24
#ማስታወሻ

#ኢትዮጵያዊያን ዛሬ ከቀኑ 10፡00 ሠዓት ለሕዳሴው ግድብ ከያሉበት ድምፃቸውን ያሰማሉ

"ድምፃችን ለግድባችን" የተሰኘና በመላው ዓለም ያሉ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ውሃ ሙሌትን በተመለከተ ደስታቸውን እንዲገልፁ ለማደረግ ያለመ ዝግጅት ዛሬ ሐምሌ 26 ቀን 2012 ዓ.ም ይከናወናል።

ከቀኑ 10፡00 ሠዓት ላይ በመላው ዓለም የሚገኙና የግድቡ እዚህ መድረስ ደስታ የፈጠረላቸው ሰዎች ለ3 ደቂቃ በያሉበት ሆነው ደስታቸውን በፈለጉት መንገድ እንዲገልፁም ተጠይቋል።

ይህን ዝግጅትና የግድቡን አሁናዊ ሁኔታ በተመለከተ በተሰጠው መግለጫ እንደተነገረው ሁሉም ሰው ከዛሬ ጀምሮ ደስታውን ለመግለፅ መዘጋጀት አለበት።

ለዚህም ድርጅቶች፣ የግለሰብ ቤቶችና #ተሽከርካሪዎች ጭምር #በሰንደቅ ዓላማ ያሸበርቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በመላው ዓለም ያሉ የደስታው ተጋሪዎችም የአገር ባሕል ልብስ በመልበስና ራሳቸውን ከኮሮና ቫይረስ በመጠበቅ ደስታቸውን እንዲገልፁ መልዕክት ተላልፏል።

@Wektawinews
966 views11:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-06-30 08:02:18 #RIP_HACHALU

የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በአርቲስት
ሀጫሉ ሁንዴሳ ህልፈተ ህይወት የተሰማቸውን ሀዘን ገልፀዋል።

ፕሬዚደንቱ በሀዘን መግለጫቸው "በፊንፊኔ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ጀግናው ወንድማችን ፣ ደማችን ፣ የትግል የለውጥ ምልክት የሆነው አርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ በመሳሪያ መመታቱን ሰማን፡፡ መረጃውን እንደሰማን ጉዳዩን ለማጣራት እና የወንድማችንን ህይወት ለማትረፍ በአቅራቢው ካሉ አካላት ጋር በመሆን ትልቅ ርብርብ ተደርጎ ነበር"ማለታቸውንና ኦቢኤን አማርኛ ዘግቧል፡፡

"በሀጫሉ ህልፈተ ህይወት እንደ አንድ አብሮ አደግ፣እንደ ትግል ጓድ እና እንደ አንድ ጀግና
የተሰማኝ ሀዘን ከፍተኛ ነው፡፡ ሀጫሉ አርቲስት ብቻ አይደለም አመራርም ነው፤ ለእኔ ደግሞ ወንድሜ አማካሪዬ ነው፤ ይህን ጀግና ነው ያጣነው፡፡

የዚህ ጀግና ግድያ እንደተራ ነገር የሚታለፍ አይደለም፤ ግድያውም ተራ አይደለም። ታስቦበት የተፈፀመ ግድያ ነው፤ በዚህ ምንም ጥርጥር የለኝም" ብለዋል አቶ ሽመልስ።

በዚህ ድርጊት የተጠረጠሩት የተወሰኑ አካላት በቁጥጥር ስር መዋላቸውንና ምርመራ መጀመሩን ፕሬዝዳንቱ ገልፀዋል። "የፀጥታ አካላትም በሁሉም አቅጣጫ ተሰማርተዋል። ለውጡን የማይፈልጉ አካላት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከመጠን በላይ ሲዝቱ ቆይተዋል፤ ለውጡንም ለማደናቀፍ ብዙ ሙከራዎች አድርገዋል፡፡ እንደዚህ አይነት ድርጊቶችን ለመቀልበስ የኦሮሚያ ፖሊስ እና የሀገሪቱ የፀጥታ አካላት ከፍተኛ ጥረት በማድረግ የተለያዩ እርምጃዎችን ሲወስዱ ቆይተዋል።

ዛሬ ደግሞ ብሄር ብሄረሰቦችን ለማጫረስ እንዲሁም የሀገርን ህልውና ለመናድ አቅደው ይህን ድርጊት ስለመፈፀማቸው ጥርጥር የለኝም" ነው ያሉት አቶ ሽመልስ።

ፕሬዘዳንቱ አክለውም "ድርጊቱን የኦሮሞ ህዝብ እና የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች በሰከነ ሁኔታ በመገንዘብ ተጠርጣሪዎቹንም አብረን በመቆም ጀግናው ታጋይ ሀጫሉ የተሰዋለት የለውጥ ትግልም ወደ ኋላ እንደማይቀለበስ ይልቁንም ለውጡ እንዲሳካ እጅ ለእጅ ተያይዘን በመረጋጋት እና በመናበብ ይህን አስቸጋሪ ጊዜ እንድንሻገር ጥሪዬን አቀርባለሁ" ብለዋል ፕሬዝዳንቱ በላኩት መግለጫ፡፡ ሁሉም የመንግስት መዋቅር በሀገሪቱ ላይ የተጋረጠውን አደጋ ለመታደግ በአንድነት መቆም እንዳለበትም ገልፀዋል፡፡ ይህን ወንጀል የፈፀሙ አካላት በቀጣይ ሊያደርጉ ያቀዱትን ስለማናውቅ ሁሉንም ነገር በተረጋጋ ሁኔታ ማየት እና ማጤን አለብንም ብለዋል አቶ ሽመልስ፡፡

በመጨረሻም ለቤተሰቡ፣ ለዘመድ አዝማዱ እና ለኦሮሞ ህዝብ ሁሉ ፕሬዘዳንቱ መፅናናትን ተመኝተው" ታጋይ ቢወድቅም ትግሉ ይቀጥላል" ብለዋል::

@Wektawinews
769 viewsedited  05:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-06-30 07:46:00
አርቲስት ሃጫሉ መገደሉን ፖሊስ አስታወቀ!

አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ በጥይት ተመትቶ ሆስፒታል ከገባ በኃላ እርዳት ሲደረግለት ቆይቶ ህይወቱ ማለፉን ማረጋገጡን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።

ከግድያው ጋር በተያያዘ የተወሰኑ ተጠርጣሪዎች መያዛቸውን ፖሊስ ያስታወቀ ሲሆን በአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያ የተሳተፉ አካላትን ፖሊስ የማጣራት ስራ በመስራት ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ ገልጿል።

@Wektawinews
620 views04:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-06-26 16:07:39
በቦሌ ሚካኤል አየር አምባ ት/ቤት አካባቢ ዛሬ እኩለ ቀን ለደቂቃዎች የቆየ ተኩስ ልውውጥ ተፈጥሮ ነበር!

ከተኩስ ልውውጡ በኋላ ካፒታል ጋዜጣ በቦታው በመገኘት እንደዘገበው በጥይት ተመቶት የወደቀ ሆኖም በሸራ የተሸፈነ ሰው ይታይ ነበር፡፡ እንዲሁም አንድ ግለሰብ መሬት ላይ ተኝቶ ማየት የተቻለ ሲሆን ግለሰቡ እንቅስቃሴ ያሳይ እንደነበር ከርቀት ለመታዘብ ችያለሁ ብሏል።

በአካባቢው የነበሩ የፌደራል ፖሊስ አባላት ለጋዜጣው እንዳረጋገጡት የነበረው የተኩስ ልውውጥ ከዝርፊያ ጋር የሚገናኝ ነው፡፡ በዘራፊነት የተጠረጠሩት ግለሰቦችም የፌደራል ፖሊስን የደንብ ልብስ በመልበስ ለወንጀል የተሰማሩ የነበሩ ሆኖም አባል ያልሆኑ ናቸው ሲሉ ገልፀዋል፡፡

የአይን እማኞች እንደገለፁት የተኩስ ልውውጡ ከሁለቱም ወገን ማለትም ከፀጥታ አካላት እንዲሁም ተጠርጥረው ከሚያመልጡት ወገን እንደነበር አስረድተዋል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ በመኪና ለማምለጥ ጥረት እያደረጉ እንደነበር የገለፁት የአይን እማኞች መኪናዋ በጥይት ተመትታ ትዛዝ ሆቴል የሚባል አካባቢ ቆማ ትገኛለች፡፡
በአካባቢው የነበሩ የፌደራል ፖሊስ አባላት ጉዳዩ ገና በመጣራት ላይ ያለ ነው ብለዋል።

ካፒታል ጋዜጣ

#EBC
@Wektawinews
643 views13:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-06-26 14:24:24
በአስገድዶ መድፈር ወንጀል የተከሰሰው ግለሰብ በ 25 አመት ፅኑ እስራት ተቀጣ

ተከሳሽ ደስታ ገበየሁ የተባለ ግለሰብ ቀኑ ነሀሴ ወር 2011 ዓ.ም ዕድሜቸው ስምንት እና ዘጠኝ አመት የሆነ ሁለት ሴት ህፃናቶችን በተለያዩ ቀናቶች በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ክልል ውስጥ በሚገኝው ተከራይቶ ከሚኖርበት ቤት ውስጥ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈፀመባቸው በመሆኑ የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ዐቃቂ ቃሊቲ ምድብ ፅ/ቤት የኢፌዲሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 627(1) ተላልፎ በመገኘቱ አራት ክሶችን መስርቶበታል፡፡

ተከሳሹ ፍርድ ቤት ቀርቦ ክሱን ክዶ የተከራከረ ቢሆንም ዐቃቤ ህግ በተከሳሽ ላይ ማስረጃ አቅርቦ በማሰማቱ እንዲሁም ተከሳሽ የተከሰሰበትን ክስ ሊያስተባብል ባለመቻሉ ፍርድ ቤቱ ተከሳሽን በአራቱም ክሶች ጥፋተኛ ነህ በማለት ሰኔ 16 ቀን 2012 ዓ.ም በዋለው ችሎት በ60 አመት እንዲቀጣ የፈረደበት ቢሆንም የተከሰሰበት ድንጋጌ ጣሪያው 25 ዓመት በመሆኑ በ 25 አመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ ተሰጥቷል፡፡

በሌላ በኩል በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ከሴቶችና ህፃናት ወንጀል ጋር ተያይዞ ከመጋቢት ወር 2012 ዓ.ም ጀምሮ 19 የምርመራ መዝገቦች ቀርበው የተጣሩ ሲሆን በ8 መዝገቦች ላይ ክስ ተመስርቶ ለችሎት መቅረባቸውን የአቃቂ ቃሊቲ ምድብ ጽፈት ቤት ምክትል ኃላፊ ሲሳይ ጎኣ የገለጹ ሲሆን ቀሪዎቹ መዝገቦች በምርመራና በመወሰን ሂደት ላይ እንደሆኑ ምክትል ኃላፊ አብራርተዋል፡፡

በመሆኑም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሴቶችና ህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች ቁጥራቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመምጣቱ ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግና ድርጊቱ ተፈፅሞ ሲያገኝም በተቻለ ፍጥነት ለፓሊስ ማሳወቅ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

@Wektawinews
492 views11:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-06-24 20:36:37
በቦሌ ለሚ ኢንደስትሪ መንደርና አካባቢው በተፈፀመ የከፍተኛ ኃይል ተሸካሚ ምሰሶ ስርቆት የኢንደስትሪ መንደሩን ጨምሮ በሰሚት፣ በቦሌ አራብሳ፣ በጎሮ፣ በአይሲቲ ፓርክ፣ በገርጂ ወረገኑ፣ በገርጂ እና ካሳንቺስ አካባቢዎች የኃይል መቋረጥ አጋጥሟል።

132 ኪሎ ቮልት ኃይል ተሸካሚ ምሰሶ በዘራፊዎች ተፈቶና ተቆርጦ በመውደቁ እንዲሁም በሌላ ምሰሶ ላይ ተጨማሪ ጉዳት በመድረሱ ኃይል መቋረጡን የኢትዮዽያ ኤሌክትሪክ ሀይል አስታውቋል።

DW

@Wektawinews
396 views17:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-06-24 19:53:07
ቦርዱ #የትግራይ #ክልል ምክር ቤት ክልላዊ ምርጫ ለማድረግ ያቀረበውን ጥያቄ እንደማይቀበል አስአስታወቀ

ቦርድ ለጣቢያችን በላከው መግለጫ የትግራይ ክልል ምክር ቤት “ኮቪድ 19ኝን እየተከላከለ 6ኛውን ዙር ምርጫ ለማካሄድ የወሰነ በመሆኑ የኢፌዴሪ ህገ መንግስት በሚያዘው መሰረት ቦርዱ ውሳኔውን ተቀብሎ ምርጫውን እንዲያስፈፅም፣ ምርጫውን ለማካሄድ የሚያስፈልግ የሰው ሃይልና ሎጂስቲክስ ዝግጅት እንዲያደርግ እና ውሳኔውን ለምክር ቤቱ እንዲያሳውቀን” ሲል ጥያቄ አቅርቦ እንደነበር አስታውሷል፡፡

6ኛው ሃገራዊ ጠቅላላ ምርጫ የሚካሄድበት ጊዜ እንዲራዘም ምክንያት የሆነው የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ሁኔታ እንደገና ተገምግሞ ምርጫ ማካሄድ የሚያስችል ሁኔታ መፈጠሩ እስከረጋገጥ ድረስ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በየትኛውም የሃገሪቱ ክልል ምርጫ አያካሂድም ብሏል፡፡

በተጨማሪም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የፖለቲካ ፓርቲዎችን መመዝገብ፣ መቆጣጠር እና ማስተዳደር፣ የምርጫ ጊዜ ሰሌዳን ማውጣት፣ የምርጫውን ከተጽእኖ ነጻ እና ፍትሃዊ በሆነ መልኩ ማስፈጸም ስልጣን ያለው ብቸኛ ተቋም መሆኑንም አንስቷል፡፡

@Wektawinews
373 views16:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-06-24 16:43:57
በአማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓታት የኮሮናቫይረስ የናሙና ምርመራ የተደረገላቸው ሁሉም ከቫይረሱ ነጻ ሆነዋል

የአማራ ክልል ጤና ቢሮ እንዳስታወቀው ባለፉት 24 ሰዓታት ከቫይረሱ ያገገመ፣ ወደ ጽኑ ህሙማን ህክምና ክፍል የገባም ሆነ በቫይረሱ ምክንያት ህይወቱ ያለፈ የለም፡፡

በአማራ ክልል እስከ ዛሬ ሰኔ 17/2012 ዓ.ም ድረስ ለ11 ሺህ 880 ሰዎች የናሙና ምርመራ ተደርጎ በ277 ሰዎች ላይ ቫይረሱ ተገኝቷል፡፡

ቫይረሱ ተገኝቶባቸው በለይቶ ሕክምና መስጫ ማዕከላት የሚገኙ ሁሉም ታካሚዎች በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኙም ቢሮው አስታውቋል፡፡

እስከዛሬ በክልሉ 84 ሰዎች ከቫይረሱ አገግመዋል፤ ሁለት ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ምክንያት ሕይወታቸውን አጥተዋል፡፡

በትግራይ ክልልም ዛሬ የተመረመሩ ሰዎች ነፃ መሆናቸው ይታወሳል

@Wektawinews
338 views13:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-06-24 16:40:55
ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦

1. የ38 ዓመት ወንድ የአዲስ አበባ ነዋሪ፤ በህክምና ማዕከል በህክምና ላይ የነበረ።

2. የ19 ዓመት ሴት የሱማሌ ክልል ነዋሪ፤ በጤና ተቋም በህክምና ላይ የነበረች።

3. የ40 ዓመት ሴት የሱማሌ ክልል ነዋሪ፤ በጤና ተቋም በህክምና ላይ የነበረች።

@Wektawinews
328 views13:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-06-24 16:31:06
በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ከ5,000 አለፉ!

ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 4,034 የላብራቶሪ ምርመራ 186 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 5,034 ደርሷል።

ከጠቅላላው የላብራቶሪ ምርምራ ውስጥ 35 (15 ከጤና ተቋም እና 20 ከማህበረሰብ በተወሰደ ናሙና) ናሙናዎች በአስክሬን ላይ የተደረገ የላብራቶሪ ምርምራ ሲሆን ሁለት ናሙናዎች ከጤና ተቋም የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶበቸዋል።

በተጨማሪ አንድ በህክምና ማዕከል ውስጥ በህክምና ላይ የነበር ሰው ህይወት አልፏል። በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸው እና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ሰባ ስምንት (78) ደርሷል፡፡

በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት ሰባ አራት (74) ሰዎች (63 ከአዲስ አበባ፣ 6 ከትግራይ ክልል፣ 2 ከሶማሊ ክልል፣ 2 ከደ/ብ/ብ/ሕ ክልል፣ እና 1 ሐረሪ ክልል) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 1486 ነው።

@Wektawinews
318 views13:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ