Get Mystery Box with random crypto!

#Update ዛሬ በናይሮቢ #በተፈረመው_ስምምነት መሰረት ፤ በሚቀጥሉት 7 ቀናት ወታደራዊ ሀላፊዎ | 🗣 ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹

#Update

ዛሬ በናይሮቢ #በተፈረመው_ስምምነት መሰረት ፤ በሚቀጥሉት 7 ቀናት ወታደራዊ ሀላፊዎቹ ለወታደሮቻቸው ኦረንቴሽን እንደሚሰጡና ከዛም የፌደራል ባለስልጣናት በትግራይ ኃላፊነታቸውን እንደሚረከቡ ይገልፃል።

የከባድ መሳርያዎች ትጥቅ አፈታትም በትግራይ ክልል ያሉ የውጭ ኃይሎች እና ከሀገር መከላከያ ሰራዊት ውጭ ያሉ ኃይሎች ከክልሉ መውጣት ጋር በአንድ ግዜ እንደሚፈፀም ይገልጻል።

የቀላል መሳርያዎች ትጥቅ አፈታትን ለማሳለጥ ከሁለቱም ወገን የተውጣጣ ኮሚቴ እንደሚቋቋምም የስምምነት ሰነዱ ላይ ሰፍሯል።

(Credit : ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት)

ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን  መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም 
@wektawi_Merej