Get Mystery Box with random crypto!

ስድስት አትሌቶች በልምምድ ላይ እንዳሉ የትራፊክ አደጋ ደረሰባቸው እሁድ እለት በልምምድ ላይ የነ | 🗣 ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹

ስድስት አትሌቶች በልምምድ ላይ እንዳሉ የትራፊክ አደጋ ደረሰባቸው

እሁድ እለት በልምምድ ላይ የነበሩ ስድስት ስማቸው ያልተጠቀሰ አትሌቶች ደርቦ በመሄድ ላይ በነበረ ተሽከርካሪ ተገጭተው ከባድ እንዲሁም ቀላል የመኪና አደጋ እንደደረሰባቸው በኦሮሚያ ልዩ ዞን አዲስ አበባ ዙሪያ የትራፊክ ደህንነት እና ቁጥጥር ዲቪዥን ኃላፊ የሆኑት ረዳት ኢኒስፔክተር ድሪባ ኩማ በተለይም ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

አደጋው የደረሰው ከጠዋቱ አራት ሰዓት ተኩል ላይ ስልጠና ላይ በነበሩ ስድስት አትሌቶች ላይ ሲሆን ኮድ 3 55562 ኦሮ የሆነ የህዝብ ማመላለሻ ሚኒባስ ከሰንዳፋ ወደ አዲስ አበባ በመሄድ ላይ በነበረበት ወቅት መሆኑ ተገልጿል፡አደጋው ልዩ ቦታው ገብርኤል መሳለሚያ ድልድይ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ላይ ሲሮጡ በነበሩ ስድስት አትሌቶች ላይ አደጋ ማድረሱ ተነግሯል፡፡

አያይዘውም እንደገለጹት አደጋው ከደረሰ በኃላ አትሌቶቹ ወደ አዲስ አበባ ምኒሊክ ሆስፒታል መወሰደቸውን እና በቀጣይ ልምምድ በሚያደርጉበት ጊዜ መኪና መንገድ ወጣ ያለ አካባቢ እንዲሆን እንዲሁም በእንቅስቃሴያቸው በሙሉ ጥንቃቄም እንዳይጎድላቸው ረዳት ኢኒስፔክተር ድሪባ ኩማ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም
https://t.me/Merja01