ድሮ ድሮ ብሶት በወለደው በዘመነ ኢህአዴግ ¤¤¤¤ ድሮ ድሮ ከአድማስ ዩኒቨርሲቲ በዲፕሎማ ለተመረቀ ልጃቸው በሬ አርደው የሚደግሱ ቤተሰቦች ነበሩ ¤ ድሮ ድሮ ኑሮ ጥሩ ስለነበረ ህዝቡ ደረጄና ሀብቴ "ሙያሽ ይዘርዘርልሽ" እያሉ ሲዘፍኑ ሆዱን ይዞ ይስቅ ነበር ¤ ድሮ ድሮ ወደደብረ ማርቆስ የሚጓዝ አውቶቡስ ውስጥ የታደለ ገመቹን የነቀምት አውቶቡስ ውስጥ የሰማኸኝ በለውን ዘፈን መስማት ኖርማል ነበር ¤ ድሮ ድሮ ታመን ጤና ጣቢያ ስንሄድ ከመድኃኒቱ በፊት ወተትና ስጋ መመገብ እንዳትረሱ የሚል ማስጠንቀቂያ ይሰጠን ነበር ¤ ድሮ ድሮ አንድ ሱፍ ለመስፋት 30 ሜትር ጨርቅ እንጠቀም ነበር ¤ ድሮ ድሮ አዜብ መስፍን የተባሉ የቤት እመቤት ባለቤታቸው በሚከፈላቸው 7500 ብር ወርሃዊ ደመወዝ ድልቅቅ ብለው እንደሚኖሩ ከታይላንድ ጉብኛታቸው በዃላ ነግረውናል ¤ ድሮ ድሮ የመንግስት ሰራተኛው በወርሃዊ ቁጠባ ኮንዶሚኒየም ይደርሰው ነበር ¤ ድሮ ድሮ አርከበ እቁባይ የተባለ የብዙ የአዲስ አበባ ወጣቶችን ህይወት የቀየረ ከንቲባ ነበረ ¤ ድሮ ድሮ አበበ ተካ የሚባል ዘፋኝ የሆነች ቀሽት ዲያስፖራ አፍቀሮ "አለቅሳለሁ" የሚል ዘፈን አውጥቶ ሲያለቃቅስ ህዝቡ በጣም ስለተሰማው ገንዘብ ተሰብስቦ በአላሙዲን ድጋፍ አሜሪካ ሄዶ ልጅቷን እንዲያገኛት ተደርጓል ¤ ድሮ ድሮ ኃይሌ ገብረስላሴ 5 ኪሜ ውድድር ሲያሸንፍ ህዝቡ ከኮተቤ ፒያሳ ድረስ 10 ኪሜ እየሮጠ ደስታውን ይገልፅ ነበር ¤ ድሮ ድሮ ሰው ቤት ገብቶ መዘፍዘፊያ የሰረቀ ሌባ ፖሊስና ህብረተሰብ ቴሌቪዥን ላይ ቀርቦ ይወገዝ ነበር ¤ ድሮ ድሮ ከሰል ለማያያዝ አንድ ሌትር ጋዝ የሚጠቀሙ እናቶች ነበሩ ¤ ድሮ ድሮ ሀገሪቱ ውስጥ ከነበረው ህዝብ መካከል ስጋ በደንብ አያገኝም ተብሎ በፍለጋ የተገኘ አንድ አዛውንት አለቤ ሾው ላይ ቀርቦ ለ3 ዓመት ስጋ በነፃ እንዲወስድ ስሙን የረሳሁት ስጋ ቤት ቃል ገብቶላቸው ነበረ ¤ ድሮ ድሮ ተኽላይ ደምቢዶሎ ውስጥ አራርሳ ባህርዳር ላይ ሆቴል ነበራቸው ¤ ድሮ ድሮ ባለስልጣናትና አርቲስቶች የእግር ኳስ ግጥሚያ በህዝብ ፊት ያካሂዱ ነበር ¤ ድሮ ድሮ "ምግብማ ሞልቷል አምላክ መች ነሳኝ" የሚል ዘፈን ነበር ¤ ድሮ ድሮ ምግብ በተትረፈረፈበት ዘመን ከመመገባችን በፊት እጃችንን መታጠብ አንርሳ የሚል ተደጋጋሚ ማስታወቂያ ነበረ ¤ ድሮ ድሮ የ4ኛ ክፍል መምህር ካዛንቺስ ተከራይቶ ይኖር ነበር ¤ ድሮ ድሮ ማር ሲበዛ ይመራል የሚሉ ማር ያላቸው ወላጆች ነበሩን ¤ ድሮ ድሮ የቀበሌያችን ሊቀመንበር ልጆች አብረውን ደጃዝማች ወንድይራድ ት/ቤት ይማሩ ነበር ¤ ድሮ ድሮ መክሰስ የሚባል 10 ሰዓት ላይ የሚበላ ምግብ ነበረ @wegoch @wegoch @paappii By yihune ephrem 1.8K viewsPapi, 10:51