Get Mystery Box with random crypto!

ከቤት ስወጣ የሚያጋጥመኝ ሶስት አይነት ሰው ነው። ሙሉ በሙሉ የነቃ (ሞቲቬሽናል ስፒች ሚሰማ መሰለ | ወግ ብቻ

ከቤት ስወጣ የሚያጋጥመኝ ሶስት አይነት ሰው ነው። ሙሉ በሙሉ የነቃ (ሞቲቬሽናል ስፒች ሚሰማ መሰለኝ) ሙሉ በሙሉ ያልነቃ (ከምኔው ታክሲ ውስጠሰ ገብቼ ያቋረጥኩትን እንቅልፍ በቀጠልኩ የሚል) እና በከፊል የነቃ ሰው ይገኙበታል። በከፊል የነቃውን ኢዜማ ልትሉት ትችላላችሁ

ቅም አያቴ እስልምናን ከመቀበሉ በፊት መዳፍ ያነብ ነበር የሚል ታሪክ ሰምቻለሁ። እኔም የርሱ የልጅ ልጅ ልጅ ልጅ የሰው ፊት ማንበብ ቀኔን እጀምራለሁ።

ለታክሲ ከተሰለፉት ቁርሱን ቂንጬ የበላ ፣ ያደረ ሽሮ የበላና አሳር የበላን አብጠርጥሬ የመለየት ልዩ ተስጥኦ አለኝ። ከቤታቸው ፓንኬክ በልተው ሚወጡ ይኖሩ ይሆናል። የታክሲ ሰልፍ ላይ ግን አጋጥመውኝ አያውቁም።
ለአንድ ብጣሽ ቁርስ ወተት እንቁላል ዱቄት የሚያባክን ሰው ወይ መኪና አለው ወይ በራይድ ነው ሚንቀሳቀሰው። ድንገት ታክሲ ከተሰለፈ ይህንን ፅሁፍ እየፃፈ ነው

ጥሩ ቁርስ የጥሩ ቀን ማስጀመርያ ነው ይላል ኒቼ ኒቼ እንዲህ ያለ ነገር ይበል አይበል አላውቅም። ዮናስ ዘውዴ ይህንን ፖስት ካየው ግን ቀጣይ ብሔራዊ ቴአትር የሚዘጋጅ መድረክ ላይ ኒቼ እንዳለው ብሎ እንደሚጠቅሰው እርግጠኛ ነኝ

ሰው የሆዱን በዝምታ ቢሸሽግ ግንባሩን ግን በፍፁም መሸሸግ አይቻለውም። ለሊቱን አለሙን ሲቀጭ ያደረና በትራስ እጦት አንገቱ የተቀጨ መለየት ለኔ በጣም ቀላል ነው።
አንዲት ቆንጆ በአጠገባችን ስታልፍ ዞሮ ካላየ ወይ ባለቤቱ አጠገቡ አለች ወይም አንገቱ ተቀጭቷል። አለዚያ ሌላ ነገር እንድንጠረጥር እንገደዳለን።

መጠርጠር ስል ሰሞኑን ሀገር እንደሚበጠብጡ የተጠረጠሩ ሰዎች እየታሰሩ ነው ተብሏል። አሁንም ግን የዘራ በረሮ ሚሸጡ ሰዎችና ጌታ መጣልህ እያሉ ሚያስደነግጡን ሰዎች ከተማው ላይ በነፃነት እየተንቀሳቀሱ ነው።ከቴም ሰላም ማስከበር¡

ትላንት ስራ ውዬ በድካም ተርከም ተርከም እያልኩ አስፋልት ስሻገር በግብዳ ስፒከር "ጌታ እየመጣ ነው" ብሎ አንባረቁብኝ። በድንጋጤ መኪና ውስጥ ተወርውሬ ነበር። ጌታ ሳይመጣ እኔ ወደርሱ ሄጄ ነበር

የሆነው ሆኖ "ቡና ጠጥቶ ከቤት መውጣት የብልሆች መገለጫ ነው ይላል ኒቼ"

@wegoch
@wegoch
@paappii

By #Muaz jemal