Get Mystery Box with random crypto!

ሰው ሂያጅ ነው! የሰው ልጅ መሄድ የሚጀምረዉ ገና ከእናቱ ማህፀን ጀምሮ ነው። በእናቱ ማህፀን | ወግ ብቻ

ሰው ሂያጅ ነው!

የሰው ልጅ መሄድ የሚጀምረዉ ገና ከእናቱ ማህፀን ጀምሮ ነው። በእናቱ ማህፀን ሳለ  ከእንቁላልነት ወደ ትንሽ ፍሬነት ይቀየራል። ከዚያም ከ 9 ወራት ትግልና ፅናት በኃላ ሰው ሆኖ ይወለዳል። ነገር ግን በዚህ ብቻ አያበቃም በእግሩ ይጓዛል በእግሩ ሲሰላች እንስሳትን አዘጋጀ። በበቅሎ በአህያ ወዘተ ይጓዝ ጀመረ። ግን አልበቃውም።

ወቸ ጉድ ከዚህ በላይ ደሞ በምኑ ሊጓዝ ነው?

ገና ምኑ ተጀምሮ የሰው ልጅ ድንቅ ፍጥረት ነው። ብሎ ብሎ ባለ ሞተሩን መኪና ሰራና በመኪና ከሀገር ሀገር መጓዝ
ጀመረ። ግን አሁንም መድረስ የፈለገበት አልደረሰም።

እና የት ለመድረስ ቀጥሎ ምን ሰራ?

በቀጣይ ደግሞ ባቡርን ሰራ ረጅሙን ተሳቢ። በዚህም አላበቃም የሰው ልጅ ይህን በነካሁት ብሎ የሚመኘውን ሰማይ አውሮፕላን ሰርቶ  አጠገቡ እንደ ቀልድ ይንሳፈፍበት ጀመር። አየርን ለመተንፈስ ብቻ ስንጠቀምበት ድንቄ ሰው ግን አየርን ለመጓጓዛም ተጠቀመበት።

በቃው ይሄን ያህል ከሄደ  በአየር ሀገር ለሀገር ዞረ

ምን ይበቃዋል ጨረቃ ላይ ለመሄድ መንኩራኩርን አበጀ ከዚያም ፕላኔቶች ጋር ደረሰ።


ፈጠራውም ገና ይቀጥላል።
ሰው ራሱን እስኪያገኝ መሄዱን አያቆምም።

እራሱን ለማግኘት ደግሞ በሞተር ነገሮችን መስራት ሳይሆን ያለበት 'ራሱን በመስራት 'ራሱን መሆን ነው። ስለዚህም ራስህን ለማግኘት በቅድሚያ ራስህን ሁን። ከዚህ በኃላ "ሰው ሂያጅ ነው" የሚባለዉ ነገር አንተ ላይ ታሪክ ሆኖ ይቀራል ማለት ነው።
ለዚህም ነው አባቶቻችን ''እንቁላል ቀስ በቀስ በእግሩ ይሄዳል'' የሚሉት። ከእንቁላል ተነስቶ እስካሁን መሄድ ያላቆመዉ አጅሬ ሰው ግን ምነኛ ድንቅ ፍጥረት ነዉ?


የሰው ልጅ ሂያጅ ነው መሄጃውን የማያውቅ ከንቱ፣
ለፍተህ ጥረህ ግረህ ብላ ቢለው አባቱ፣
መዳረሻም የለው የመሄጃው ማብቂያ፣
ራሱን ሲያገኝ ነው የፍሬው መለኪያ።


አንተ  ግን  መሄድህን  መቼ  ታቆማለህ  /እስከየት  ትሄዳለህ...?  እኔ  እልሃለው  ምቾት  ሞልቶ  እስኪተርፍልህ    ሳይሆን  ራስህን  እስክታገኝ  ሂድ  ፡፡
          
         ተፃፈ በኢማን አብዲ(ረዱ)

       ጥቅምት 04,2015ዓ.ም
@redu_30

@getem
@getem
@getem