Get Mystery Box with random crypto!

በሰውየው ዙሪያ ከገንዘብ ነክ ነገሮች በተጨማሪ ብዙ ብልግናዎች እንደሚከወኑ ያወቅኩትም በጎን መቆም | ወግ ብቻ

በሰውየው ዙሪያ ከገንዘብ ነክ ነገሮች በተጨማሪ ብዙ ብልግናዎች እንደሚከወኑ ያወቅኩትም በጎን መቆም ስጀምር ነው። አዲስአበባ ሲመጣ ሳሎኑ መጂልሱ ላይ ተቀምጦ የከተማው እምቡጥ እምቡጥ የመሳሰሉ ሴቶች እየመጡ እንደሚታረድ በግ ሽንጥና ዳሌያቸውን እያገላበጠ ፈትሾ ይመርጥ እና የወደዳትን ለራሱ የተቀሩትን እቤቱ መጥተው አብረውት ሲቅሙ እና ሲያጨሱ ለሚቆዩት እንግዶቹ ልክ <ምን ይምጣላችሁ?> ብሎ እንደሚያቀርበው ምግቡ ያቀርባቸዋል። መጀመሪያ ቀን ነውርነቱ አሳፈረኝ። የሴቶቹ ምንም የማፈር ስሜት ፊታቸው ያለመኖር እኔን መሬት ተሰንጥቃ እንድትውጠኝ እስከመመኘት አሳፈረኝ። ሲቆይ ልምድ ነው አላልኳችሁም? ለመድኩት። ሴቶቹ አንዱ ባለሃብት ላይ አይኔ እያየ ለሁለት የማይኮን ሲሆኑ አይኔን ሳላርገበግብ መቆም ለመድኩበት። ከዛ በኋላ እይዘዋለሁ ብዬ የማላስበውን ያህል ገንዘብ እየኖረኝ መጣ። ከሰውየው ጋር በየሀገሩ መዞርም ለመድኩ። በዞርንበት በተለይ እግሊዝኛ የሚነገርበት ሀገር ስሄድ ያለመማሬ የምር አስቆጨኝ እና እንግሊዝኛ ለመማር እቤቴ አስተማሪ ቀጠርኩ። ከዓመት በኋላ እየተመላለሰ ሰውየው ካስተማረኝ እንግሊዝኛ በላይ በልምድ በዙሪያዬ እነርሱ የሚያወሩት አረብኛ ይገባኝ እና መናገር መሞከር ጀመርኩ።

የጎን ክንፍ አጃቢ ከሆንኩ ከዓመት በኋላ የሰውየው የቅርብ ጠባቂዎች በሙሉ ሰልጥነውት እኔ ያልሰለጠንኩት ስልጠና መኖሩ ተነግሮኝ የመን ለስልጠና ሄድኩ። በየጊዜው ለቀናት ከኪዳን መራቁን እየተላመድነው መጥተናል። እስከአሁንም ቦታው የግለሰብ ይሁን የመንግስት በማይገባኝ ካምፕ በመሰለ ቦታ ስልጠና ለ6 ወር ወሰድኩ። አብዛኛው ስልጠና የወታደር ስልጠና ምን እንደሚመስል ባላውቅም እንደዛ ዓይነት ይመስለኛል። በየቀኑ ፈሴ ጢጥ እስኪል ከብዙ ወንዶች እና በጣት ቁጥር ከማይሞሉ ሴቶች ጋር የሚሰጡኝን የቴክኒክ እና የጉልበት ስልጠናዎች መውሰድ ነበር። አንዳንዴ ደግሞ ለስለላ የሚያሰለጭኑኝ እስኪመስለኝ በሰዓቱ በስርዓቱ የማይገቡኝን የጭንቅላት ስልጠናዎች እና ፈተናዎች ወሰድኩ።

ከስድስት ወር በኋላ ስመለስ የሰውየው ቀኝ እጅ ከመሆኔ በተጨማሪ የሚከፈለኝ ደሞዝ በህልሜ እንኳን አስቤው የማላውቀው ነበር። በዛ ላይ ጭኔን የሚያሳዩትን ብጣቂ ሚኒዎች ያለመልበስ መብት ተሰጠኝ እና በምትኩ ሙሉ ሱፍ በሱሪ መልበስ ጀመርኩ። በገንዘቤ ሳይሆን በሰውየው ገንዘብ መኪና ተገዛልኝ እና የመኪና ባለቤት ሆንኩ። አንድ ቀን እስከዛ ቀን ድረስ ሲሄድ ያልገጠመኝ ቤት አጅቤው ሄድኩ (አሁን የእኔ የሆነው የራቁት ጭፈራ ቤት) ከፊት የሚታየውን የአዘቦት ጭፈራ ቤት የሚመስል በሙዚቃ አንድ ገበያ ህዝብ የሚውረገረግበትን አዳራሽ የሚያክል ሳሎን አልፈን ወደውስጥ በሚስጥር በር ዘለቅን። ኮሪደሩ ላይ የተቀበለን አስተናጋጅ ወደተዘጋ ክፍል ወሰደን። አራት የምንሆን ሴት ጠባቂዎቹ አጅበነው ስንቆም ክፍሉ ከእርሱ ውጪ ማንም አልነበረበትም። ተራ በተራ ሴቶቹ እየገቡ የቆመው ፖል ላይ ሲጥመለመሉ ሲያስቀይር ሌላ ስትመጣ ሲያስቀይር ሌላ ስትመጣ ቆይቶ ሁለቱን መረጠ እና ፓንት ለማለት የሚያስቸግር ክር ነገር ነገራቸው ላይ ጣል አድርገው፣ የጡታቸውን ጫፍ ብቻ የሚሸፍን ጨርቅ ጩታቸው ላይ አገልድመው ይቀነጣጠሱ ገቡ። ለምጄው የለ? እየቆየ የለበሱትን እንዲያወልቁለት አዘዘ እና ረብጣ ብር አስቀመጠ። እኛን ዞር ብለው ሳያዩ እርቃናቸውን ሆኑለት። ……

ከፖላቸው ወርደው አጓጉል ቦታ እየነካኩት ሰውየው ላይ መደነስ ጀመሩ!! እኔ ብቻ ስቀር ሌሎቹን ጠባቂዎቹን እንዲወጡ አድርጎ እንኳን በእውኔ በፊልም ባየው የሚያስመልሰኝ የሚመስለኝን ብልግና ሴቶቹን አስደረጋቸው። የዛን ቀን እየወጣሁ በሴቶቹ ፍርድ አይደለም የፈረድኩባቸው <እንዴት ያለ የማይታለፍ አበሳ ቢገጥማቸው ነው እንዲህ ራሳቸውን ለማዋረድ ግድ ያልሰጣቸው?> እያልኩ አሰብኩ። የሰውየውን ምናምን ባደረጉበት አፋቸው ምግብ ይበሉበታል? እላለሁ።

እዛ ቤት መመላለስ ያዘወትር ጀመር። አንድ ቀን ታዲያ ይገጥመኛል ብዬ በምንም አጋጣሚ ያላሰብኩት ሰው ገጠመኝ። አለቃዬን አጅቤ ከክፍሉ ስወጣ ሙሉሰው በጋርድ ታጅቦ ወደሌላ ክፍል ሲገባ አየሁት። ደንዝዤ ቆምኩ። ሰውየው እንኳን እስኪያስተውለኝ ተደነባበርኩ። እሱ አላየኝም። ምናልባት ቢያየኝም አያውቀኝም። እኔ ግን ደንግጬ እግሬ ከቆመበት አልንቀሳቀስ አለኝ!!

        ..........  አልጨረስንም  ........

@wegoch
@wegoch
@paappii