Get Mystery Box with random crypto!

ልጅ ስትወልድ ነው ቤተሰቦችህን የምታመሰግነው ከቤ :) ህፃናት ቤትህን ሲያምሱት ህወሀት ማረኝ ትላ | ወግ ብቻ

ልጅ ስትወልድ ነው ቤተሰቦችህን የምታመሰግነው ከቤ :)
ህፃናት ቤትህን ሲያምሱት ህወሀት ማረኝ ትላለህ። ለምሳሌ ልጅህ የቤትህን ቴሌቪዥን ኩባያ ወርውሮ ሊሰብርብህ ይችላል ። ነገ ወሳኝ ስብሰባ አለኝ ብለህ በክብር ያኖርከውን የሱፍ ጃኬት ባሊ ውስጥ ነክሮ ሲያንቦራጭቅ ልታገኘው ትችላለህ ። ውዷ ባለቤትህ ናፍቃህ እቅፍ አድርገሀት ጉያህ ከመክተትህ ቅናት ያንገበገበው ፈልፈላህ ስኒ ወርውሮ ግንባርህን ይገምስሀል በተለይ ወንድ ልጅ ራሱን የቻለ ወያኔ ነው። ልጄን ቅዱስ ብዬ ከምጠራው ጌታቸው ረዳ ብዬ ለምን አልሰየምኩትም የሚል ቁጭት አንገብግቦኝ ያውቃል። ሌላው ልጅ ስትወልድ የምትረዳው የሴቶችን አስማት ነው። ሴት ልጅ ምትሀተኛ ናት። ሚስትህ የውጭውን ስራ ሰርታ ቤት ተፍተፍ ብላ ልጅህን እንደፀባዩ ስትይዝልህ የሴት ልጅን ተፈጥሮ ታደንቃለህ። ብዙ ወንዶች በባህሪያችን ስልቹ ነን። 10 ደቂቃ ልጅህን አቅፈህ ተቀምጠህ ትግል ሲጀምርልህ ትማረራለህ። አንዳንዴ ረዥም ገመድ አዘጋጅቼ ከጠረጴዛ ግርጌ ልሰረው ወይ ልትል ትችላለህ ።
ቢሆንም...ቢሆንም...ወንድም መላ አለው። ልጄ ሲረብሽ ጊልዶና ሳንቾ ትዝ ይሉኛል። ጊልዶ የሚደብረኝን ያህል መርቄው አውቃለሁ። የጊልዶ ባዶ ...ባዶ ሙዚቃ ቅንብሮች ልጄን ያስጨፍሩታል። የኤልያስ መልካ አጥንት እየወቀሰኝ ሳንቾን እከፍትለታለሁ። ሙዚቃው እስኪፈፀም የሰላም አየር እምጋለሁ። ሙዚቃው ሲፈፀም Phase 2 ጦርነት በይፋ ቤቴ ውስጥ ይጀመራል። ህወሀት ማነው ቅዱሴ ያንሰራራል። የቤቱ ህገመንግስት ተጣሰ ይለኛል። ወልቃይት ....(ወይኔ ጨለልኩ በቃ !)... አንተ የተቀመጥክበት ቦታ የኔ ነው ብሎ ያንባርቃል። እየተንጫነጭኩ ቦታዬን አስረክባለሁ ።
ከልጅህ ጋር ትንሽ ከተጎራበጥክ ባለቤትህ በግልምጫ ታነሳሀለች። ያልሰከነ ቡና ልትቀሳልህ ትችላለች...እንደ ጣና ሀይቅ በቀጠነ ሽሮም ልትመታ ትችላለህ። This is life brother!
....ፈጣሪ ላያስችል አይሰጥም ብለህ ስትማረር ብትውልም የልጅህ አንገት ስር ገብተህ ስትስመው አመፁን ትረሳዋለህ። ሌላ ልጅ መድገም ሁሉ ያምርሀል። ህፃናት ገነትን በአንገታቸው ይዘው ይዞራሉ። በስራ እየጦዝክ በመሀል ልጅህ ይናፍቅሀል። ብጥብጡ.. .አመፁ...ረብሻውም ለካ አንድ መሳጭ የህይወት ሂደት ነው አባዬ ! እየከነፍክ ቤትህ ትገባለህ.. .የሶስተኛው ዙር ጦርነት መለከት ይነፋል :)

@getem
@getem
@paappii

#mikael aschenaki