Get Mystery Box with random crypto!

እየጾሙ አለመጾም ተወዳጆች ሆይ! እየጾሙ የጾምን ፍሬ ፃማ የማያገኙበት ሁኔታ እንዳለ ታውቁ ዘንድ | ውዳሴ ማርያም/wdasemaryam

እየጾሙ አለመጾም

ተወዳጆች ሆይ! እየጾሙ የጾምን ፍሬ ፃማ የማያገኙበት ሁኔታ እንዳለ ታውቁ ዘንድ እወዳለሁ፡፡ ይህስ እንደ ምን ነው ያላችሁኝ እንደሆነም፦

ከምግበ ሥጋ ተከልክለን ከምግበ ኃጢአት ያልተከለከልን እንደ ሆነ፣

ከጥሉላት ርቀን ነዳያንን ያልጎበኘን እንደ ሆነ፣
ወይን ከመጠጣት ታቅበን በክፉ መሻት ከመስከር ያልራቅን እንደ ሆነ፣

ጀምበር እስክትጠልቅ ድረስ ከእህል ከውኃ ርቀን በዓይናችን መልካም ያልሆኑ ትዕይንቶችን ከማየት ያልጦምን እንደሆነ ነው ብዬ በእውነት ያለ ሐሰት እመልስላችኋለሁ፡፡ ስለዚህ እየጾሙ እንዲህ አለመጾም እንዳለ ዕወቁ፤ ተረዱም፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

      ቅዱሳን እየጾሙ ካለመጾም እመብርሀን ትሰውረን!

ይህንን መልዕክት ለወዳጅ ዘመድው ያጋሩ
@wdasemaryam
@wdasemaryam
@wdasemaryam