Get Mystery Box with random crypto!

'ፈተና ሲገጥመን ውስጣችን ሊረበሽ ወይም በቀቢጸ ተስፋ ሊያዝ አይገባውም፡፡ ወርቅን የሚያነጥር ሰው | ውዳሴ ማርያም/wdasemaryam

"ፈተና ሲገጥመን ውስጣችን ሊረበሽ ወይም በቀቢጸ ተስፋ ሊያዝ አይገባውም፡፡ ወርቅን የሚያነጥር ሰው በእሳት ውስጥ የጨመራትን የወርቅ ቅንጣት እዚያ ውስጥ ምን ያህል ጊዜ መቆየት እንዳለባት ያውቃል፤ መቼ ከእሳቱ ሊያወጣት እንደሚገባውም ያውቃል፡፡

እንዲሁ እስከ መጨረሻው በእሳቱ ውስጥ ተጥላ እንድትቀርና በዚያ እንድትቃጠል አይፈቅድም፡፡ እግዚአብሔር ደግሞ ይህን ከወርቅ አንጣሪው በላይ ያውቃል፡፡ መቼ ከርኩሰታችን እንደምንነጻ ያውቃል፡፡ በመኾኑም ራሳችንን በመጣልና ተስፋ በመቁረጥ በክፋት ላይ ክፋት እየጨመርን እንዳንኼድ ሽቶ መቼ ከዚያ ፈተና እንደሚያወጣን ያውቃል፡፡

ስለዚህ ድንገት ያላሰብነው ነገር ቢገጥመን በፍጹም የምናማርር፣ ወይም ተስፋ የምንቆርጥ ልንኾን አይገባንም፡፡ ከዚህ ይልቅ የእነዚህ ነገሮች ምንነትን የሚያውቅ እግዚአብሔርን መጠበቅ፣ እርሱ እስከ ፈቀደው ጊዜ ድረስም ልቡናችንን በእሳት እንዲፈተን ማድረግ ይገባናል፡፡ ምክንያቱም ይህ ነገር በእኛ ላይ እንዲኾን (እንዲመጣ) የፈቀደው ለእኛ ጥቅምና በዚያ ውስጥ ኾነን በምናሳየው ጥረት ይበልጥ ሊያከብረን ስለሚወድ ነው፡፡"

(#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
ምንጭ፡- ከቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ


ሼር ሼር ሼር ሼር
   

@wdasemaryam
@wdasemaryam
@wdasemaryam