Get Mystery Box with random crypto!

#ሚካኤል በዙፋኑ ፊት የሚቆመው ክብርና ስልጣን የተሰጠው ሊረዳኝ መጣ ሚካኤል የአምላክ አገልጋ | ውዳሴ ማርያም/wdasemaryam

#ሚካኤል

በዙፋኑ ፊት የሚቆመው
ክብርና ስልጣን የተሰጠው
ሊረዳኝ መጣ ሚካኤል
የአምላክ አገልጋይ ባለሟል(2)

ከላይ ከሰማይ ከራማው መንደር
አለኝ ቃልኪዳን ዘመን ሚሻገር
በስሙ ውሀን እያጠጣሁኝ
ስንቱን መከራ ስንቱን አለፍኩኝ
ብላቴናነት አይገድበኝም
የንጉስ ቁጣ አያስፈራኝም
በጉባኤ ፌት መዝገብ ገልጬ
ስለ ሚካኤል ላውራ አብልጬ
#አዝ
መዳን ሆነለት ጎጆዬ ዛሬ
ታላቅነቱን በመመስከሬ
ነገን እንዳልፈው መሰናክሉን
ሚካኤል  ይቅደም ዘርግቶ ክንፉን
ይሔ ዝማሬ ይሔ ምስጋና
ለረዳኝ መልዐክ ይገባልና
ድምፄን አውጥቼ መሰክራለሁ
ቅዱስ ሚካኤል ለኔ ልዩ ነው
#አዝ
ስምህ ይቅደመኝ ጠዋት ስወጣ
ምልጃህ ይታደገኝ እንዳልቀጣ
ነብሴ እድሏ በቀኝ መቆም ነው
ቅዱስ ሚካኤል አማላጁዋ ነው
ይሔ ዝማሬ ይሔ ምስጋና
ለረዳኝ መልዐክ ይገባልና
ድምፄን አውጥቼ መሰክራለሁ
ቅዱስ ሚካኤል ለኔ ልዩ ነው

        ዘማሪ አብርሃም ተገኔ
   

ሼር ሼር ሼር ሼር
   

@wdasemaryam
@wdasemaryam
@wdasemaryam