Get Mystery Box with random crypto!

✟✟  መንፈሳዊ ኃይል ✟✟ ሰው በእግዚአብሔር መንፈስ ሲቃኝ አቅም ይጨመርለታል፡፡ መንፈሳዊ ኃ | ውዳሴ ማርያም/wdasemaryam

✟✟  መንፈሳዊ ኃይል ✟✟

ሰው በእግዚአብሔር መንፈስ ሲቃኝ አቅም ይጨመርለታል፡፡ መንፈሳዊ ኃይል ይታጠቃል/ገንዘብ ያደርጋል/፡፡መንፈሳዊ ኃይል የራቀው ግን በቀላሉ የሚረታ፣በፍርሀት የሚርድ፣የሚያየው የሚሰማው የሚያስፈራው እና የሚያውከው ይሆናል፡፡ መንፈስ_ቅዱስ ከራቀው ሞቱ፣ በሽታው፣ ኑሮው ያስፈራዋል፡፡

እግዚአብሔር ሲያድርብን እንጨክናለን፣ እንጠነክራለን፡፡
ጾም፣ ጸሎት፣ ምጽዋት፣ ትሩፋት፣ ቃለ እግዚአብሔር ፣ ቅዱስ ሥጋው እና ክቡር ደሙ ኃይለ_እግዚአብሔርን ገንዘብ ማድረጊያ ናቸው፡፡

ሥጋውና ደሙ ፡መዝ. 103፡15 እክል ያጸንዕ ኃይለ ሰብእ=እኽል የሰውን ኃይል ያጸናል፡፡ እኽል እንደሚያበረታ ቅዱስ ሥጋውም ነፍስን ያበረታል፡፡ጽንዐ ሥጋ ጽንዐ ነፍስ ነውና፡፡ ኃይል መንፈሳዊ የሚሆን ሥራ የሚያሠራ ይህ ቅዱስ ሥጋውና ክቡር ደሙ ነው፡፡

ብርቱዎቹ አባላት ለራሳቸው ይተጋሉ፤በቀረው አትርሱኝ እያሉ አባቶችን እያሳሰቡ መንፈሳዊውን ውጊያ በመንፈሳዊው ኃይል ይፋለማሉ፡፡


እግዚአብሔር ያበርታን

@wdasemaryam
@wdasemaryam
@wdasemaryam