Get Mystery Box with random crypto!

የቡድን-7 አገራት ውጭ ጉዳይ ሚንስትሮች፣ በኢትዮጵያ የሰፈነው ውጥረትና ኢትዮጵያ ከሱማሌላንድ ጋር | Wasu Mohammed(ዋሱ መሀመድ)

የቡድን-7 አገራት ውጭ ጉዳይ ሚንስትሮች፣ በኢትዮጵያ የሰፈነው ውጥረትና ኢትዮጵያ ከሱማሌላንድ ጋር የተፈራረመችው የባሕር በር መግቢያ ስምምነት እንደሚያሳስባቸው ትናንት ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

አገራቱ፣ ኢትዮጵያ እና ሱማሊያ "ኹሉንም የንግግር መስመሮች" ክፍት በማድረግ ውጥረቶችን እንዲያደርግቡ ጠይቀዋል።

በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች፣ የኢኮኖሚ ቀውስና የምግብ ዋስትና ማሽቆልቆል አሳሳቢ እንደኾኑም አገራቱ ገልጸዋል።

የቡድኑ አባል አገራት፣ የመንግሥት የሰብዓዊ መብቶች ጥበቃ ዘላቂ እንዲኾን፣ ሲቪሎችን ከጥቃት እንዲጠበቁ፣ ውጥረቶች በፖለቲካዊ ንግግር እንዲፈቱ፣ እርቅ፣ የሽግግር ፍትህና ተጠያቂነት እንዲሰፍን ጥሪ አድርገዋል።

በተያያዘ ዜና የቡድን-7 አገራት፣ ሱማሊያና ኢትዮጵያ በባሕር በር መግቢያ ዙሪያ የገቡበትን ውጥረት ለመፍታት "ኹሉንም የንግግር መስመሮች ክፍት እንዲያደርጉ" ላቀረቡት ጥሪ፣ የሱማሊያ መንግሥት ትናንት እኩለ ሌሊት ላይ ባወጣው መግለጫ አሉታዊ ምላሽ ሰጥቷል።

የሶማሊያ መንግሥት፣ ኢትዮጵያ ከሰሜናዊቷ ግዛቴ ሶማሊላንድ ጋር የደረሰችበትን የባሕር በር መግቢያ የመግባቢያ ስምምነት እስካልሰረዘችና የሱማሊያን አንድነት፣ ሉዓላዊነትና በውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ያለመግባት መርህ ሙሉ በሙሉ እስካላረጋገጠች ድረስ፣ ንግግር ማድረግ የሚሳካ ነገር አይደለም ብሏል።(Wazema)
==================
ቤተሰብ በቅንነት ሰብስክራይብ በማድረግ ተባበሩ       
https://www.youtube.com/channel/UCrdWHrcXNEhMfbp1ucgxd1g
አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ Join አድርገው በዚህ ይከታተሉ
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
ማስታወቂያና ጥቆማ መቀበያ
https://t.me/wasumohammed