Get Mystery Box with random crypto!

ባንኩ ሌላ ማሳሰቢያ አወጣ ያለአግባብ የራሳችሁ ያለሆነን ገንዘብ ከባንኩ ወስዳችሁ ወደ ቤቲንግ | Wasu Mohammed(ዋሱ መሀመድ)

ባንኩ ሌላ ማሳሰቢያ አወጣ

ያለአግባብ የራሳችሁ ያለሆነን ገንዘብ ከባንኩ ወስዳችሁ ወደ ቤቲንግ ተቋማት ገንዘቡን ያዘዋወራችሁ አቅራቢያችሁ በሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ በመገኘት ለዚሁ የተዘጋጀውን ቅጽ በመሙላት እንድታመለክቱ ባንኩ አሳስቧል።

ባንኩ መጋቢት 7 ቀን 2016 ባጋጠመው የሲስተም ችግር ምክንያት ያለአግባብ የገንዘብ ልውውጥ እንደነበር ይታወቃል።

በዚህም በርካታ ግለሰቦች በጥሬ ገንዘብና በዲጂታል የክፍያ አማራጮች የወሰዱትን የገንዘብ እየመለሱ ይገኛሉ።ሆኖም አንዳንድ ግለሰቦች የወሰዱትን ገንዘብ ወደ ቤቲንግ ተቋማት በማዛወራቸው መመለስ እንደተቸገሩ ገልጸዋል።

በመሆኑም ገንዘቡን ተመላሽ ለማድረግ እንዲቻል ወደ ቤቲንግ ተቋማት የራሳችሁ ያልሆነውን ገንዘብ ያዘዋወራችሁ አቅራቢያችሁ በሚገኝ የባንክ ቅርንጫፍ በመገኘት ለዚሁ የተዘጋጀውን ቅጽ በመሙላት እንድታመለክቱ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጥሪ አቅርበዋል።
ቤተሰብ በቅንነት ሰብስክራይብ በማድረግ ተባበሩ       
https://www.youtube.com/channel/UCrdWHrcXNEhMfbp1ucgxd1g
አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ Join አድርገው በዚህ ይከታተሉ
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
ማስታወቂያና ጥቆማ መቀበያ
https://t.me/wasumohammed