Get Mystery Box with random crypto!

ዛሬ መጋቢት 14/2016 ማለዳ በእንጦጦ ጋራ ስር የመሬት መንቀጥቀጥ አጋጥሞ ነበር ተባለ። ከጥ | Wasu Mohammed(ዋሱ መሀመድ)

ዛሬ መጋቢት 14/2016 ማለዳ በእንጦጦ ጋራ ስር የመሬት መንቀጥቀጥ አጋጥሞ ነበር ተባለ።

ከጥዋቱ 1 ሰዓት ከ45 ደቂቃ 25 ሰኮንድ የቆየ የመሬት መንቀጥቀጥ በእንጦጦ ጋራ ስር ማጋጠሙን ሰምተናል።

የመሬት መንቀጥቀጡ በርዕደ መርት መለኪያ(በሬክትር ልኬት )2.0 ሆኖ መመዝገቡን በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የስፔስ ሳይንስ እና አስትሮኖሚ ተቋም ሀላፊ ፕሮፈሰር አታላይ አየለ ለሸገር ነግረዋል።

ይህ የመሬት መንቀጥቀጥ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ እና ፉሪ ተራራ ሥር በሚገኙ መሣሪያዎች የተመዘገበ መሆኑ ተነግሯል።

የመሬት መንቀጥቀጡ የተፈጠረው 9.1113 ኬክሮስና 38.753 ኬንትሮስ መስመሮች በሚገናኙበት ነጥብ ላይ ያረፈ ሲሆን ይህም በእንጦጦ ጋር ስር መሆኑን ማወቅ ተችሏል ተብሏል።

በሰሜን አዲስ አበባ በተለይም ፎቅ ላይ ያሉ ነዋሪዎች ንዝረቱን መስማታቸውን አስረድተዋል።

የመሬት መንቀጥቀጡ ጉዳት የማድረስ አቅሙ በጣም ዝቅተኛ መሆኑንም ፕሮፈሰር አታላይ ነግረውናል ሲል ሸገር ኤፍ ኤም 102·1ዘግቧል።
ቤተሰብ በቅንነት ሰብስክራይብ በማድረግ ተባበሩ       
https://www.youtube.com/channel/UCrdWHrcXNEhMfbp1ucgxd1g
አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ Join አድርገው በዚህ ይከታተሉ
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
ማስታወቂያና ጥቆማ መቀበያ
https://t.me/wasumohammed