Get Mystery Box with random crypto!

ዛሬ በአዲስ አበባ በዳግማዊ አጼ ምኒሊክ አደባባይ የተከናወነውን የታላቁ አድዋ ድል አከባበር 'ለመ | Wasu Mohammed-ዋሱ መሀመድ

ዛሬ በአዲስ አበባ በዳግማዊ አጼ ምኒሊክ አደባባይ የተከናወነውን የታላቁ አድዋ ድል አከባበር "ለመረበሽ የፈለጉ አካላት ሁከት ለመቀስቀስ ሞክረው ነበር" ሲል ማምሻውን የመንግስት ኮምንኬሽን ጽሕፈት አስታውቋል።ጸጥታ ኃይሎች ድርጊቱን ለመከላከል ሲሞክሩ "በጥቂት ምዕመናን ላይ ጉዳት ደርሷል"በማለትም ሂደቱን ገልፆታል።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በበኩሉ"…ታቦታተ ሕጉ ከመንበረ ክብራቸው  ወጥተው የዑደት ሥነ ሥርዓት ከተፈጸመ በኋላ ክብረ በዓሉ እየተከናወነ ባለበት ወቅት ከመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ወደ ቅጽረ ቤተ ክርስቲያኑ በተወረወረ አስለቃሽ ጭስ የበዓሉ ሥነ-ሥርዓት ሳይጠነቀቅ ታቦታተ ሕጉ ወደ መንበረ ክብራቸው ተመልሰዋል።ወደቅጽረ ቤተክርስቲያኑ በሚያስገቡ ሁለቱም መግቢያ በሮች በተወረወረው አስለቃሽ ጭስ በርካታ ምዕመናን በመጎዳታቸው ራሳቸውን ስተው ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል።>> በማለት ገልፀዋል።
====≡=============≡=====
ፈጣንና ወቅታዊ መረጃዎችን ያለገደብ ለማግኘት ፈጥነው ከታች ያለውን የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ፣ አንብበው ሲጨርሱ ለሌሎች ሼር ያድርጉ መረጃ ህይወት ነው።

http://t.me/wassulife
http://t.me/wassulife