Get Mystery Box with random crypto!

የማስታወስ ችሎታን የሚጨምሩ ምግቦች በቫይታሚን የበለጸጉ ምግቦችን የየእለት ማዕዳችን አካል ማድረ | Wasu Mohammed-ዋሱ መሀመድ

የማስታወስ ችሎታን የሚጨምሩ ምግቦች

በቫይታሚን የበለጸጉ ምግቦችን የየእለት ማዕዳችን አካል ማድረግና አትክልትና ፍራፍሪዎችን ማዘውተር ለአዕምሮ ጤና ወሳኝ ድርሻ አለው ተብሏል
አዕምሯችን ለማሰብና ለማንሰላሰል ከፍተኛ ሃይል ይጠቀማል።
በየቀኑ ከምናቃጥለው ካሎሪ 20 በመቶውን አዕምሯችን እንደሚጠቀም ጥናቶች ያሳያሉ።
ማንኛውም አይነት ምግብ ግን ለአዕምሯችን ጤናም ሆነ ለማስታወስ ችሎታችን ይረዳል ማለት እንዳልሆነም ነው ጥናቶች የሚጥቁሙት።
በንጥረ ነገር የበለጸጉ ምግቦችን መውሰድ ብቻም አዕምሯችን ደስተኛና ጤናማ እንደማያደርገው ይነገራል።
አትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም አሳ የሚያዘወትሩ ሰዎች የጤናማ አዕምሮ ባለቤት መሆናቸው ተረጋግጧል።

እነዚህ ምግቦች የደም ግፊትን ስለሚቆጣጠሩ ከእድሜ ጋር ተያይዞ የሚገጥሙ የመርሳት ችግሮችን ለማስውአገድ እንደሚያግዙም ነው የሚነገረው።
ከዚህ በታች የተዘረዝሩት ምግቦችም የአዕምሮን ጤና በማስተካከል የመርሳት በሽታን ለመከላከል ወሳኝ ድርሻ እንዳላቸው ጥናቶች አመላክተዋል።

1. ጎመን

አረንጓዴ ቅጠል ያላቸው አትክልቶች በቫይታሚን ኬ፣ ፎሊክ አሲድ፣ ቤታ ካሮቲን የበለጸጉ ናቸው። እናም እንደ ጎመን ያሉ አትክልቶች ከገበታ አለመጥፋት ለአዕምሮ ጤና ወሳኝ ነው ተብሏል።
 
2. ለውዝ

ለውዝ ወይም ኦቾሎኒ በፕሮቲን እና ጤናማ ስብ የበለጸገ መሆኑ ለአዕምሮ ምግብነት ተመራጭ ያደርገዋል። የኦሜጋ 3 ክምችቱም ከፍተኛ መሆኑ የመርሳት ችግርን ለመቀነስ አይነተኛ ሚና እንዲጫወት ያደርገዋል።

3. ቲማቲም

በቲማቲም ውስጥ በብዛት የምናገኘው ላይኮፒን ንጥረነገር እንደ አልዛይመር ያሉ የአዕምሮ ጤና ችግሮችን ለማስወገድ ትልቅ ድርሻ አለው። በአንድ መጠነኛ ቲማቲም ውስጥ 3 ነጥብ 2 ግራም ላይኮፒን እንደሚገኝ ጥናቶች ያሳያሉ።

4. የብዕርና አገዳ ሰብሎች

እንደ ስንዴ፣ ገብስ እና ሩዝ ያሉ ሰብሎች በቫይታሚን ኢ የዳበሩ ናቸው። እነዚህን ሰብሎች በፋብሪካ አቀነባብሮ ከመጠቀም ይልቅ ተፈጥሯዊ ይዘታቸውን ሳይለቁ ጥቅም ላይ ማዋል ለአዕምሮ ጤና ወሳኝ ድርሽ ኣእንዳለው ጥናቶች አመላክተዋል። በቀን ውስጥ 48 ግራም ቫይታሚን ኢ ለማግኘትም የማዕዳችን አካል ልናደርጋቸው ይገባል ተብሏል።

5. ብሮኮሊ(የአበባ ጎመን)

ብሮኮሊ በቫይታሚኖች ከመበልጸጉ ባሻገር የካሎሪ መጠኑ ዝቅተኛ ነው። በብሮኮሊ በከፍተኛ መጠን የምናገኘው ግሉኮሲኖላትስ ከውሃ ጋር ሲዋሃድ የሚፈጥረው አይዞቲዮካያንትስ የምግብ ውህደትን በማፋጠን የአዕምሮ ጤናም እንዲጠበቅ ያግዛል።

6. አሳ

በኦሜጋ 3 የበለጸገው አሳ በርካታ የጤና በረከቶች አሉት። በደም ውስጥ የሚገኘውና ለመርሳት በሽታ የሚዳርገው ቤታ አምሎይድ የተሰኘ ፕሮቲን መጠን እንዲቀንስም አሳ መመገብ አይነተኛ ድርሻ አለው ተብሏል። 

7. ቤሪ (ሰማያዊ እንጆሪ፣ አፕል)

በቀን አንድ አፕል መመገብ ዶክተር ለምኔ ያስብላል፤ ቤሪዎችን ማዘውተርም የአዕምሮ ሃኪምን ከመጎብኘት ይታደጋል ነው የሚሉት ጥናቶች። በፍላቮኖይድስ የበለጸጉ ቤሪዎች አዕምሯችን በሚገባ ስራውን እንዲያከናውን የሚያስችሉ ንጥረነገሮችን አከማችተው ይዘዋል። የማስታወስ ችግር እየገጠማቸው የሚገኙ ሰዎች ቢጠቀሟቸው ፈጣን ለውጥ ማየት ይችላሉ ነው የተባለው።

8. ጥቁር ቼኮሌት

ጥቁር ቼኮሌት የያዛቸው የካፌይን፣ ፍላቮኖይድስ እና አንቲኦክሲዳንትስ ለአዕምሮ ጤና ተመራጩ ምግብ ያደርገዋል። ከፍተኛውን የጥቁር ቼኮሌት በረከት ለማግኘትና የስኳር ፍጆታን ለመቀነስ ግን ቀለሙ ከ70 በመቶ በላይ ጥቁር መሆኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋል።

9. እንቁላል

በቫይታሚን ቢ6፣ ቢ12 እና ቢ 9 የዳበረው እንቁላል በፕሮቲን ከመበልጸጉም ባሻገር ለአዕምሮ ጤና ወሳኝ ድርሻ ያላቸውን ንጥረ ነገሮች ይዟል። ጥናቶችም እንቁላልን መመገብ የማስታወስ ችሎታን ለመጨመር እንደሚያግዝ አረጋግጠዋል።

10. እርድ

እርድ ለአዕምሮ ጤና ትልቅ ድርሻ እንዳለው በጥናት የተረጋገጠለትን ከርኩሚን የተሰኘ ንጥረነገር በስፋት ይዟል። ከርኩሚን የአዕምሮ ህዋሳት እድገትን በማፋጠን የመርሳት በሽታ (አልዛይመርን) ለመከላከል ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው ተብሏል።
====≡=============≡=====
ፈጣንና ወቅታዊ መረጃዎችን ያለገደብ ለማግኘት ፈጥነው ከታች ያለውን የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ፣ አንብበው ሲጨርሱ ለሌሎች ሼር ያድርጉ መረጃ ህይወት ነው።

http://t.me/wassulife
http://t.me/wassulife