Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮጵያ ለምትኖሩ ደንበኞቻችን አንድ አመት ሙሉ ያለምንም 'አገልግሎት ክፍያ' (Service Cha | Wasa Electronics

ኢትዮጵያ ለምትኖሩ ደንበኞቻችን አንድ አመት ሙሉ ያለምንም "አገልግሎት ክፍያ" (Service Charge) ስናገለግላችሁ እንደቆየን ይታወቃል : ይህም ማለት ደውላችሁ ቀጠሮ አስይዛችሁ ባለሙያዎችን ልከንላችሁ በተለያየ ምክንያት እቃው ሳይሰራ ቢቀር #ለምሳሌ እቃ ቅያሬ የሚያስፈልገው ከሆነና ደንበኛው ራሴ እገዛለሁ ካለ ወይም አሁን እቃ ለመግዛት ዝግጁ አይደለሁም ካለ ፣ እቃው ሊሰራ የማይችልበት ሁኔታ ላይ ከሆነ ወዘተ ••• ምንም ክፍያ ሳንጠይቅ ያለፈውን አንድ አመት አገልግለናችኋል ::

በሀገራችን ኢትዮጵያ ባይለመድም በውጪው ሀገር የአገልግሎት ክፍያ ማለትም ባለሙያ መጥቶ ላየበት ብቻ የሚከፈል ክፍያ የተለመደ ነው : በሀገራችን ኢትዮጵያም ከሐምሌ ወር ጀምረን 100 (መቶ ብር) Service Charge የጀመርን መሆኑን እንገልፃለን

ማሳሰቢያ :- አሜሪካን ሀገር የምትኖሩ ደምበኞቻችን በፊት እንደነበረው Service Charge $75 የሚቀጥል መሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን ::