Get Mystery Box with random crypto!

ለምሳሌ አንድ ሰው የቢትኮይን ተጠቃሚ ሲሆን ልክ እንደ ጂ-ሜል እና ፌስ ቡክ የመለያ ስም አውጥቶ | Wasa Electronics

ለምሳሌ አንድ ሰው የቢትኮይን ተጠቃሚ ሲሆን ልክ እንደ ጂ-ሜል እና ፌስ ቡክ የመለያ ስም አውጥቶ የሚስጥር ቁልፍ መርጦ መጠቀሚያ ይከፍታል፡፡ የሚስጥር ቁጥሩ በጣም ጠንካራ በመሆኑ የመሰረቅ አደጋ አይገጥመውም፡፡ ከዚያ ከፈለገው ሰው ጋር ቢትኮይን መላላክ ይችላል፡፡ ያ የተላላከው የገንዘብ ዝውውር በአለም ላይ ባሉ ኮምፒውተሮች ቅጂው ይቀመጣል፡፡ እነዚህ ሁለት ሰዎች ቢከዳዱ እንኳ አለም ላይ ባሉ ኮምፒውተሮች ዝውውሩ ተመዝግቦ በቅጂ መልክ ስለሚቀመጥ እውነቱን ማወቅ ይቻላል፡፡

በቀላል ምሳሌ እንየው፡፡ ለምሳሌ አንድ ሰው ጫማ መግዛት ቢፈልግ እና ባንክ ቤት ገንዘብ ለማውጣት ቢሄድ ባንክ ቤቱ ሰውየው በስሙ ገንዘብ መኖርና አለመኖሩን አረጋግጦ ገንዘብ ይሰጠዋል፡፡ ሰውየው ገንዘብ እንዳለውና እንደሌለው የሚያውቀው ባንኩ ብቻ ነው፡፡ እሱን ካረጋገጠ በኋላ ገንዘቡን ይሰጠውና የሚፈልገውን መግዛት ይችላል፡፡

ሰውየው በክፍያ ካርድ ቢሆን መግዛት የሚፈልገው እና ካርዱን ለባለሱቁ ሰጥቶ የጫማ መግዣውን ቢያስቆርጥ፤ ሰውየው ገንዘብ እንዳለውና እንደሌለው የሚቆጣጠረው በተመሳሳይ ሶስተኛ ወገን የሆነው ባንኩ ነው፡፡

ወደ ቢትኮይን ሰንመጣ የቢትኮይን መጠቀሚያ ያለው ሰው እቃ ገዝቶ የመገበያያ ገንዘብ ወይም ቢትኮይን እንዳለውና እንደሌለው የሚቆጣጠሩት አለም ላይ ያሉ ሰዎች ናቸው፡፡ ቢትኮይን የሚተላለፍለት ሰው ቢትኮይን አለው ወይ ብሎ ሲጠይቅ አለም ላይ ያሉ ኮምፒውተሮች በቂ ቢትኮይን ካለው ‹‹አዎ›› ከሌለው ደግሞ ‹‹የለውም›› ብለው ማረጋገጫ ይሰጡታል፡፡ ክፍያው ከተፈፀመ በኋላ ደግሞ ቅጂው በመላው አለም ላይ ባሉ ኮምፒውተሮች ተሰራጭቶ ይቀመጣል፡፡

ክፍያው ሲፈፀም ግልባጩ አልያም ቅጂው በዓለም ላይ ባሉ ኮምፒውተሮች የሚቀመጠው በሚስጥራዊ ስም ነው፡፡ እንጂ በተገልጋዩ የመጠሪያ ስም አይደለም፡፡ ከመጀመሪያው የቢትኮይን መጠቀሚያ ሲከፈት ሚስጥራዊ ኮድ አብሮ ይፀድቃል፡፡ ያ ምስጢራዊ መጠቀሚያ ማንም የማይከፍተውና ሊያጭበረብረው የሚችል አይደለም፡፡ የመገበያያ ገንዘቡ ለዚያ ነው ረቂቅ አንዳንዶችም ምናባዊ የሚሉት፡፡

ምንዛሬውስ?

ከእነዚህ ዲጂታል ገንዘቦች ውስጥ ቢትኮይን ከፍተኛ ዋጋ ያለው የብሎክ ቼይን ቴክኖሎጂ ነው፡፡ ቢትኮይን በፈረንጆች 2008 ሳቶሺ ናከሞሮ በተባለ ሰው የተፈጠረ ምናባዊ የመገበያያ ገንዘብ ነው፡፡ ይህ አዲስ ዋጋ ያለው ገንዘብ አለም አሁን እየተጠቀመባቸው ካሉ ገንዘቦች ሁሉ በምንዛሬ ከፍተኛ ዋጋ ያለው ረቂቅ ገንዘብ ነው፡፡ የቢትኮይን ዋጋ በየጊዜው ይጨምራል፡፡ የተወሰነ መዋዠቅም ያጋጥመዋል፡፡ ለምሳሌ ግንቦት 2010 ላይ የ1 ቢትኮይን ዋጋ 0.01 ዶላር ነበር፡፡ ታህሳስ 2017 የ1 ቢትኮይን ዋጋ 19ሺ783 ዶላር ደረሰ፡፡ የካቲት 2021 ላይ አንድ ቢትኮይን 60ሺ ዶላር ገብቶ ነበር። ዛሬ ሰኔ 25/ 2014 አንድ ቢትኮይን 19,262.40 ዶላር ነው።

የቢትኮይን ገንዘብ ከፍተኛ ዋጋ አውጥቶ የነበረው እነ ቴስላ በቢትኮይን ላይ ከፍተና ገንዘብ በማፍሰሳቸው ነበር። ባለሃብቶች ቢትኮይንን መግዛት ሲጀምሩ እና የተለያዩ ተቋማት ግብይት በዚህ ዲጂታል ገንዘብ መፈፀም ሲጀምሩ ዋጋው እየጨመረ ይሄዳል።

የብሎክቼን አልሚዎች፡-

የብሎክቼን አልሚዎች (Blockchain miners) በጥብቅ ሰንሰለት ቴክኖሎጂ ውስጥ የሚዘዋወሩ የዲጂታል ገንዘቦችን ዝውውር የሚቆጣጠሩ እና የሚያዘምኑ ናቸው። በዓለም ላይ ባሉ ኮምፒውተሮች ውስጥ የተመዘገቡ መረጃዎች እና የተዘዋወሩ የዲጂታል ገንዘቦችን ትክክለኛነት የሚያረጋግጡ ናቸው። ይህ ስራ በግል እና በቡድን ሊሰራ ይችላል። ብሎክቼንን በማስተዳደር ረገድ ግን ዓለም ላይ ያሉ ሰዎች ሁሉ መብት አላቸው። ዝውውሩን ለማረጋገጥ ደግሞ ከፍተኛ አቅም ያለው ኮምፒውትር ያላቸው ማይነሮች ይሳተፋሉ።

የዲጂታል ገንዘብ የሚነሳበት ተቃውሞ፡-

የዲጂታል ገንዘብ መንግስታት/ባንኮች/ ቁጥጥር ሰለማያደርጉበት ወንጀልን ሊያስፋፋ ይችላል ተብሎ ይሰጋል። ችግር ተፈጥሮ መንግስታት የገንዘብ ዝውውር እገዳ ለመጣል ቢፈልጉ ይህ አስቸጋሪ ይሆንባቸዋል፡፡ ነገር ግን ለሌሎች ዘርፎች የብሎክ ቼይን ቴክኖሎጂ ትልቅ ጠቀሜታ አለው።

አሜሪካ፤ ካናዳ፤ ፊንላንድና ቤልጂየም በተለያየ መልኩ ቢትኮይንን የተቀበሉት ሲሆን ቻይና፤ ሩስያ፤ ቬትናምና ቦሊቪያ ደግሞ እገዳ የጣሉ ሀገራት ናቸው፡፡ ነገር ግን የሀገራት አቋም በተለያዩ ምክንያቶች የሚቀያየርበት ጊዜ አለ።

Prevቀዳሚየኤኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ተቋማት የትምህርት ስርዓትንና የሥራ ፈጠራን በቴክኖሎጂ ለመደገፍ የሚያስችል ስምምነት አደረጉ።

አድራሻ :- ከቦሌ መድኃኔዓለም ወደ ሃያ ሁለት በሚወስደው መንገድ ላይ ከአደይ አበባ ስታዲየም ከፍ ብሎ ወርቁ ህንፃ ፊት ለፊት አበጋዝ ሆቴል አንደኛ ፎቅ

𝟬𝟵 𝟬𝟯 𝟳𝟲 𝟬𝟬 𝟳𝟲 ወይም 𝟬𝟵 𝟬𝟯 𝟳𝟱 𝟱𝟱 𝟳𝟱

ዋሳ ኤሌክትሮኒክስ
"ሁሉንም አገልግሎት በአንድ ጊዜ እና ቦታ"



https://t.me/Wasa_Electronics