Get Mystery Box with random crypto!

Wasa Electronics

የቴሌግራም ቻናል አርማ wasa_electronics — Wasa Electronics W
የቴሌግራም ቻናል አርማ wasa_electronics — Wasa Electronics
የሰርጥ አድራሻ: @wasa_electronics
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 5.91K
የሰርጥ መግለጫ

አላማችን እንያንዳንዱን ኢትዮጵያዊ የ ቴክኖሎጂ ተጠቃሚና ባለሙያ ማድረግ ነው !
ዋሳ የኢትዮጵያ ናሳ !

Ratings & Reviews

1.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-19 20:08:56
እንኳን ለደብረ ታቦር በዓል በሰላም አደረሳችሁ።
1.1K views17:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 15:04:06
የተለመዱ የላፕቶፕ እና የኮምፒዩተር ችግሮች


1. ከመጠን በላይ መሞቅ (Overheating)
የአየር ማናፈሻ ቱቦዎች ተሸፍነው ላፕቶፕዎን ለስላሳ ወይም ወጣገባ ላይ፣ እንደ አልጋ፣ ትራስ፣ ወይም ጭንዎ ላይ ሲያስቀምጡት የአየር ፍሰትን ይቀንሳል። አቧራ፣ ቆሻሻ፣ ጸጉር የላፕቶፕዎን (fan) ለማቀዝቀዝ ይቸገራል ።

2. ባትሪ በፍጥነት መቀነስ (Battery Dying Quickly)
ባትሪ በፍጥነት መቀነስ ምክንያት default settings program, brightness ,close background programs ,turn down backlit keyboard ,adjust the power plan (save mode)

3. ቫይረሶች ወይም ማልዌር(Viruses or Malware)
ቫይረሶች ወደ ላፕቶፕዎ እንዳይገቡ ለመከላከል በጣም ጥሩው መንገድ የፀረ-ቫይረስ (antivirus software)ሶፍትዌር መጫን ነው። በፀረ-ቫይረስ ሶፍትዌር ላይ ገንዘብ ማውጣት የማይፈልጉ ከሆነ፣ እንደ 'Ad-Aware' እና 'Spybot: Search and Destroy' ከቫይረሶች እና ከማልዌር ለመከላከል ነፃ(software) መጠቀም ይችላሉ።

4. የሲስተም ብልሽት(System Crash)
የኮምፒዩተር ወይም የሲስተም ብልሽት በአጠቃላይ በኮምፒዩተር ላይ ያለ አፕሊኬሽን ወይም ሃርድዌር በትክክል ለመስራት ይቆማል፣ እና አንዳንድ ጊዜ ከብልሽቱ ጋር የስህተት (error code) ሪፖርት ልታዩ ትችላላችሁ፣ አንዳንድ ጊዜ ምንም አይነት የስህተት ኮድ ላታዩ ትችላላችሁ ።
2.8K views12:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 08:23:14
እንኳን አደረሰን ፤ አደረሳችሁ!

ለመላዉ የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1443ኛው ዐ.ሂ ዒድ አል አድሀ (አረፋ) በዐል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን

ዒድ ሙባረክ መልካም በዐል

•═••• •••═• ​​

https://t.me/Wasa_Electronics
767 viewsedited  05:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 22:49:30
ኢትዮጵያ ለምትኖሩ ደንበኞቻችን አንድ አመት ሙሉ ያለምንም "አገልግሎት ክፍያ" (Service Charge) ስናገለግላችሁ እንደቆየን ይታወቃል : ይህም ማለት ደውላችሁ ቀጠሮ አስይዛችሁ ባለሙያዎችን ልከንላችሁ በተለያየ ምክንያት እቃው ሳይሰራ ቢቀር #ለምሳሌ እቃ ቅያሬ የሚያስፈልገው ከሆነና ደንበኛው ራሴ እገዛለሁ ካለ ወይም አሁን እቃ ለመግዛት ዝግጁ አይደለሁም ካለ ፣ እቃው ሊሰራ የማይችልበት ሁኔታ ላይ ከሆነ ወዘተ ••• ምንም ክፍያ ሳንጠይቅ ያለፈውን አንድ አመት አገልግለናችኋል ::

በሀገራችን ኢትዮጵያ ባይለመድም በውጪው ሀገር የአገልግሎት ክፍያ ማለትም ባለሙያ መጥቶ ላየበት ብቻ የሚከፈል ክፍያ የተለመደ ነው : በሀገራችን ኢትዮጵያም ከሐምሌ ወር ጀምረን 100 (መቶ ብር) Service Charge የጀመርን መሆኑን እንገልፃለን

ማሳሰቢያ :- አሜሪካን ሀገር የምትኖሩ ደምበኞቻችን በፊት እንደነበረው Service Charge $75 የሚቀጥል መሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን ::
1.1K viewsedited  19:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 17:24:18 ለምሳሌ አንድ ሰው የቢትኮይን ተጠቃሚ ሲሆን ልክ እንደ ጂ-ሜል እና ፌስ ቡክ የመለያ ስም አውጥቶ የሚስጥር ቁልፍ መርጦ መጠቀሚያ ይከፍታል፡፡ የሚስጥር ቁጥሩ በጣም ጠንካራ በመሆኑ የመሰረቅ አደጋ አይገጥመውም፡፡ ከዚያ ከፈለገው ሰው ጋር ቢትኮይን መላላክ ይችላል፡፡ ያ የተላላከው የገንዘብ ዝውውር በአለም ላይ ባሉ ኮምፒውተሮች ቅጂው ይቀመጣል፡፡ እነዚህ ሁለት ሰዎች ቢከዳዱ እንኳ አለም ላይ ባሉ ኮምፒውተሮች ዝውውሩ ተመዝግቦ በቅጂ መልክ ስለሚቀመጥ እውነቱን ማወቅ ይቻላል፡፡

በቀላል ምሳሌ እንየው፡፡ ለምሳሌ አንድ ሰው ጫማ መግዛት ቢፈልግ እና ባንክ ቤት ገንዘብ ለማውጣት ቢሄድ ባንክ ቤቱ ሰውየው በስሙ ገንዘብ መኖርና አለመኖሩን አረጋግጦ ገንዘብ ይሰጠዋል፡፡ ሰውየው ገንዘብ እንዳለውና እንደሌለው የሚያውቀው ባንኩ ብቻ ነው፡፡ እሱን ካረጋገጠ በኋላ ገንዘቡን ይሰጠውና የሚፈልገውን መግዛት ይችላል፡፡

ሰውየው በክፍያ ካርድ ቢሆን መግዛት የሚፈልገው እና ካርዱን ለባለሱቁ ሰጥቶ የጫማ መግዣውን ቢያስቆርጥ፤ ሰውየው ገንዘብ እንዳለውና እንደሌለው የሚቆጣጠረው በተመሳሳይ ሶስተኛ ወገን የሆነው ባንኩ ነው፡፡

ወደ ቢትኮይን ሰንመጣ የቢትኮይን መጠቀሚያ ያለው ሰው እቃ ገዝቶ የመገበያያ ገንዘብ ወይም ቢትኮይን እንዳለውና እንደሌለው የሚቆጣጠሩት አለም ላይ ያሉ ሰዎች ናቸው፡፡ ቢትኮይን የሚተላለፍለት ሰው ቢትኮይን አለው ወይ ብሎ ሲጠይቅ አለም ላይ ያሉ ኮምፒውተሮች በቂ ቢትኮይን ካለው ‹‹አዎ›› ከሌለው ደግሞ ‹‹የለውም›› ብለው ማረጋገጫ ይሰጡታል፡፡ ክፍያው ከተፈፀመ በኋላ ደግሞ ቅጂው በመላው አለም ላይ ባሉ ኮምፒውተሮች ተሰራጭቶ ይቀመጣል፡፡

ክፍያው ሲፈፀም ግልባጩ አልያም ቅጂው በዓለም ላይ ባሉ ኮምፒውተሮች የሚቀመጠው በሚስጥራዊ ስም ነው፡፡ እንጂ በተገልጋዩ የመጠሪያ ስም አይደለም፡፡ ከመጀመሪያው የቢትኮይን መጠቀሚያ ሲከፈት ሚስጥራዊ ኮድ አብሮ ይፀድቃል፡፡ ያ ምስጢራዊ መጠቀሚያ ማንም የማይከፍተውና ሊያጭበረብረው የሚችል አይደለም፡፡ የመገበያያ ገንዘቡ ለዚያ ነው ረቂቅ አንዳንዶችም ምናባዊ የሚሉት፡፡

ምንዛሬውስ?

ከእነዚህ ዲጂታል ገንዘቦች ውስጥ ቢትኮይን ከፍተኛ ዋጋ ያለው የብሎክ ቼይን ቴክኖሎጂ ነው፡፡ ቢትኮይን በፈረንጆች 2008 ሳቶሺ ናከሞሮ በተባለ ሰው የተፈጠረ ምናባዊ የመገበያያ ገንዘብ ነው፡፡ ይህ አዲስ ዋጋ ያለው ገንዘብ አለም አሁን እየተጠቀመባቸው ካሉ ገንዘቦች ሁሉ በምንዛሬ ከፍተኛ ዋጋ ያለው ረቂቅ ገንዘብ ነው፡፡ የቢትኮይን ዋጋ በየጊዜው ይጨምራል፡፡ የተወሰነ መዋዠቅም ያጋጥመዋል፡፡ ለምሳሌ ግንቦት 2010 ላይ የ1 ቢትኮይን ዋጋ 0.01 ዶላር ነበር፡፡ ታህሳስ 2017 የ1 ቢትኮይን ዋጋ 19ሺ783 ዶላር ደረሰ፡፡ የካቲት 2021 ላይ አንድ ቢትኮይን 60ሺ ዶላር ገብቶ ነበር። ዛሬ ሰኔ 25/ 2014 አንድ ቢትኮይን 19,262.40 ዶላር ነው።

የቢትኮይን ገንዘብ ከፍተኛ ዋጋ አውጥቶ የነበረው እነ ቴስላ በቢትኮይን ላይ ከፍተና ገንዘብ በማፍሰሳቸው ነበር። ባለሃብቶች ቢትኮይንን መግዛት ሲጀምሩ እና የተለያዩ ተቋማት ግብይት በዚህ ዲጂታል ገንዘብ መፈፀም ሲጀምሩ ዋጋው እየጨመረ ይሄዳል።

የብሎክቼን አልሚዎች፡-

የብሎክቼን አልሚዎች (Blockchain miners) በጥብቅ ሰንሰለት ቴክኖሎጂ ውስጥ የሚዘዋወሩ የዲጂታል ገንዘቦችን ዝውውር የሚቆጣጠሩ እና የሚያዘምኑ ናቸው። በዓለም ላይ ባሉ ኮምፒውተሮች ውስጥ የተመዘገቡ መረጃዎች እና የተዘዋወሩ የዲጂታል ገንዘቦችን ትክክለኛነት የሚያረጋግጡ ናቸው። ይህ ስራ በግል እና በቡድን ሊሰራ ይችላል። ብሎክቼንን በማስተዳደር ረገድ ግን ዓለም ላይ ያሉ ሰዎች ሁሉ መብት አላቸው። ዝውውሩን ለማረጋገጥ ደግሞ ከፍተኛ አቅም ያለው ኮምፒውትር ያላቸው ማይነሮች ይሳተፋሉ።

የዲጂታል ገንዘብ የሚነሳበት ተቃውሞ፡-

የዲጂታል ገንዘብ መንግስታት/ባንኮች/ ቁጥጥር ሰለማያደርጉበት ወንጀልን ሊያስፋፋ ይችላል ተብሎ ይሰጋል። ችግር ተፈጥሮ መንግስታት የገንዘብ ዝውውር እገዳ ለመጣል ቢፈልጉ ይህ አስቸጋሪ ይሆንባቸዋል፡፡ ነገር ግን ለሌሎች ዘርፎች የብሎክ ቼይን ቴክኖሎጂ ትልቅ ጠቀሜታ አለው።

አሜሪካ፤ ካናዳ፤ ፊንላንድና ቤልጂየም በተለያየ መልኩ ቢትኮይንን የተቀበሉት ሲሆን ቻይና፤ ሩስያ፤ ቬትናምና ቦሊቪያ ደግሞ እገዳ የጣሉ ሀገራት ናቸው፡፡ ነገር ግን የሀገራት አቋም በተለያዩ ምክንያቶች የሚቀያየርበት ጊዜ አለ።

Prevቀዳሚየኤኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ተቋማት የትምህርት ስርዓትንና የሥራ ፈጠራን በቴክኖሎጂ ለመደገፍ የሚያስችል ስምምነት አደረጉ።

አድራሻ :- ከቦሌ መድኃኔዓለም ወደ ሃያ ሁለት በሚወስደው መንገድ ላይ ከአደይ አበባ ስታዲየም ከፍ ብሎ ወርቁ ህንፃ ፊት ለፊት አበጋዝ ሆቴል አንደኛ ፎቅ

𝟬𝟵 𝟬𝟯 𝟳𝟲 𝟬𝟬 𝟳𝟲 ወይም 𝟬𝟵 𝟬𝟯 𝟳𝟱 𝟱𝟱 𝟳𝟱

ዋሳ ኤሌክትሮኒክስ
"ሁሉንም አገልግሎት በአንድ ጊዜ እና ቦታ"



https://t.me/Wasa_Electronics
1.5K views14:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 17:24:18 ዲጂታል ግብይት ማለት የገንዘብ ዝውውርን ጨምሮ እቃ መግዛትና መሸጥን በዲጂታል መልኩ ማስኬድ ማለት ነው። በመሸጥና በመግዛት ሂደት ውስጥ በኦንላይን ግብይት ከፍያን በተለያዩ የክፍያ አማራጮች ከወረቀት ነፃ በሆነ መልኩ መፈፀም ነው።

የዲጂታል ገንዘብ ከወረቀት ገንዘብ በመውጣት የተለያዩ የቴክኖሎጂ አማራጮችን በመጠቀም ሊታይ እና ሊዳሰስ የማይችል ምናባዊ ገንዘብ መፍጠር ማለት ነው። ይህ የገንዘብ አይነት ገና ወደ አንድ ስምምነት የተመጣበት አይደለም።

ብሎክቼን እና ዲጂታል ገንዘብ

በዓለም ላይ የሚፈጠሩ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች የሰዎችን የአኗኗር ዘይቤ በእጅጉ እየቀያየሩት ይገኛሉ። በተለይ ዲጂታል ቴክኖሎጂው መሰፋፋት በተለምዷዊው አሰራር መጓዝ ለሚፈልጉት ፈተና እየሆነባቸው ነው። እነዚህ ሰዎች ሳይወዱ በግድ ቴክኖሎጂው በራሱ ጊዜ ይዟቸው ይጓዛል፡፡ ካልሆነ ግን ከውድድር ውጭ መሆን ነው።

በአሁኑ ጊዜ የፋይናንስ ስርዓቱ ወደ ዲጂታል አሰራር እየተቀየረ ነው። የወረቀት ብር ዝውውር በእጅጉ እቀነሰ በዲጂታል መልኩ ክፍያ እና ግብይት እየተፈፀመ ከፍ ሲል ደግሞ የዲጂታል መገበያያዎች እየተፈጠሩ ነው። የገንዘብ ዝውውር በአጭበርባሪዎች አይን ውስጥ ሰለሚገባ በከፍተኛ ደረጃ ቁጥጥር እና ጥንቃቄ የሚያስፈልገው ነው።

ለዚህ ነው የቴክኖሎጂ ባለሙያች ፊታቸው ወደ ብሎክቼን እና የዲጂታል ገንዘብ እያዞሩ ያሉት።

ጥብቅ ሰንሰለት (ብሎክ ቼይን) ምንድነው? የተቀመረ (የዲጂታል) ገንዘብስ?

በአገልግሎት አሰጣጥ ውስጥ በመካከል አገልግሎቱን የሚሰጥ የታመነ አንድ አካል ይኖራል። ለምሳሌ በገንዘብ ዝውውርና ቁጠባ ውስጥ ባንክ የሚባል የታመነ ተቋም አለ። በመሬት አሰተዳደር ውስጥ ደግሞ መንግሰት ያቋቋመው መሬት አስተዳደር ወይ ደግሞ ሌላ ስም የተሰጠው መስሪያ ቤት ይኖራል። ባንኮች ከደንበኞቻቸው ገንዘብ በመቀበል ያስቀምጡላቸዋል። ገንዘብ ያዘዋውሩላቸውል። ግብይት እንዲፈፀሙ ያደርጓቸዋል። ደንበኛው ባንኩን ስለሚያምን ገንዘቡን ያስቀምጣል።

በመሬት አሰተዳደር ውስጥ ደግሞ ዜጎች የመሬት ባለቤትነት ማረጋገጫቸውን መንግስት ይሰጣቸዋል። መሬታቸውን በማስመዝገብና በማስተዳደር መካከል መንግስት ያቋቋመው አንድ ተቋም አለ። እነዚህ ተቋማት ውስጥ ያሉ ሰራተኞች ደንበኞቻቸውን ማጭበርብር ቢፈልጉ ሊያደርጉት ይችላሉ። ለምሳሌ አንድ 10 ሄክታር ያለው አርሶ አደር መሬት አስተዳደር ውስጥ ያሉ ሰዎች 2ቱን ሄክታር ለሌላ ሰው አስተላልፈው 8 ሄክታር ነው ያለህ ሊሉት ይችላሉ። ወይንም አንድ መኖሪያ ቤት ያለውን ሰው መረጃዎቹን በማጥፋት ሰሙን በሌላ ሰው አዙረው ቤት የለህም ብለው ሊያጭበረብሩት ይችላሉ።

የጥብቅ ሰንሰለት ቴክኖሎጂ ይህንን ችግር ለመቅረፍ እና በሶስተኛ ወገን ያሉ አካላትን ከመካከል ለማውጣት እቅድ ያለው ቴክኖሎጂ ነው። ያ ማለት በማይሳሳት፣ በማይሰረዝ እና በማይጭበረበር በሶስተኛ ወገን ጣልቃ ገብነት በማይዘረፍ ስርዓት መተካት ነው።

ጥብቅ ሰንሰለት ወይም ብሎክቼን በሚሊየን የሚቆጠሩ የኮምፒውተር መረጃዎችን ባልተማከለ መልኩ የሚመዘግብ የብሎክ ጥርቅም የሆነ ቴክኖሎጂ ነው፡፡ ይህ ቴክኖሎጂ በባንኮች እጅ የሚገኘውን እና በመንግሥታት ግምጃ ቤት ቁጥጥር የሚደረግበትን የገንዘብ ዝውውርና የመረጃ ፍሰት ያልተማከለ ለማድረግ እቅድ አለው።

ከዚህ በተጨማሪ ከገንዘብ ዝውውር እስከ የመሬት ባለቤትነት ምዝገባ ያሉ ሥራዎችን ሊከወንበት እንደሚችል ተስፋ የተጣለበት አዲስ ቴክኖሎጂ ነው፡፡

መረጃዎች በሁሉም ኮምፒውተሮች ተመዝግቦ ስለሚገኝ በጭራሽ የማይሳሳት፣ የማይሰረዝ እና የማይጭበረበር በሶስተኛ ወገን ጣልቃ ገብነት የማይዘረፍ የአሰራር ሥርዓት ያለው ቴክኖሎጂ ነው፡፡ለምሳሌ አንድ ሰው በዲጂታል መልክ ያለውን የገንዘብ መጠን ላይ አንድ ዜሮ ጨምሮ መጠኑን ከፍ ለማድረግ ሙከራ ቢያደርግ ዓለም ላይ ያሉ ኮምፒውተሮች ላይ መረጃው ሰለሚመዘገብ ኮምፒውተሮቹ ማጨበርበሩን ይነግሩትና ውድቅ ያደርጉበታል።

ይህ ቴክኖሎጂ በተለይ በአፍሪካ ምድር አጨቃጫቂና የግጭት መንስኤ የሆነውን የመሬት አስተዳደርን በመመዝገብ ችግሩን ይፈታል ተብሎ ይታመንበታል፡፡ በጥብቅ ሰንሰለት (በብሎክ ቼይን) ቴክኖሎጂ የተመዘገበ የመሬት አስተዳደር ስርዓት ደግሞ በሁሉም ኮምፒውተሮች ተመዝግቦ ስለሚገኝ በኃላፊዎችና በሰራተኞች ከሚደርስበት መጭበርበርና ከሶስተኛ ወገን ስርቆት ይገጥመዋል ተብሎ የማይሰጋበት ከስርቆት የፀዳ ያደርገዋል፡፡ ለምሳሌ አንድ ሰው መኪና ገዝቶ ክፍያውን በዚህ ቴክኖሎጂ ቢፈፅምና ሻጩ አልሰጠኝም ብሎ ቢክድ ዓለም ላይ ኮምፒተሮች ለገዢው ምስክር ሆነው ይቆማሉ።

በብሎክቼይን የተመዘገበ አንድ መሬት በሙስና ለሌላ ሰው ቢተላለፍ መረጃው ኮፒ ሆኖ በአለም ላይ ባሉ ኮምፒውተሮች ስለሚቀመጥ የትም ቦታ ላይ ይህ ስራ እንደተሰራ ስለሚነግረን ሙሰኞችን ለመቆጣጠር ያስችላል፡፡ ከአፍሪካ ውስጥ ሩዋንዳ ወደዚህ ቴክኖሎጂ በመግባት የመሬት አያያዝን ለማዘመን በቴክኖሎጂው ባለሙያዎች ጋር ስምምነት ተፈራርማ እንቅስቃሴ ማድረግ ጀምራለች፡፡

ኢትዮጵያ ደግሞ የብሎክቼን ቴክኖሎጂን ለማስተዋወቅ ለመጀመሪያ ጊዜ ሴቶች ብቻ የተሳተፉበትን ቡድን አሰልጥና አስመርቃለች። እነዚህ ሴቶች በተለያዩ ተቋማት ውስጥ ስራዎችን እየሰሩ ይገኛሉ። ይህም ኤሌክትሮኒክስ የገንዘብ ዝውውር ስርዓት ውስጥ ዲጂታላይዝ የሆነ ስርዓትን ለመፍጠር የምታደርገውን ጥረት የሚደግፍ ነው፡፡

ብሎክ ቼይን የተሳካና ግልፅ የሆነ ምርጫም ለማካሄድ ጥቅም ላይ ይውላል፡፡ ለዲጂታል መታወቂያ፤ የማንፈልጋቸውን መረጃዎች ሙሉ ለሙሉ ለመሸጥ፤ የቅጅ መብትን ለማስጠበቅ፤ ለቤቶች አስተደዳር፤ የእቃ ዝውውርን ለማከናወን፤ ለግብር መክፈያ፤ ለህክምና ስራ (የታካሚዎችን መረጃ ለመያዝ እና ለመሳሰሉት)፤ ለህገወጥ የመሳሪያ ዝውውር ቁጥጥር፤ እና ለመሳሰሉት ጥቅም ላይ የሚውል ቴክኖሎጂ ነው፡፡

የተቀመረ ገንዘብ (ዲጂታል ገንዘብ) ወይም ክሪፕቶ ከረንሲ ምንድነው?

የቴኖክሎጂ ባለሙያዎችን እስከ ዛሬ ሲያስጨንቃቸው የነበረው ጉዳይ አንድን እቃ ቅጂው እጃቸው ላይ ሳይኖር ለሌላ ሰው እንዴት ማስተላለፍ ይቻላል? የሚለው ነው፡፡ ለምሳሌ 50 ብርን ለአንድ ሰው በዲጂታል መንገድ ለመላክ ኮፒው ላኪው ጋር አለመቅረቱ ምንም ማረጋገጫ የለም፡፡ ይህ ጉዳይ ክሪፕቶግራፈሮች ለረጅም ጊዜ ሲቸገሩበት የነበረው ጉዳይ ነው፡፡ ክሪፕቶ ከረንሲ ይህንን ችግር የፈታና የዲጂታል ገንዘብ ቅጂው ላኪው ጋር ሳይቀር መላክ የሚያስችል አዲሱ ቴክሎጂ ነው፡፡

የጥብቅ ሰንሰለት ቴክኖሎጂ ወይም ብሎክቼን የዲጂታል ገንዘቦችን (ምናባዊ ገንዘብ) ይጠቀማል። ለምሳሌ አለም ላይ ብር፣ ዶላር፣ ዩዋን የሚባሉ የወረቀት መገበያያ ገንዘቦች እንዳሉ ሁሉ ቢትኮይን፣ኢቲሪየም፤ ኢቲሪየም ካሽ፤ ዳሽ፤ ዚካሽ የሚባሉ የዲጂታል ገንዘቦች አሉ።

በተለመደው አሰራር የሀገራት የገንዘብ ዝውውር መንግስት እና ባንኮች የሚቆጣጠሩት ነው፡፡ ቢትኮይን የተባለው ገንዘብ ግን ዝውውሩን የሚቆጣጠረው ባለቤቱ ሲሆን የዝውውሩ ህጋዊነት ማረጋገጫ ደግሞ ሁሉም የቢትኮይን ተጠቃሚዎች ናቸው፡፡ ሰዎች በአለም ላይ ካሉ ከሚፈልጉት ሰው ጋር በየትኛውም ቦታ ሆነው ሶስተኛ ወገን ወይም ባንክ ሳያስፈልግ የሚገበያዩበት ቴክኖሎጂ ነው። ማንም ሊቆጣጠረው እና ሊያጭበረብረው አይችልም፡፡ መንግስታትም ቢሆኑ፡፡ ቁጥጥሩ በሁሉም ግልሰቦች እጅ ሆኖ በሁሉም የቢትኮይን ረቂቅ ገንዘብ ተጠቃሚ ኮምፒውተሮች ላይ መረጃዎቹ ሰፍረው ይገኛሉ፡፡
1.1K views14:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 09:23:17
አድራሻ :- ከቦሌ መድኃኔዓለም ወደ ሃያ ሁለት በሚወስደው መንገድ ላይ ከአደይ አበባ ስታዲየም ከፍ ብሎ ወርቁ ህንፃ ፊት ለፊት አበጋዝ ሆቴል አንደኛ ፎቅ

𝟬𝟵 𝟬𝟯 𝟳𝟲 𝟬𝟬 𝟳𝟲 ወይም 𝟬𝟵 𝟬𝟯 𝟳𝟱 𝟱𝟱 𝟳𝟱

ዋሳ ኤሌክትሮኒክስ
"ሁሉንም አገልግሎት በአንድ ጊዜ እና ቦታ"



https://t.me/Wasa_Electronics
1.2K views06:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-24 16:05:17
አድራሻ :- ከቦሌ መድኃኔዓለም ወደ ሃያ ሁለት በሚወስደው መንገድ ላይ ከአደይ አበባ ስታዲየም ከፍ ብሎ ወርቁ ህንፃ ፊት ለፊት አበጋዝ ሆቴል አንደኛ ፎቅ

𝟬𝟵 𝟬𝟯 𝟳𝟲 𝟬𝟬 𝟳𝟲 ወይም 𝟬𝟵 𝟬𝟯 𝟳𝟱 𝟱𝟱 𝟳𝟱

ዋሳ ኤሌክትሮኒክስ
"ሁሉንም አገልግሎት በአንድ ጊዜ እና ቦታ"



https://t.me/Wasa_Electronics
2.0K viewsedited  13:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-17 16:02:04
አድራሻ :- ከቦሌ መድኃኔዓለም ወደ ሃያ ሁለት በሚወስደው መንገድ ላይ ከአደይ አበባ ስታዲየም ከፍ ብሎ ወርቁ ህንፃ ፊት ለፊት አበጋዝ ሆቴል አንደኛ ፎቅ

𝟬𝟵 𝟬𝟯 𝟳𝟲 𝟬𝟬 𝟳𝟲 ወይም 𝟬𝟵 𝟬𝟯 𝟳𝟱 𝟱𝟱 𝟳𝟱

ዋሳ ኤሌክትሮኒክስ
"ሁሉንም አገልግሎት በአንድ ጊዜ እና ቦታ"



https://t.me/Wasa_Electronics
2.3K views13:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-02 09:08:41
ውድ የእስልምና እምነት ተከታይ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን በሙሉ እንኳን ለ 1443ኛው የ ኢድ አል ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

በዓሉ ከ ምንግዜውም በላይ የሰላም ፣ የደስታ ፣ የፍቅር ፣ የመተሳሰብ ይሆን ዘንድ እንመኛለን።


EID MUBARAK!


https://t.me/Wasa_Electronics
3.5K viewsedited  06:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ