Get Mystery Box with random crypto!

Orthodox Mezmur | ኦርቶዶክስ መዝሙር

የቴሌግራም ቻናል አርማ ortodox_mezmure — Orthodox Mezmur | ኦርቶዶክስ መዝሙር O
የቴሌግራም ቻናል አርማ ortodox_mezmure — Orthodox Mezmur | ኦርቶዶክስ መዝሙር
የሰርጥ አድራሻ: @ortodox_mezmure
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 959
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ ቻናል ላይ ማንኛውንም ☦☦የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ስርአትን የጠበቁ
✥ አስተምሮቶችን ✟
❖ ስብከቶችን ✟
❖ መዝሙሮችን ✟
❖ መንፈሳዊ መጽሐፍቶችን ያገኛሉ።☨☨

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-23 14:27:41
46 views11:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-23 10:10:33
"ከድንግል ማርያም ሥጋን የተዋሐደ እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ሰውንም የፈጠረ ከሙታን ተለይቶ የተነሳ ሙታንንም የሚያስነሳ እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው።"

ሃይማኖተ አበው ዘሄሬኔዎስ

https://t.me/Ortodox_Mezmure
57 viewsedited  07:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-21 18:10:15
ለአራት ቀናት ብቻ ለሞተው አልዓዛር ያለቀሰ ጌታ ለዘመናት በኃጢአት ለሞትን ለእኛ ምንኛ ያለቅስ ይሆን? ሰውነታች በበደል ለረከሰ ፣ በምኞት መቃብር ለተቀበርን ፣ በዝሙት ለተበላሸን ፣ በጥላቻ ለሸተትን ለእኛ ክርስቶስ ምንኛ ያለቅስ ይሆን? የኃጢአት ድንጋይ ተጭኖን ፣ የፍትወት መግነዝ ተጠምጥሞብን ላለን ለእኛ የጌታ ዕንባ ምን ያህል ይፈስስልን ይሆን? አልዓዛርስ ውጣ ቢባል ይወጣል ፣ ካለንበት ኃጢአት መቃብር መውጣት ለማንፈልግ ለእኛ ጌታ እንደምን ያለቅስ ይሆን? የእኛ ሞት ከአልዓዛር ሞት በላይ ዘልቆ የማይሰማው ይመስላችኋል? እንዴት አይሰማውም? ለአልዓዛር ዕንባውን ያፈሰሰው ጌታ ለእኛ እኮ ያፈሰሰው ደሙን ነው ።
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

https://t.me/Ortodox_Mezmure
71 viewsedited  15:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-19 13:09:04
" ከአለቃችሁ ከሚካኤል በቀር ማንም የሚያጸናኝ የለም። "

[ ዳን፲፪፥፩ ]

---------------------------------------------------

በዚያች ሌሊትም ድንቅ መልአክ ቅዱስ_ሚካኤል ከሰማያት በግርማ ወረደ:: ወደ ሰናክሬም የጦር ሠፈር ደርሶ አንድ ጊዜ የእሳት ሰይፉን መዝዞ ቢያሳያቸው ከአሕዛብ ሠራዊት ፻፹፭ ሺህ [185] ሺ ኃያላን እንደ ቅጠል ረገፉ:: በለኪሶ የነበረው ሰናክሬም በጧት ቢነሳ ሠራዊቱ ሁሉ ወደ አስከሬን ክምር ተቀይሯል::

በድንጋጤ ወደ ነነዌ ሒዶ ወደ ጣዖት ቤቱ ሲገባ የራሱ ልጆች [አድራማሌክና ሳራሳር] ገደሉት:: ትዕቢተኛው ሰናክሬም ለአሕዛብ ሁሉ መዘባበቻ ሆነ:: ቅዱስ ሕዝቅያስ ግን በፈጣሪው ታምኗልና ቅዱስ ሚካኤል ሞገስ ሆኖ የዓለም ነገሥታት ሁሉ ፈሩት:: [፩ነገ.፲፰፥፲፫] [፲፱፥፩]


እግዚአብሔር በሊቀ መላእክት ክንፍ ሃገራችንን ከአሕዛብ ስውር ጦር ይጠብቅልን:: ከሰማዕቱም በረከት ያሳትፈን::

https://t.me/Ortodox_Mezmure
121 viewsedited  10:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 17:28:17
204 views14:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 17:27:27
" ጴጥሮስ ሆይ የተሰቀልክበትን መስቀል ተስፋ ይሆነኝ ዘንድ ሰጠኝ
ጳውሎስም በአንገትህ መቆረጥ ደም የነካት መጎናጸፊያ ተስፋ እንዲሆነኝ ስጠኝ"
መልክአ ጴጥሮስ ወጳውሎስ
https://t.me/Ortodox_Mezmure
179 viewsedited  14:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 17:26:29
" የዮና ልጅ ጴጥሮስ ሆይ ደምህ በመስቀል ጽዋ ተቀዳ የጳውሎስ ደም ደግሞ ወደ ሰማያት ጮኸ
                                         ቅዱስ ያሬድ

" ክርስቶስ ለደቀ መዛሙርቱ በዚህ ዓለም ሳሉ ብቻ ሳይሆን ከሞቱ በኃላ እንኳ እንዲያበሩና እንዲሠለጥኑ አድርጓቸዋል ።እስኪ ንገረኝ የታላቁ እስክንድር መቃብር የት አለ ? እንዲሁም የሞተበትን ቀን እስኪ ንግረኝ የክርስቶስ አገልጋዮች ግን መቃብራቸው እንኳ ሳይቀር የተከበረ ነው ያረፉበት ቀንም በሚገባ የታወቀ ነው ዕለተ ዕረፍታቸውም በዓለሙም ሁሉ የበዓል ቀን ሆኖ ይከበራል "
                                ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

እንኳን ለቅዱሳን ሐዋርያት ለቅዱስ  ጴጥሮስ እና ቅዱስ ጳውሎስ ዓመታዊ መታሰቢያ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!!

ሁለቱ ቅዱሳን ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስ እና ቅዱስ ጳውሎስ መድኃኒዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰማያዊ አገልግሎት በድንቅ አጠራሩ የጠራቸው ናቸው  በማቴ 4 ፣18 እንደተጻፈ ቅዱስ ጴጥሮስ ከወንድሙ ቅዱስ እንድርያስ ጋር ሆኖ ዓሳ በማጥመድ ላይ እያለ ጌታ ኑ እና ሰዎችን የምታጠምዱ አድርጋችኃለው ሲላቸው መረቡን ትቶ የተከተለ ቅዱስ ሐዋርያ ነው በሐዋ 9፣14 እንደተጻፈ ቅዱስ ጳውሎስ ክርስቲያኖችን ለማሳደድ ከሊቀ ካህናቱ የፍቃደ ደብዳቤ ይዞ በደማስቆ ሲያልፍ ጌታ ለሐናንያ እንዳለው በአህዛብ እና በነገሥታት በእሥራኤል ልጆች ፊት የጌታን ስም ይሸከም ዘንድ የተመረጠ እና የተጠራ ምርጥ ዕቃ ነው ።ለተጠሩለት አገልግሎትም እስከ መጨረሻው ታምነው እስከ ምድር ዳርቻ ሄደው ወንጌልን በብዙ ትጋት ያስተማሩ ቅዱሳን ናቸው የቤተ ክርስቲያናችን ጌጥ ቅዱስ ያሬድ በዝማሬው ይሄንን ሲገልጽ እንዲህ ይላል
       "  ቅድመ ዓለም የነበረ ዛሬ የለ ወደ ፊትም ዓለምን አሳልፎ ለዘለዓለም የሚኖር የእግዚአብሔር ቃል ስምዖን ጴጥሮስንና ጳውሎስን መምህራን አድርጎ ለሰማያዊ ሥራ ሾማቸው ሂዱ አስተምሩ በስሜ ስበኩ አላቸው ከዚያ ትምህርታቸው በዓለም ሁሉ ተሰማ "

ቅዱስ ጴጥሮስ ዓሳ የሚያጠምድበትን መረብ ትቶ ክርስቶስን የተከለበትን የአገልግሎት ጥሪ በምድር ላይ ፈጽሞ ወደ አምላኩ በክብር የሚሄድበት ጊዜ ሲደርስ በዘመኑ የክርስቲያኖች ጠላት የነበረው የሮም ንጉሥ ወደ አካይያ ዘምቶ ድል አድርጎ በደስታ ወደ ሮሜ ሲመለስ መኳንንቱን ለማስደሰት፤ ጣዖታቱንም ለማክበር ሲል በቅዱስ ጴጥሮስና በሌሎችም ክርስቲያኖች ላይ የሞት ፍርድ ዐወጀ፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስም በሮም ሲያስተምር ቆይቶ የሮም መኳንንት እንዳይገድሉት ትጥቁን ለውጦ ከሮም ሲወጣ ጌታችን መስቀል ተሸክሞ ተገለጸለት፡፡
በዚህ ጊዜ ‹‹አቤቱ ጌታ ሆይ ወዴት ትሔዳለህ?›› ሲል ቢጠይቀው።  ጌታችንም ‹‹ልሰቀል ወደ ሮም እሔዳለሁ›› አለው፡፡ ‹‹ዳግመኛ ትሰቀላለህን?›› ባለው ጊዜም ‹‹አንተ ስትፈራ ጊዜ ነው ›› ሲል መለሰለት፡፡ ያን ጊዜም ‹‹ጐልማሳ ሳለህ ወገብህን ታጥቀህ ወደ ወደድከው ትሔድ ነበር ስትሸመግል ግን እጅህን ታነሣና ሌላ ሰው ያስታጥቅሃል፤ ወደማትወደውም ይወስድሃል፤›› ዮሐ 21፣18 በማለት ጌታችን የነገረው ቃል አሟሟቱን የሚያመለክት መሆኑን አስታውሶ ወደ ሮም ተመልሶ ስብከቱን ቀጠለ በሮማውያን እጅም ወደቀ ። እንደ ሥርዓታቸውም ቅዱስ ጴጥሮስን ከገረፉት በኋላ ሊሰቅሉት ሲሉ ወታደሮቹን ‹‹እንደ ክብር ንጉሥ እንደ ጌታዬ  ኢየሱስ ክርስቶስ አቁማችሁ ሳይኾን፣ ዘቅዝቃችሁ ስቀሉኝ›› አላቸው ቅዱስ ያሬድ በድጓው " ጴጥሮስ ወደ መስቀል ፊት ተመለከተ እንዲህም ሲል ጸለየ እኔ ወደ መስቀል መውጣትን ለምን እታክታለሁ ለምን እሰንፋለሁ ሲል ቁልቁል ይሰቅሉት ዘንድ ጠየቀ" እንዳለ
እነርሱም እንዳላቸው አድርገው ሐምሌ 5 ቀን ዘቅዝቀው ሰቅለውታል፡፡ በመስቀል ላይ ሳለም ተከታዮቹን በሃይማኖታቸው እንዲጸኑ ካዘዛቸው በኋላ ነፍሱን ለእግዚአብሔር ሰጠ፡፡

ብርሃን ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ በደማስቆ ሳለ የተጠራበትን አገልግሎት የጌታ ምርጥ ዕቃ ሆኖ ፈጽሞ ሲጨርስ ወደ አምላኩ በክብር የሚሄድበት ጊዜ ሲደርስ የሮም ንጉሥ ኔሮን ቄሣር የክርስቲያኖች ቍጥር እየጨመረ የመጣው በቅዱስ ጳውሎስ ትምህርት በመማረካቸው ምክንያት መኾኑን ተረድቶ፤ ይልቁንም የቤተ መንግሥቱ ሰዎች ሳይቀር በቅዱስ ጳውሎስ በመማረካቸው ተቈጥቶ ቅዱስ ጳውሎስን ወደ ፍርድ ሸንጎው አስቀረበው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም በቀኝ እጁ ከሰንሰለቱ ጋር መስቀሉን ይዞ ንጉሡንና ወታደሮችን ሳይፈራ የኢየሱስ ክርስቶስን የእግዚአብሔር ልጅነትና አምላካዊ ሥልጣን ይመሰክር ነበር፡ንጉሡም በቍጣ ይሙት በቃ ፈረደበት።  ወደሚገደልበት ስፍራ ሲወስዱትም በንግግሩና በአስተያየቱ ሁሉ ምንም ፍርኀት አይታይበትም ነበር፡፡ እንዳውም በጦርነት ድል አድርጎና ማርኮ እንደ ተመለሰ ወታደር ይደሰት ነበር እንጂ፡፡ ለሚገድሉትም ይቅርታን ይለምን ነበር፡፡

በገዳዮቹና በተከታዮቹ ፊትም የክርስትና ሽልማቱ የእግዚአብሔር መንግሥት መኾኑን የሚያስገነዝብ ቃል እያስተማረ እግዚአብሔር የሚሰጠውን የጽድቅ አክሊል ለመቀበል ይቻኮል ነበር ፡፡ ወታደሮች ሊገድሉት ሲወስዱትም ከንጉሥ ኔሮን ወገን የኾነችውን የአንዲት ብላቴና መጐናጸፊያ ‹‹ዛሬ እመልስልሻለሁ›› ብሎ ከተቀበላት በኋላ ‹‹መልካሙን ገድል ተጋድያለሁ፤ ሩጫዬን ጨርሻለሁ ሃይማኖቴን ጠብቄአለሁ፤ ወደፊትም የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶልኛል፤›› በማለት ራሱ በመልእክቱ እንደ ተናገረው  ፊቱን በብላቴናዋ መጐናጸፊያ ተሸፍኖ አንገቱን በሰይፍ ተቀልቶ አገልግሎቱን በሰማዕትነት ፈጽሟል፡፡

" ቅዱስ ጴጥሮስ የሃይማኖት ዐለት ነው ቅዱስ ጳውሎስ ልሳነ ምዑዝ ነው በታወቀች በዓላችሁ የምሕረት አሥራታችሁን ያዙ " ብሎ ቅዱስ ያሬድ በዝማሬው እንዳመሰገናቸው በእነዚህ በከበሩ ቅዱሳን ሐዋርያት የዕረፍት ቀን ጌታ ለሀገራችን እና ለህዝቦቿ ምሕረትን ያደርግ

https://t.me/Ortodox_Mezmure
150 viewsedited  14:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 06:09:37

132 views03:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 06:09:21 አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ (ገብረ ሕይወት)

ጻድቁ የተወለዱት ግብፅ (ንሒሳ አካባቢ) ሲሆን አባታቸው ስምዖን እናታቸው አቅሌስያ ይባላሉ:: አባታችን ገብረ ሕይወት የጻድቃን አለቃ የቅዱሳን የበላይ ተጋድሎአቸውና ድንቅ ተአምራቸው እንደ ሰማይ ከዋክብት የበዛ ቅዱስ ሰው ናቸው። የጻድቁን ክብር መናገር የሚችል ምን አነደበት ይኖራል? እንደ ምንስ ባለ ብራና ይጻፋል? ዜናቸውንስ ለመስማት የታደለ እንደ ምን ዓይነት ሰው ይሆን?

አባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስ ለ562 ዓመታት በዚህች ዓለም ሲኖሩ እህል ያልቀመሱ /ምግባቸው ምስጋና ነውና/ ልብስ ያልለበሱ /ጠጉር አካላቸውን ይሸፍን ነበርና/ ሐዋርያዊ ሆነው ከግብፅ እስከ ኢትዮዽያ ብዙ ነፍሳትን ያዳኑ አባት፤ ሃገራችንን አስምረው አስራት እንድትሆናቸውም ተቀብለው ምድረ ከብድ አካባቢ አርፈዋል።

ጻድቁ ገብረ መንፈስ ቅዱስም ገብረ ሕይወትም ይባላሉ። በ562 ዓመታት ሕይወታቸው እንደ ሐዋርያት ከምድረ ግብፅ እስከ ኢትዮዽያ ወንጌልን ሰብከዋል። በዚህም በሚሊየን (አእላፍ) ለሚቆጠሩ ነፍሳት የድኅነት ምክንያት ሆነዋል።

ጻድቁ እንደ ሰማዕታትም ከከሃዲ ሰዎች ብዙ መከራን ተቀብለዋል። እንደ ባሕታውያን ለብዙ መቶ ዓመታት ሰው ሳያዩ ቆይተዋል። ለየት የሚለው ግን የጽድቅ ሕይወታቸው ነው፤ ከእልፍ አዕላፍ አጋንንት ጋር ተዋግተው ድል ማድረግ ችለዋልና።

የንሒሳው ኮከብ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ለኢትዮጵያ ልዩ ፍቀር አላቸው። ስለ ሃገሪቱና ሕዝቧ ፍቅር ሲሉ ለ100 ዓመታት በደብረ ዝቋላ መከራን ተቀብለዋል። ምሕረትን ሲለምኑ ሥጋቸው አልቆ በአጥንታቸው ቁመው ነበርና ሃገራችን አሥራት ሆና ተሰጠቻቸው።

ስለዚህም ነው በሃገሪቱ ውስጥ ከ2,000 በላይ የጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳማትና አድባራት ዛሬም ድረስ ያሉት። በ8ኛው ክ/ዘመን አካባቢ የተወለዱት አባታችን ያረፉት በ14ኛው መቶ ክ/ዘመን አካባቢ ነው። ፍጥረታትን ሁሉ አዘው መጋቢት 5 ቀን ሲያርፉ ግሩማን መላእክት ገንዘው አካላቸውን ሠውረዋል።

ሥላሴን የተሸከመ አካላቸው በጐልጐታ ተቀብሯል የሚሉም አሉ። "ሰላም ለመቃብሪከ ዘኢተከሥተ ለባዕድ: ከመ መቃብሩ ለሙሴ ወልደ ዮካብድ: ዜና መቃብሪከሰ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ጸማድ: ቦ ዘይቤ በኢየሩሳሌም አጸድ: ወቦ ዘይቤ ኀለወ በከብድ።" እንዲል::

ጻድቁ አባታችን አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ እረፍቱ መጋቢት 5 ቀን ነው ይህ ደግሞ በታላቁ ዓብይ ጾም ወቅት ነው ፍትሃ ነገስት አንቀጽ 15 ላይ በዓብይ ጾም በዓል ማክበር ይከለክላል የሀዘን ወቅት ነውና ከበሮ አይመታም እልልታና ጭብጨባ የለም ፍጹም ሀዘን እንጂ የመጋቢት 27 ስቅለት ጥቅምት 27 ቀን እንደሚከበረው ሁሉ ወደ ጥቅምት 5 ቀን ተዛውሮ እንዲከበር ተደረገ፡፡

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

#ስንክሳር_ዘወርኀ_ጥቅምት
134 views03:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 22:00:26
እርስዋም አንተ አይሁዳዊ ስትሆን ሳምራዊት ከምሆን ከእኔ ውኃ ትለምናለህ? አለችው፡፡ እንዲህ ነው ነገሩ፡፡ የቆሰለች ነፍስ ስለ ዘር ታወራለች፡፡ ተስፋ የቆረጠች ነፍስ የዘር ጉዳይ ሲሆን ልሳንዋ ይከፈታል፡፡ ውኃ ለማጠጣት ዘር መጠየቅን ምን አመጣው፡፡ ውኃው አይሁዳዊ ነው? ወይንስ ሳምራዊ? ውኃ ጠማኝ የሚል ሁሉ ውኃ ይገባዋል እንጂ ዘሩ አይጠየቅም፡፡ እርስዋ ግን ጠየቀችው፡፡ በእርግጥ ይህች ሳምራዊት ሴት ይህን ጥያቄ የጠየቀችው ክርስቶስ መሆኑን ከማወቅዋ በፊት ነበር፡፡ ክርስቶስ መሆኑን ካወቀች በኋላ ግን ስለ አይሁዳዊነትና ስለ ሳምራዊነት ስትናገር አልተሰማችም፡፡ ‘’አንተ አማራ ስትሆን ጉራጌ ከምሆን ከእኔ ውኃ ለምን ትለምናለህ?’’ ‘’አንቺ ኦሮሞ ስትሆኚ ትግሬ ከምሆን ከእኔ እንዴት ውኃ ትለምኛለሽ?’’ በሚል ጥያቄ ሀገሩን ያጨናነቁተ ክርስቶስን ያወቁ ክርስቲያኖች መሆናቸው ግን ልብን የሚሰብር እውነታ ነው፡፡ በዚህ ጠባያችን እንደ ክርስቲያን ሳንኖር እንደ ክርስቲያን ልንሞት መሆኑ ምንኛ ያሳዝናል?

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

https://t.me/Ortodox_Mezmure
192 viewsedited  19:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ