Get Mystery Box with random crypto!

ጦቢያ የግጥም መድብል

የቴሌግራም ቻናል አርማ was143 — ጦቢያ የግጥም መድብል
የቴሌግራም ቻናል አርማ was143 — ጦቢያ የግጥም መድብል
የሰርጥ አድራሻ: @was143
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4.90K
የሰርጥ መግለጫ

አማራ ነኝ ያውም ትግሬ
እንደ ሮሃ ተፈልፍዬ፣ልክ እንደ አክሱም ተገትሬ
ምጠብቅሽ እልፍ ዘመን፣በጣይ እና በጨረቃ
ስቀልድ ነው ኦሮሞ ነኝ፣ከተናገርኩ በሀቂቃ
እንደውም ሁሉን ብሔር ነኝ፣ዘረኝነትን የምደቃ
ዘሬ ሰው ነው፣ብሔሬም ሰው፣ሰው ነኝ በቃ
።።።።።።።።።።
@WAS143 ይጎብኙ
@WAS143
@WAS143
በቀጥታ ለማግኘት
@WASYA
@WASYA
ማንኛውንም መልዕክት ለመላክ
@WASYA

Ratings & Reviews

1.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-27 17:26:26 "የማርያም ማጀት"
ኤልያስ ሽታኹን
~ ~ ~ ~ ~
እንዴት አባበልች መለኮትን አቅፋው?
ይነግራት ነበረ እግዜርም ሲከፋው?
ማርያም
ቅሩብ ለትሁታን
ማርያም
ተስፋቸው ለሙታን

ልጅ ሰጪ ለመሃን
ማርያም እመብርሃን::

መጽሐፉማ ይላል
"እንቅልፍ የለው ከቶ"
እግዜር ግን ተገኘ ድንግል ስር ተኝቶ::
እንቅልፉን ወሰደው መለኮት በስጋ
ያርፍባት የለም ወይ እጇን የተጠጋ::

ማነው የጎበኘው የማርያምን ማጀት?
ለራበው ታዝናለች እንደልጇ ካንጀት::

በምን አቦካችው የ'ለት ዱቄት መና
ውኃ ቀድታ ነበር? ወይ ወርዶ ደመና?

አይባልም ለርሷ
እንጀራና ዳቦ እንዴት ጋገረችው
እሳት አይደለም ወይ የተሸከመችው?

@WAS143
@WAS143
414 viewsWasye, 14:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 17:25:29 "ልጇን የጠረጠረ
የእናቱን አበሰረ"
ኤልያስ ሽታኹን
~ ~ ~ ~ ~
ነፍሴና ጉልበቴ ይሉልሻል በርከክ
ውዳሴሀ ለእግዝትነ ማርያም
ዘይትነብብ በ'ለተ ሰርክ::

ሰኞ
ቶማስን ያየ
ከንቱ ነፍሴ ያስብሻል በሰመመን
ልጅሽን የጠረጠረ ባንቺ የተዘጋ ማመን::

ኦ ማርያም
ናፍቆት የመላዕክት
ኦ ማርያም
የአዳም ምልክት

ማክሰኞ
ብልህ ነው እግዜሩ ብቻ ሁሌ ጥሩት
በእናት ይመልሳል ልጅ ቢጠረጥሩት::

ኦ ማርያም
መነሳት በቅድስና
ኦ ማርያም
እንበለ ሙስና::

ረዕቡ
እንደሚከተለው የክፉ ቀን ወጥመድ
ከቀጭን ሽቦ ላይ ፈርቶ እንደሚራመድ
እንደዚያ ሰው አለሁ::

ኦ ማርያም
ፀጋ ትምክህቱ
ኦ ማርያም
ሚካኤል እህቱ::

ሐሙስ
እንደዚያ ሰው አለሁ
ጨለማ ባቅሙ ደፍሮ ሚያስጨንቀኝ
መቀነትሽ ታጥቆ ማንስ ባጠመቀኝ?

ኦ ማርያም
ብሳሳት
ነፍሴን ነፍስሽ ታንሳት::
ኦ ድንግል ሆይ
ማርያምን ብረሳት
ነፍሴን ቀኜ ትርሳት::

አርብ(ስቅላት)
አትሂጅ ትተሽኝ አኑሪኝ በግርግም
ግድ ሆኖብኝ እንጂ መኖር አልፈልግም ::
ግድ ሆኖብኝ እንጂ የምመላለሰው
ግድ ሆኖብኝ እንጂ አፈር የምልሰው
ያነጫንጨኛል
የእናቱን መዳፍ ከእጁ እንደቀሙት
ልረፍና ጥሪኝ ከጥላሽ ስር ልሙት::

ቅዳሜ
ፍቅርሽ የለው ጠረፍ
መንገዴ ይቅናና ጥሪኝ ልቤ ይረፍ::

እሁድ
ደከመኝ እኮ ጌታዬ ደከመኝ እኮ የኔ አምላክ
ወይ እንደሰው አይደለሁ? ወይም እንደመልአክ?
ደከመኝ እኮ ማርያም - ደከመኝ እኮ እማምላክ

ደከመኝ እኮ
@WAS143
@WAS143
1.1K viewsWasye, 14:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 21:30:29 የዚህ ቤት ባለቤት ፥ ጥሩነሽ ዲባባ

(በእውቀቱ ስዩም)

የጠዋት እቅልፍን ከነፍሴ በላይ እወዳለሁ፤ጫጫታ እጠየፋለሁ፤ አንዳንዴ መላ ከተማውን “ ሳይለንት ሞድ “ ላይ ማድረግ ቢቻል እንዴት አሪፍ ነበር ብየ እመኛለሁ፤ የጥንት የጎጃም ደብተራዎች የነጋሪት ድምጽ የሚዘጋ ድግምት ነበራቸው ይባላል፤ በሚቀጥለው አገር ቤት ስሄድ የዚህን ምስጢር ማጣራት አለብኝ ፤
ዛሬ ጠዋት ፥ ከበድ ያለ የትርምስና የጫጫታ ደምጽ ቀሰቀሰኝ፤
ካልጋየ ላይ እየተቅመደመድሁ ተነስቼ ፤ እየተራገምኩ በሩን ከፈትኩት:
:
አምስት ጩጨዎች ናቸው፤ ከቁመታቸው እሚበላልጥ ዱላ ይዘዋል፤ እያንዳንዱ ዱላ ጫፉ ሁለት ሶስት ቆርኪ ስለተንጠለጠለለት፥ በረንዳየን በወቀረው ቁጥር ባንዴ የከበሮና የጽናጽል ድምጽ ያወጣል ፤ ዋናው አስጨፋሪ ልጅ ከሌሎች ልጆች በውፍረትም በቁመትም የሚብልጥ መዛጊያ የሚያክል ዱላ ይዟል፡: የዱላ አያያዛቸው ፥ከጭፈራው ጎን ለጎን ህብረተሰቡን የማስቦካት አላማ እንዳላቸው ያሳብቃል፤
“ መጠናል ባመቱ
አረ እንደምን ሰነበቱ”
ሲል ጀመረ ባለመዛጊያው፥
አቡሽ! የዛሬ አመት እዚህ አገር አልነበርኩም፤ ጭፈራውን ለምን በቀደዳ ትጀምረዋለህ? ነውር አይደለም እንዴ?
ጩጨዎቹ ግሳጼየን ከመ-ጤፍ ሳይቆጥሩ ሆታውን ተያያዙት ፤ ፤ አንደኛው ልጅ አይናፋር ብጤ ነው ፤ ሆታውን አይቀበልም፤ ዝምታውን ለማካካስ በረንዳየን በዱላው በሀይል ይወቅጠዋል፤

“እዚያ ማዶ !
ሆ !
አንድ አበባ !
ሆ !
እዚህ ማዶ አንድ አበባ!

የዚህ ቤት ጌታ
ሆ!
ጥሩነሽ ዲባባ”
አለ አስጨፋሪው፤

“ እኔ የቤቱ ተከራይ ነኝ ፤ ቢሆንም፤ ሙገሳውን ለባለቤቱ አስተላልፋለሁ” አልኩ፤
አስጨፋሪው በቃሉ የያዘው ጭፈራ ሲያልቅበት ፤ ከኪሱ ቢልቦርድ እሚያክል ወረቀት አወጣ፤
“ በቃ! በቃ! እንኩዋን አደረሳችሁ፤ ዛሬ ኪሴ ውስጥ ገንዘብ ስለሌለ በሚቀጥለው አመት ተመለሱ “ ብየ ልገባ ስል፤ አስጨፋሪው ፤
“ በሞባይል ባንክ ትራንስፈር ልታረግልን ትችላለህ” አለኝ
ትውልዱን እየተራገምኩ፥ ወደ ቤት ገባሁና ተመልሼ ወጣሁ፤ አስጨፋሪው የሰጠሁትን አስር ብር አገላብጦ በቅሬታ አይቶ ወደ ኪሱ ከጨመረ በሁዋላ ተከታዮቹን እየነዳ መውረድ ሲጀምር “ እግረመንገዳችሁን ይቺን ይዛችሁልኝ ውረዱ “ አልሁና በረንዳየ ጥግ ላይ በግብዳ ብጫ ፌስታል ቁዋጥሬ ያስቀመጥኩትን ቆሻሻ ብድግ አድርጌ አቀበልኩዋቸው ፤

ሁለተኛውን ደረጃ ከወረዱ በሁዋላ አስጨፋሪው ቀና ብሎ እያየኝ እንዲህ ሲል ሰማሁት “

“ የወፍ ፋፋ የወፍ ፋፋ
አንተ ሶየ ተነፋ “

ወደ ምኝታቤት ተመልሼ አልጋየ ላይ ስወጣ ፤ ሁለተኛው ዙር የጩጨ ባንድ በረንዳየን መውቀጥ ጀምሯል፤
@WAS143
@WAS143
1.5K viewsWasye, 18:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-19 00:38:29 ጦቢያ የግጥም መድብል pinned «ከ“ሆያ-ሆዬ” ጎትቶ “አንቺ ሆዬ” ፡ ያወረሰኝ ፍቅርሽ ነው ያጎረመሰኝ፤ ጢም ካፊያ ካገጬ ብጉር ዶፍ ከጉንጬ የፈላ ያጥለቀለቀኝ ሽክር ድምጽ ደርሶ ያነቀኝ ጨርቄን አስጥሎ ያሞቀኝ ፍቅርሽ ነው ማደጌን ያሳወቀኝ። አስታውሽው ስንተዋወቅ...ከርሻችን ስንቀራረም... ከልብሴ ስታላቅቂኝ... ጉያዬ ባዶ አልነበረም? ሳገኝሽ እንደ መስከረም፤ ለመለምኩ መለመላዬን ፍቅርሽ አስጌጠው ጉያዬን ለገላሽ መረማመጃ ወረሰኝ…»
21:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-17 22:44:49 የሌት ማሕሌት
(በእውቀቱ ስዩም)

ትንሽ ቆየት ብሎ ፥ ኮረንቲው ይጠፋል
እሱን ተከትሎ፥ደምኖ ያካፋል
ከናፍቆትሽ በቀር፥ ሁሉ ነገር ያልፋል ::
አሁን መብራት ጠፋ ፥ ተረኛ ነን አይደል
ቁና ይዠ ቀረብሁ፥ ጨለማ ሲታደል ፤
እያገላበጠ ብቻነት አመሰኝ፥
“ ዝናቡ እየጣለ ጋራ ጋራውን
ጎርፍ ያመጣሽ ‘ንደሁ ልጠብቅ ጎርፉን “
የሚል እንጉርጉሮ፥ በድንገት ታወሰኝ ::
ግን ይሄ ትውስታ
አራራይ ትዝታ
ለቆሰለው ልቤ፥ መዳኒት አልሆነም
ያባቶቼ ዘፈን፤ ለኔ አልተዘፈነም፤

ማዶ ዝናብ ዘንቧል፤
ዶፉን ተከናንቧል-
-እንጦጦ-ዲልዲላ
በገፈጅ ይመስል ፥ቀበናም ቢሞላ
ምንም አያመጣም፤ ከ’ድፍ ውሀ ሌላ
እሳት ነው ፍጥረትሽ፥ ከውሃ ጋ አትኖሪም
አንቺ መብረቅ እንጂ፥ ጎርፍ አትሳፈሪም::
( አዳምኤል)

@WAS143
@WAS143
2.6K viewsWasye, 19:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 23:19:19
My Letesenbet
2.4K viewsWasye, 20:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 08:37:53 የማለዳ እንጉርጉሮ
(በእውቀቱ ስዩም)
አንዳንዴ ደግሞ ጎህ ቀዶ
አብሮኝ ያደረው ደወል ፥ ከራስጌየ ተጠምዶ
ከወፍ ቀድሞ ሲያመጣልኝ፥ ነግቶብሀል የሚል መርዶ
ብትት ብየ ደንብሬ፥
ግማሽ ፊቴን፥ ትራሴ ውስጥ ቀብሬ
“ እኮ ዛሬም እንደ ወትሮ
ካውቶቢስ ወደ ቢሮ
ከኬላ ወደ ኬላ
ዛሬም በግንባሬ ወዝ ልበላ
እሺ ከዚያስ በሁዋላ
እያልሁ ስሞግት ልቤን፥ መልሱን አያመለከትተኝ
ይሄን ያህል ነው የታከተኝ።

ጉዞየ ካዋላጅ እቅፍ፥ እስከ ገናዦች አልጋ
ባራት እግር ተጀምሮ፤ ባራት ሰው ሸክም እስኪዘጋ
መንገዱ መንገድ እየሳበ
ትንንሹ ዳገትም፤ ለትልቁ እያስረከበ
እንደ ሐረግ ስጎተት፥ እንደ ጥንቸል ስፈጥን፥
ምን ሽልማት ታሰበልኝ ?” ይህ ልፋቴን የሚመጥን፥
እያልሁኝ ሳውጠነጥን ፥

አንዳንዴ ደግሞ ሲመረኝ፥
እንደ ለማዳ ፈረስ ፥ ሞትን በፉጨት መጥራት ሲያምረኝ፥
ዛፉን የተቀማ አሞራ
በኮረንቲ ምሶሶ ላይ፥ ቤቱን ባዲስ መልክ ሲሰራ
ማሯን የተዘረፈች ንብ፥ በያበባው ስትሰማራ
አይና
እንዲህ እንዲህ እላለሁኝ፤ ራሴን በራስ ሳጽናና
‘ ሺህ ጊዜ ብትራቀቅ፥ ቃላት መርጠህ ብትገጥም
ከዚህ አሞራ አታንስም፥ ከዚች ንብም አትበልጥም
ተፈጥሮ ትግልን እንጂ፥ የድል ዋስትናን አትሰጥም’’
ቻለው!
@WAS143
@WAS143
2.9K viewsWasye, 05:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-30 11:17:24 የቀበሮ ፀሎት
(ታገል ሰይፉ)
------
እባክህ አምላኬ- ብትሬን ቀባና
እኔም ልወዝወዘው-የሙሴን ጎዳና
ያላንዳች ፍርሃት-ያለምንም ችግር
ባህሩን ከፍዬ- ህዝቤን እንዳሻግር፡፡
*
አቤት የኔ ጌታ ይህም አያረካም
በቃልህ ታምኜ -ከሆንኩልህ መልካም
ለእኔም ፍቀድልኝ-ያብራምን ምልክት
ከምድር አሸዋ-ዘሬ እንዲበረክት፡፡
*
አቤቱ ምን ልሁን-ይህም አልጠቀመኝ
እስቲ እንደ ዮናስ-ህዝብ ፊት አቁመኝ
*
ትንቢቴን ሰምቶልኝ-ሀገር ይተራመስ
ሰው እህል ይጡም-ከብቱም ሳር አይቅመስ፡፡
ይህም አያረካም-ይልቅ እንደዳዊት
አንተን በሚፈራ-ብዙ ሺህ ሠራዊት
ዙፋኔ ተከቦ-በደስታ እንዳመልክህ
የዚህን ሰው ኮከብ -አውጣልኝ እባክህ
*
አደራህን ታዲያ- ጭንቅ አትወድም ነፍሴ
ልመናዬን ሰምተህ-ካደረግከኝ ሙሴ
መከራውን ማረኝ-ያርባ ዓመት ስደቱን
በሲና በረሃ-መራብ መጠማቱን፡፡
*
ነቢዩ ዮናስን -አርገህም ስትፈጥረኝ
የባህሩን ፍዳ- ያሳውን ሆድ ማረኝ፡፡
*
አብረሃምን ሆኜም-በደስታ ሳመልክህ
ልጅህን እረደው-አትበለኝ እባክህ፡፡
***
የዲዊትም ኮከብ-በኔ ላይ ሲወጣ
እባክህ አምላኬ -ጎልያድ አይምጣ፡፡
@WAS143
@WAS143
2.8K viewsWasye, 08:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-25 21:20:22 ከ“ሆያ-ሆዬ” ጎትቶ
“አንቺ ሆዬ” ፡ ያወረሰኝ
ፍቅርሽ ነው ያጎረመሰኝ፤

ጢም ካፊያ ካገጬ
ብጉር ዶፍ ከጉንጬ
የፈላ ያጥለቀለቀኝ
ሽክር ድምጽ ደርሶ ያነቀኝ
ጨርቄን አስጥሎ ያሞቀኝ
ፍቅርሽ ነው ማደጌን ያሳወቀኝ።

አስታውሽው ስንተዋወቅ...ከርሻችን ስንቀራረም...
ከልብሴ ስታላቅቂኝ... ጉያዬ ባዶ አልነበረም?
ሳገኝሽ እንደ መስከረም፤
ለመለምኩ መለመላዬን
ፍቅርሽ አስጌጠው ጉያዬን
ለገላሽ መረማመጃ
ወረሰኝ ጥቁር ስጋጃ
ለጉያሽ የክብር ንጣፍ
ለበስኩኝ የጠጉር ምንጣፍ።
ሁለት ወር እንዳላለፈው፡ ፆታውን እንዳልለየ ሽል
ሁለመናዬ ውሽልሽል
ነበርኩኝ ባንቺ ሳልገኝ
ፍቅርሽ ነው ወንድ ያደረገኝ።

ከቴዘር ከኳስ ነጥሎ ፡ ኳሴን አስተዋወቀኝ
ብዮቼን ጉርጌ አስቀብሮ፥ ነበልባል ጉድጓድ ጠበቀኝ።
ጡት እንኳ...አቃቤ ወተት ፥ ፍም ሆነ...ዘገንኩት በእጄ
እሰይ...!
ልጅነት የጣልኩበትን ፡ ለማደግ ማንሳቴ በጀ።

ሰም ንክር ሸማ ገላዬ፡ ጧፍ ሆነ ተንቀለቀለ
ነፍስሽ ከነፍሴ ተዘራች፡ ስጋዬ ውስጥሽ በቀለ
እኔ ወደኔ ፈሰስኩኝ፡ ፍጥረቴ ተቀላቀለ።
“አይ የልጅ ነገር!” እስከምል ፡ ያላንቺ ራሴን ስቃኝ...
ከጭቃ ቡኮዬ ነጥቆ፡ ወደ ትንፋሽሽ ያነቃኝ
ፍቅርሽ ነው ላ´ዳም ያበቃኝ።
(ረድኤት አሰፋ)
@WAS143
@WAS143
2.8K viewsWasye, 18:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-06 18:25:14 ልረሳሽ እየጣርሁ ነው
(በእውቀቱ ስዩም)
በጣራው ላይ ሲረማመድ፥ የዝናቡ ልዝብ ኮቴ
መጋረጃው ሲውለበለብ፥ ሰንደቅ ሆኖ ለመስኮቴ
ዋርካው በቅጠል ጽዋ
ውሀ ሲያቁር ከሕዋ
የምድርን ጉሮሮ ሊያርስ
መሬት ፍጥረትን ስትፀንስ
በዚህ ሁሉ ጸጋ መሀል፥ ያንቺን መሄድ ስተምነው
ኢምንት ነው፥ ምንም ነው
ልረሳሽ እየጣርሁ ነው::

መጣ፥ መጣ ፥ መጣ ፥ የዝናቡ ኮቴ አየለ
ክረምት የፍጥረት መሲሕ፥ በቀጠሮው ከተፍ አለ
ስሱ የጉም አይነርግብ፥ ውብ ገጽሽን ሸፋፈነው
የርጥብ አፈር ፥ ርጥብ ሽታ፥ ውብ ሽቶሽን አዳፈነው
ልረሳሽ እጣርሁ ነው ::

የዝናቡ ኮቴ ይደምቃል
እንደ ብስል ሾላ ፍሬ ፥ አሮጌው ሰማይ ይወድቃል
አዲስ ሰማይ ይነቃል፥
እንኳንስ የግርሽ ኮቴ ፥ ጎዳናሽም ታጥቦ ያልቃል
ልረሳሽ እየጣርኩ ነው ።

(የማለዳ ድባብ)
@WAS143
@WAS143
3.3K viewsWasye, 15:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ