2022-10-03 21:07:37
የኢትዮጵያና ህንድ አጋርነት በተለያዩ ዘርፎች ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገለጸ
መስከረም 23/2015 (ዋልታ) የኢትዮጵያና ህንድ አጋርነት በኢንቨስትመንት፣ ንግድ፣ ቴክኖሎጂና ትምህርት ዘርፎች ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገለጸ።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የመካከለኛው ምሥራቅ፣ ኤስያ እና ፓስፊክ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄነራል አምባሳደር ገበየሁ ጋንጋ ከህንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የምስራቅና ደቡባዊ አፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጀነራል አምባሳደር ቡኒት ኩንዳል ጋር ተወያይተዋል።
አምባሳደር ገበየሁ ጋንጋ የህንድ እና የኢትዮጵያ ታሪካዊ ዘመናትን ያስቆጠረው ግንኙነት በኢኮኖሚና በባህላዊ መስኮች የቆየ ወዳጅነት እንደነበር አስታውሰዋል፡፡
ይህ የሁለትዮሽ ግንኙነት ዛሬ ላይ ዘርፈ ብዙ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ተጠናክሮ መቀጠሉንም ገልጸዋል።
በቅርቡ የኢትዮጵያ እና የህንድ የምክክር ፎረም በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ ጠቁመው በህዝብ ለህዝብ ግንኘነት፣ በባለብዙ ወገን ግንኘነት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይም በትብብር እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል።
አምባሳደር ቡኒት ኩንዳል በበኩላቸው የሁለትዮሽ ግንኙነቱን ይበልጥ ለማሳደግ በኢንቨስትመንት፣ በንግድና በቴክኖሎጂ እንዲሁም በትምህርት ዘርፎች ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ እንደመሆኗ እና በምስራቅ አፍሪካ ያላትን ተፅዕኖ ፈጣሪነት በመጠቀም በእድገት እና በልማት የትብብር ዘርፎች በጋራ እንሰራለን ማለታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።
ለፈጣን መረጃዎች:-
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth1
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth1
አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን!
1.2K views18:07