Get Mystery Box with random crypto!

WALTA_TV_ETH 🔉

የቴሌግራም ቻናል አርማ waltatveth1 — WALTA_TV_ETH 🔉 W
የቴሌግራም ቻናል አርማ waltatveth1 — WALTA_TV_ETH 🔉
የሰርጥ አድራሻ: @waltatveth1
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 30.95K
የሰርጥ መግለጫ

This is Walta Media and Communication Corporate’s official Telegram channel.
For more updates please visit https://www.facebook.com/wmcc https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-10-12 13:17:24
በገንዘብ ሚኒስትሩ የተመራ ልዑካን ቡድን ከዓለም ባንክ የምሥራቅና ደቡባዊ አፍሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ጋር ተወያየ
በገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ የተመራው የኢትዮጵያ የልዑካን ቡድን ከዓለም ባንክ የምሥራቅና ደቡባዊ አፍሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ቪክቶሪያ ክዋክዋ ጋር ተወያየ።

በዓለም ባንክና የዓለም የገንዘብ ድርጅት ዓመታዊ ስብሰባ ላይ እየተካፈለ የሚገኘው የኢትዮጵያ የልዑካን ቡድን በአሜሪካ ከኢፌዲሪ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ስለሺ በቀለ ጋር በመሆን ከዓለም ባንክ የምሥራቅና ደቡባዊ አፍሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ቪክቶሪያ ክዋክዋ እንዲሁም ከባንኩ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ዑስማን ዲዮን ጋር በመገናኘት ውይይት አድርጓል፡፡

ውይይቶቹ በባንኩ የኢትዮጵያ አገራዊ ፕሮግራም፣ የቅድሚያ ትኩረት መስኮች እንዲሁም ወቅታዊ የልማት ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ ባንኩ በሚያደርገው ድጋፍ ላይ ያተኮረ እንደነበር ተገልጿል። 

በውይይቶቹ ወቅት የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ ኢትዮጵያ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ያጋጠሟትን ዘርፈ-ብዙ ተግዳሮቶች ለመቋቋም እያደረገች ያለውን ጥረት ለመደገፍ የዓለም ባንክ ላሳየው ቁርጠኝነት ምስጋናቸውን ገልጸዋል፡፡

በኢትዮጵያ የቅድሚያ ትኩረት የምትሰጣቸውን የልማት ፍላጎቶች በዝርዝር ያቀረቡት ሚኒስትሩ ወቅታዊ የሰብዓዊ ድጋፍ እና የረዥም ጊዜ የልማት ድጋፍን ማመጣጠን አስፈላጊ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በዚህ መሠረት በድርቅና ግጭት ምክንያት የተፈጠረውን የምግብ እጥረት በመቅረፍ ህይወት ለማዳን የሚያግዝ ሰብዓዊ ድጋፍ ያለጥርጥር አስፈላጊ ሆኖ፣ የዚህ ተግዳሮት መሠረት የሆኑ ችግሮችን ለመቅረፍ የሚረዳ የረዥም ጊዜ የልማት ድጋፍ ስወሳኝ መሆኑንና ባለፉት ጥቂት ዓመታት የተገኙ የልማት ውጤቶችን ቀጣይነት ማረጋገጥ ተገቢ መሆኑን አጽንዖት ሰጥተዋል፡፡ 
ለፈጣን መረጃዎች:-
t.me/WALTATVEth1
1.5K views10:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-12 13:17:23
"አፍሪካ ሰለብሬትስ" የተሰኘ መርኃ ግብር ሊካሄድ ነው

ጥቅምት 2/2015 (ዋልታ) "አፍሪካ ሰለብሬትስ" የተሰኘ የአፍሪካን ልዩነት በአንድነት ውስጥ ለማክበር ያለመ መርኃ ግብር ሊካሄድ ነው።

መርኃ ግብሩ የአፍሪካን ባህላዊ ቅርሶች ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት ለማዋል እና የአፍሪካን የውስጥ ንግድ እና ቱሪዝምን ለማስተዋወቅ ያለመ ነው ተብሏል፡፡

መርኃ ግብሩን ሌጀንደሪ ጎልድ ኤቨንት ኦርጋናይዘር ከአፍሪካ ህብረት፣ ከኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ከንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር እና ከብሪቲሽ ካውንስል ጋር በመተባበር እንደሚያዘጋጀው ተጠቁሟል።

መርኃ ግብሩ ከጥቅምት 9 እስከ 11/215 ዓ.ም በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ የሚካሄድ ይሆናል፡፡

በእለቱም የተለያዩ አፍሪካዊ ልብሶች፤ ባህላዊ ምግቦች እንደሚቀርቡ እና ከተለያዩ ሀገራት የመጡ አፍሪካዊያን የሙዚቃ ስራቸውን እንደሚያቀርቡ እንዲሁም የአርት ኤግዚቢሽን እንደሚኖር ተገልጿል።

በተጨማሪም አፍሪካዊያንን እርስ በእርስ በቢዝነስ ለማስተሳሰር አፍሪካ ቶክስ ቢዝነስ የተሰኘ የውይይት መድረክ እና ኢንቨስትመንት ፎረም መድረክ ይካሄዳል ተብሏል።

ለፈጣን መረጃዎች:-
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth1
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth1

አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን!
1.1K views10:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-12 13:17:23
ሚኒስቴሮቹ የጋራ እቅድ ትግበራ ስምምነት ተፈራረሙ

ጥቅምት 2/2015 (ዋልታ) የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እና የግብርና ሚኒስቴር በቅንጅት ለሚሰሯቸው ስራዎች የጋራ እቅድ ትግበራ ስምምነት ተፈራረሙ።

የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል የግብርናውን ዘርፍ በቴክኖሎጂ የተደገፈ ለማድረግ በትኩረት እንሰራለን ብለዋል።

የግብርና ሚኒስትር ኡመር ሁሴን በበኩላቸው ስምምነቱ በግብርናው ሴክተር ያለውን ችግር ለመፍታት የሚያግዝ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

አክለውም ሀገራዊ የሆኑ ፕሮግራሞችን ለመስራት ከአመራር ሰጭነት በተጨማሪ የቴክኒክ ብቃት እጅግ አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡

በግብርናው ዘርፍ የቴክኖሎጂ ምርምር የሚጠቀም እንዲሁም ክህሎትን ያዳበረ ባለሙያ እንዲኖረን ከሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ጋር ያደረግነው የጋራ ስምምነት ትልቅ ፋይዳ እንዳለውም ገልጸዋል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች:-
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth1
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth1

አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን!
1.0K views10:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-12 13:17:23
የሴካፋ ከ17 ዓመት በታች የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታዎች ዛሬ ይደረጋሉ

ጥቅምት 2/2015 (ዋልታ) የሴካፋ ከ17 ዓመት በታች ውድድር ዛሬ ሲቀጥል የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታዎች ይደረጋሉ።

በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት እየተካሄደ የሚገኘው የሴካፋ ከ17 ዓመት በታች ውድድር የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታዎች ሲደረጉ ዩጋንዳ ከሶማሊያ እና ታንዛኒያ ከደቡብ ሱዳን ይጫወታሉ።

በምድብ ሁለት ቀዳሚ ሆና ያጠናቀቀችው ዩጋንዳ ከሶማሊያ ጋር የምታደርገው ጨዋታ ቀን 6 ሰዓት ላይ ይጀምራል።

የምድብ አንድ ቀዳሚ ሆና ያጠናቀቀችው ታንዛኒያ ከደቡብ ሱዳን ጋር ቀን 9 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያካሂዳሉ፡፡

የግማሽ ፍፃሜ ሁለቱም ጨዋታዎች በዋልታ ቴሌቪዥን እንዲሁም በማኅበራዊ ሚዲያ አማራጮች በቀጥታ ሥርጭት የሚተላለፉ ሲሆን እንዲከታተሉ ተጋብዘዋል፡፡

የዛሬውን የሴካፋ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ 6፡00 ላይ ዩጋንዳና ሶማሊያ ይጫወታሉ፡፡ ማን እንደሚያሸንፍ በትክክል የገመቱ ሦስት ተመልካቾቻችንን የሞባይል ካርድ እንሸልማለን፡፡
ግምቶን በአጭር የጽሁፍ መቀበያ አድራሻችን 8970 ላይ በመላክ ይገምቱ! ይሸለሙ::

ለፈጣን መረጃዎች:-
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth1
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth1

አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን!
925 views10:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-12 13:17:23
የኢትዮጵያ ጀማሪ ኩባንያዎች በዱባይ ጂ አይ ቴክስ 2022 እየተሳተፉ ነው

ጥቅምት 2/2015 (ዋልታ) አስር የኢትዮጵያ ጀማሪ ኩባንያዎች በዱባይ ጂ አይ ቴክስ ለመጀመሪያ ጊዜ እየተሳተፉ ነው።

በኢንቬሽንና ቴክኖሊጂ ሚኒስቴር የምርምርና ኢኖቬሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ባይሳ በዳዳ የተመራ የመንግሥት እና ጀማሪ ኩባንያዎች ቡድን በኤክስፖው እየተሳተፈ ነው።

ቡድኑ በጃፓን ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት አስተባባሪነት ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 5 ቀን 2015 ዓ.ም ለሚቆየው የዱባይ ቴክኖሎጂና ጀማሪ ኩባንያዎች ኤክስፖ ለመሳተፍ ነው ያቀናው።

በኤክክፖው ከ170 በላይ ሀገራት የመጡ ታላላቅ ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች እና ጀማሪ ኩባንያዎች ይሳተፋሉ፡፡

በኤክስፖው ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የግብርና፣ የአይ ሲ ቲ እና የዲጂታል፣ ቴክኖሎጂዎችን መሰረት ያደረጉ አስር ጀማሪ ኩባንያዎችን በማሳተፍ ምርትና አገልጎሎታቸውን እንዲያስተዋውቁ እያደረገች ነው፡፡

በዚህም በተለየዩ ዓለም አቀፍ ውድድሮች እንዲሳተፉና ባለሃብቶች ጋር እንዲገናኙ ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል መባሉን የኢንቬሽንና ቴክኖሊጂ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች:-
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth1
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth1

አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን!
886 views10:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-12 13:17:23
በገንዘብ ሚኒስትሩ የተመራ ልዑካን ቡድን ከዓለም ባንክ የምሥራቅና ደቡባዊ አፍሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ጋር ተወያየ

ጥቅምት 2/2015 (ዋልታ) በገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ የተመራው የኢትዮጵያ የልዑካን ቡድን ከዓለም ባንክ የምሥራቅና ደቡባዊ አፍሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ቪክቶሪያ ክዋክዋ ጋር ተወያየ።

በዓለም ባንክና የዓለም የገንዘብ ድርጅት ዓመታዊ ስብሰባ ላይ እየተካፈለ የሚገኘው የኢትዮጵያ የልዑካን ቡድን በአሜሪካ ከኢፌዲሪ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ስለሺ በቀለ ጋር በመሆን ከዓለም ባንክ የምሥራቅና ደቡባዊ አፍሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ቪክቶሪያ ክዋክዋ እንዲሁም ከባንኩ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ዑስማን ዲዮን ጋር በመገናኘት ውይይት አድርጓል፡፡

ውይይቶቹ በባንኩ የኢትዮጵያ አገራዊ ፕሮግራም፣ የቅድሚያ ትኩረት መስኮች እንዲሁም ወቅታዊ የልማት ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ ባንኩ በሚያደርገው ድጋፍ ላይ ያተኮረ እንደነበር ተገልጿል።

በውይይቶቹ ወቅት የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ ኢትዮጵያ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ያጋጠሟትን ዘርፈ-ብዙ ተግዳሮቶች ለመቋቋም እያደረገች ያለውን ጥረት ለመደገፍ የዓለም ባንክ ላሳየው ቁርጠኝነት ምስጋናቸውን ገልጸዋል፡፡

በኢትዮጵያ የቅድሚያ ትኩረት የምትሰጣቸውን የልማት ፍላጎቶች በዝርዝር ያቀረቡት ሚኒስትሩ ወቅታዊ የሰብዓዊ ድጋፍ እና የረዥም ጊዜ የልማት ድጋፍን ማመጣጠን አስፈላጊ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

https://www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate/posts/pfbid0ra6WHrJXCMRWt7pMgL3wEZUNk8VTZLCzc6AGPZLYtW7UMoEhzMUBCH8PmpKTA6gcl

ለፈጣን መረጃዎች:-
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth1
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth1
1.1K views10:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-11 20:24:29
አገልግሎቱ እና የጁቡቲ የመረጃ ተቋም በድንበር አካባቢ የጸጥታና ደኅንነት ጉዳዮች ዙሪያ በጋራ የሚያከናውኗቸውን ስምሪቶች አጠናክረው ለመቀጠል ውይይት አደረጉ

ጥቅምት 1/2015 (ዋልታ) የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት እና የጁቡቲ የመረጃ ተቋም በድንበር አካባቢ የጸጥታና ደኅንነት ጉዳዮች ዙሪያ በጋራ የሚያከናውኗቸውን ስምሪቶች አጠናክረው ለመቀጠል ውይይት አደረጉ።

የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ለዋልታ ቴሌቪዥን በላከው መግለጫ እንዳመለከተው በጅቡቲ የመረጃ ተቋም ዳይሬክተር ጀነራል ሐሰን ሰይድ የተመራ ከሀገሪቱ የጸጥታና ደኅንነት አካላት የተወጣጣ የልዑካን ቡድን በብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ጉብኝት አካሂዷል፡፡

የአገልግሎት መሥሪያ ቤቱ ምክትል ዳይሬክተር ጀነራል ሲሳይ ቶላና ሌሎች የተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች ለልዑካን ቡድኑ አቀባበል ያደረጉለት ሲሆን፤ ከጉብኝት መርሐግበሩ ጎን ለጎን በጁቡቲ የመረጃ ተቋም ዳይሬክተር ጀነራል ሐሰን ሰይድ የተመራው ከሀገሪቱ የጸጥታና የደኅንነት አካላት የተወጣጣ የልዑካን ቡድን እና የኢትዮጵያ አቻ ተቋማት የተካፈሉበት የሁለትዮሽ ውይይት ተካሂዷል፡፡

ሁለቱ ሀገራትም በድንበር እንዲሁም አካባቢ በቀጣናው በሚስተዋሉ የጸጥታና ደኅንነት ጉዳዮች ዙሪያ በጋራ የሚያከናውኗቸውን ስምሪቶች አጠናክረው ለመቀጠል ተስማምተዋል፡፡

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid023xNzjBRv7o34jUXXH2nQR49V8uEgQmynx8vJnkmKj4Bteb83JR8U6K8p3MDhVLbTl&id=100064690148931
ለፈጣን መረጃዎች:-
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth1
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth1

አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን!
924 views17:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-11 20:24:29
የሀገራችንን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር ወጣቶች የአምባሳደርነት ሚናቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ተገለጸ

ጥቅምት 1/2015 (ዋልታ) ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ያላትን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር ወጣቶች የአምባሳደርነት ሚናቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ተናገሩ።

ኢትዮጵያ አፍሪካዊ ወንድማማችነትን የመትከል አረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብርን በምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ከቀናት በኋላ ታካሂዳለች።

በተለያዩ የጎረቤት ሀገራት ለአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርኃ ግብር ለሚሄዱ ወጣቶች ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በተገኙበት ሽኝት ተደርጎላቸዋል።

ለወጣቶቹ መልዕክት ያስተላለፉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ በተለያዩ የዓለማችን ክስተቶች ቀዳሚ እንደነበረች አስታውሰዋል።

በተለይ በተለያዩ ሀገራት በሰላም ማስከበር ዘርፍ ጠንካራ ስራዎች ማከናወኗን ገለጸው የአረንጓዴ አሻራ የወንድማማችነት መርኃ ግብርም የኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ እንቅስቃሴ አንዱ አካል መሆኑን ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ ጥንካሬዋና እድገቷ የሚወሰነው በወጣቶች በመሆኑ ሁሉም የራሱን ኃላፊነት በሚገባ በመወጣት አሻራውን ማስቀመጥ እንዳለበት አሳስበዋል ሲል የዘገበው ኢብኮ ነው።

"ፕላንት አፍሪካን ፍራተርኒቲ" ዝግጅት ኢትዮጵያ የጀመረችውንና በስኬት እያከናወናችው ያለውን የአረንጓዴ አሻራ ወደ ጎረቤት ሀገራትም ማስፋፋት አላማውን ያደረገ መርኃ ግብር ነው።
ለፈጣን መረጃዎች:-
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth1
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth1

አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን!
705 views17:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-11 20:24:29
ከ15 ሺሕ በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የታዳሽ ኃይል ፕሮጀክት ይፋ ሆነ

ጥቅምት 1/2015 (ዋልታ) ከ20 ሚሊዮን ዶላር በላይ በሆነ ወጪ በግብርና ስራ የሚተዳደሩ ከ15 ሺሕ በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የታዳሽ ኃይል ፕሮጀክት ይፋ መደረጉ ተገለጸ።

በኢትዮጵያ የግሎባል ኢነርጂ አሊያንስ ለሰዎችና ለሕዋ የመጀመሪያ የሆነው ተደራሽ ታዳሽ ኃይል ለግብርና ስራዎች ፕሮጀክት ማስጀመሪያ መርኃ ግብር ተካሂዷል።

በመርኃ ግብሩ ማስጀመሪያ ላይ ንግግር ያደረጉት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሀብታሙ ኢተፋ (ፒኤችዲ) የኤሌክትሪክ ኃይል ተደራሽነት በጤና፣ በትምህርት፣ በመጠጥ ውሃ አቅርቦት፣ በኃይል ተጠቃሚነት፣ ለኢንዱስትሪ ማስፋፋት እና የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል ወሳኝነት አለው ብለዋል።

ከ50 በመቶ በላይ ዜጎች የኃይል ተጠቃሚ አይደሉም ያሉት ሚኒስትሩ ችግሩን ለመፍታት የብሔራዊ ኤሌክትሪፊኬሽን ፕሮግራም ተቀርጾ በ2030 የኤሌክትሪክ ኃይል በሀገር አቀፍ ደረጃ ለማዳረስ እየተተገበረ መሆኑን ገልጸዋል።

ተደራሽ ታዳሽ ኃይል ለግብርና ፕሮጀክት የታዳሽ ኃይል ላይ መሰረት አድርጎ የተቀረጸ ፕሮጀክት ሲሆን ከብሄራዊ ኤሌክትሪፊኬሽን ፕሮግራም ጋር አብሮ የሚሄድ ነው ብለዋል።

ተደራሽ ታዳሽ ኃይል ለግብርና ስራዎች ፕሮጀክት በሙከራ ደረጃ በኦሮሚያ ክልል በአራት ሳይቶች፣ በአማራ ክልል በሦስት ሳይቶች፣ በሲዳማ ክልል በአንድ ሳይት እንዲሁም በደቡብ ክልል በአንድ ሳይት የሚተገበር ይሆናል ነው የተባለው።

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid02PugLsciYDEWbN5hGoRmhHJE6r9QQCq5DwD8ZYY7to6Wjtg3xj3or8qWkLkGLA322l&id=100064690148931
ለፈጣን መረጃዎች:-
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth1
609 views17:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-11 20:24:29
በፀጉር ንቅለ ተከላ ስራ ከተሰማሩ ተቋማት ለሁለቱ ብቻ ፈቃድ መስጠቱን ባለስልጣኑ አስታወቀ

ጥቅምት 1/2015 (ዋልታ) በፀጉር ንቅለ ተከላ ስራ ከተሰማሩ ተቋማት ለሁለት ተቋማት ብቻ ፈቃድ መሰጠቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን አስታወቀ።

የባለስልጣኑ የጤና ተቋማት ብቃት ማረጋገጥና ቁጥጥር ዳይሬክተር በድሪያ ሁሴን በህጋዊነት የሚታወቁት መርሺያ ሰርጂካል ሴንተር እና ሀሌሉያ ሆስፒታል ብቻ ናቸው ብለዋል።

ከጤና ጉዳት አንፃር በማህበራዊ ሚዲያ ማስታወቂያ ከሚነገርላቸው ህገወጦች ህብረተሰቡ እንዲጠነቀቅ ጥሪ አቅርበው በህገወጦቹ ላይ ክትትል ተደርጎ እርምጃ እና እርምት ይወሰዳል ብለዋል ዳይሬክተሯ።

አሁን ላይ ባለስልጣኑ ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመሆን ዘርፉ ላይ የተጠናከረ ደረጃና መመሪያ እያዘጋጀበት ይገኛል ማለታቸውን የዘገበው ኢብኮ ነው።

ሀሰተኛና እውቅና የሌላቸው ተቋማትን ሳያጣሩ ማስታወቂያ የሚያሰራጩ አካላትም ከድርጊታቸው ሊቆጠቡ ይገባል ብለዋል።

ባለስልጣኑ ከመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ጋር በመሆን የማስታወቂያ ህጋዊነት እና ማረጋገጫ ሰነድ እያሰናዳ መሆኑም ተገልጿል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች:-
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth1
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth1

አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን!
586 views17:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ