Get Mystery Box with random crypto!

አል ሂላል ለኪሊያን ምባፔ ያቀረበዉን ከፍተኛ ዋጋ የዝዉዉር ጥያቄ ፒኤስጂ መቀበሉ ተገለጸ ሐምሌ | AddisWalta - AW

አል ሂላል ለኪሊያን ምባፔ ያቀረበዉን ከፍተኛ ዋጋ የዝዉዉር ጥያቄ ፒኤስጂ መቀበሉ ተገለጸ

ሐምሌ 17/2015 (ዋልታ) የሳውዲዉ ቡድን አል ሂላል የፓሪስ ሴንት ዠርሜይን ፈረንሳዊ ኮከብ ኪሊያን ምባፔን ለማስፈረም ያቀረበውን ክብረወሰን የሆነ 300 ሚሊዮን ዩሮ የዝውውር ዋጋ ፒኤስጂ መቀበሉ ተገልጿል፡፡

በእግር ኳስ ታሪክ ዉዱን የ300 ሚሊዮን ዩሮ ክፍያ ለመፈፀም ጥያቄ አቅርበዉ በፒኤስጂ ተቀባይነት አግኝቷልም ተብሏል።

እስካሁን በምባፔ እና በአል-ሂላል መካከል ምንም አይነት ድርድር ያልተደረገ ሲሆን ባለቤት ክለቡ ግን ተጫዋቹ ኮንትራቱን ካላራዘመ ለመሸጥ መወሰኑም ነው የተነገረው፡፡

በሀብታሙ ገደቤ