Get Mystery Box with random crypto!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አዲስ እና ጠንካራ ዓለም አቀፍ የግብርና የፋይናንስ ሞዴል እንደሚያ | AddisWalta - AW

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አዲስ እና ጠንካራ ዓለም አቀፍ የግብርና የፋይናንስ ሞዴል እንደሚያስፈልግ ገለጹ

ሐምሌ 17/2015 (ዋልታ)አዲስ እና ጠንካራ ዓለም አቀፍ የግብርና የፋይናንስ ሞዴል መኖር አስፈላጊ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ።

በሁለተኛው የተባበሩት መንግስታት የምግብ ስርዓት ጉባኤ ወቅት ባደረጉት ንግግር ለምግብ ዋስትና፣ ለስራ እድል ፈጠራ ብሎም ለአጠቃላይ የኢኮኖሚ እድገት አዲስ እና ጠንካራ ዓለም አቀፍ የግብርና የፋይናንስ ሞዴል አስፈላጊ መሆኑን በአፅኖት ተናግረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ የትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት “ኢትዮጵያ ውስጥ ከፖሊሲ እና ስትራቴጂዎች ባለፈ የግብርና ልማትን ለማጎልበት አቅምን ማሳደግ፣ በምግብ ራስን መቻልን ማረጋገጥ ብሎም የአየር ንብረት ለውጥን ለመዋጋት ዋና ዋና ግቦችን ይዘን በርካታ ጅምር ስራዎችን እየሰራን ነው” ብለዋል።

ሁለተኛው የተባበሩት መንግስታት የምግብ ስርዓት ጉባኤ ከሐምሌ 17-19 በጣሊያን አዘጋጅነት እየተካሄደ ነው፡፡