Get Mystery Box with random crypto!

በበጀት ዓመቱ ከ6ሺሕ በላይ የሳይበር ጥቃት ሙከራዎች መደረጋቸው  ተገለጸ ሐምሌ 17/2015 (ዋ | AddisWalta - AW

በበጀት ዓመቱ ከ6ሺሕ በላይ የሳይበር ጥቃት ሙከራዎች መደረጋቸው  ተገለጸ

ሐምሌ 17/2015 (ዋልታ) በበጀት ዓመቱ 6ሺሕ 959 የሳይበር ጥቃቶች መደረጋቸውን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር አስታወቋል፡፡

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የ2015 በጀት አመት አፈጻጸምን አስመልክቶ መግለጫ ሠጥቷል።

የአስተዳደሩ ዋና ዳይሬክተር ሠለሞን ሶካ በ2015 የበጀት ዓመት በኢትዮጵያ 6ሺሕ 959 የሣይበር ጥቃት መመዝገቡንና ከዚህ ውስጥ 6ሺሕ 768ቱ የጥቃት ሙከራዎች መሆናቸውን ገልፀው የተቀሩት 191 ግን የተሣኩ የሳይበር ጥቃት መሆናቸውን ተናግረዋል።
https://www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate/posts/683457737153892?ref=embed_post