Get Mystery Box with random crypto!

ዋልድባ ገዳም

የቴሌግራም ቻናል አርማ waldiba — ዋልድባ ገዳም
የቴሌግራም ቻናል አርማ waldiba — ዋልድባ ገዳም
የሰርጥ አድራሻ: @waldiba
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 5.44K
የሰርጥ መግለጫ

👉 ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ በነገረ መለኮት፣ በነገረ ማርያም፣ በነገረ መስቀል፣ በነገረ ቅዱሳንና በምሥጢራት ላይ፣
👉 ወቅታዊ የቤ/ክ ሁኔታና የቅ/ሲኖዶስ ውሳኔዎች፣
👉 የመንፈሳዊ ጉዞዎች ዓመታዊ መርሐ ግብር...
ለጥያቄዎ
@zeWaldiba_bot
@Gedamewali
@Elmestoagia
👇 YouTube: https://www.youtube.com/channel/UCUBStsekCniQtATyZDdFqQQ

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-07-19 08:36:26
2.7K viewsአንተነህ ውብሸት, 05:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 06:42:53
1.2K viewsእልመስጦአግያ ዘሐዋርያት, 03:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 06:36:55 ★ በየዓመቱ እንደተለመደው የቅዱስ ገብርኤልን በዓለ ንግሥ ምክንያት በማድረግ ስዕለት ሰሚው ቁሉቢ ቅ/ገብርኤል ገዳምን የምንሳለምበት የንግሥ ጉዞ አንጋፋው ማኅበራችን ያዘጋጃል። ዘንድሮም ከሐምሌ 16 - 20 ድረስ በሚኖረን የቁሉቢ ገብርኤል ንግሥ ጉዟችን በሐረርና በጅጅጋ ከተሞች ያሉ ታሪካዊ አብያተ ክርስቲያናትን ተሳልመን ለመመለስ ዝግጅታችንን አጠናቅቀን በምዝገባ ላይ ነን። ስለሆነም ከማኅበራችን ጋር ተጉዘው "በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ" እንዲሉ በአንድ ጉዞ ሌሎች ተጨማሪ ገዳማትና አድባራትንም ትሳለሙ ዘንድ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

ኑ አብረን እንጓዝ!!! ሊሞላ ጥቂት ወንበሮች ብቻ ስለቀሩን ቀድመው ይመዝገቡ።

★★★ ያስተውሉ! ወደ ቁልቢ ከእኛ ጋር ሲጓዙ የግሑሣን በዓት ከሆነው ከቁሉቢ ቅ/ገብርኤል ገዳም በተጨማሪ ታሪካዊዎቹን የሐረር አድባራት ጀጎል መድኃኔዓለምና ቅ/ሥላሴን እንዲሁም በርካታ ኦርቶዶክሳዊያን ክርስቲያኖች ሰማእትነት የተቀበሉባቸውን ጅጅጋ ቅ/ኪዳነ ምሕረትና ቅ/ሚካኤል አብያተ ክርስቲያናትን ይሳለማሉ።

★ ሼር በማድረግ የበዓለ ንግሡ ተካፋይ እንዲሆኑ ፈቃደ እግዚአብሔር ለሆነላቸው ሁሉ የመባረካቸው ምክንያት ይሁኑ።

{#ማሳሰቢያ፦ በቦታው ላይ ያለው ሰላም በአንፃራዊነት ወደ ቀደመ መረጋጋቱ ስለተመለሰ የሀገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስ ብፁዕ አባታችን አቡነ መቃርዮስ ከክልሉ ባለሥልጣናት በመነጋገር ምዕመናን በቦታው ተገኝተን ያለምንም ስጋት ክብረ በዓሉን እንድናከብር በEOTC TV ላይ ጥሪ አድርገዋል። ስለዚህ በፀጥታው ሥጋት ሰበብ ከስዕለት ሰሚው ቁሉቢ ገብርኤል ሊያስቀረን የሚታገለውን ጥንተ ጠላታችን ዲያብሎስን ድል ነሥተን "ተሰማልኝ ስዕለቴ!" እያልን አብረን ለመጓዝ እንነሣ}

#መነሻ፦ ሐምሌ 16 እና 17 #መመለሻ፦ ለሁሉም ሐምሌ 20
√ ሐሜሌ 16 የሚነሣው ጅጅጋና ሐረር ይገባል ድሬዳዋ አይገባም የጉዞ ዋጋ ማረፊያ ቤትን ጨምሮ 1700 ብር
√ ሐምሌ 17 የሚነሣው ድሬደዋ ይገባል ጅጅጋ አይገባም የጉዞ ዋጋ ማረፊያ ቤትን ጨምሮ 1500 ብር
#መነሻ_ቦታዎች፦ ቀጨኔ መድኃኔዓለም፣ አራዳ ቅ/ጊዮርጊስ፣ መስቀል አደባባይ ቅ/እስጢፋኖስ እና መገናኛ

#የምዝገባ_ቦታዎች፦
፩) ቀጨኔ መድኃኔዓለም አካባቢ፦፦
ማትያስ የመኪና ዕቃ መሸጫ፣
ማርሶሊ ፎቶ ቤት፣

፪) አራዳ ጊዮርጊስ አካባቢ
ገኒ የወንዶች ፀጉር ቤት
መሲ ሕትመትና ማስታወቂያ

፫) ባላችሁበት አካባቢ ለመመዝገብ (ትኬት ለመቁረጥ) በሚከተሉት የመምህር አንተነህ ውብሸት የባንክ አካውንቶች በካሽ ወይም በሞባይል ባንኪንግ አስገብታችሁ ደረሰኙን የጉዞው ቀን ይዞ መምጣት ወይንም Screenshot አድርጋችሁ በቴሌግራም ልትልኩልን ትችላላችሁ።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000099794899
አቢሲኒያ ባንክ 73439825
አዋሽ ባንክ 01320104564900

★★★ የማኅበራችንን የጉዞ መርሐ ግብር ከወደዱት ይደውሉልና አብረውን ይጓዙ!!!

★ ይህን የመንፈሳዊ ጉዞ መልዕክት እርሶ በሚጠቀሙበት ድህረገጽ ላይ ሼር በማድረግ ይተባበሩን።

❖ በማኅበራችን የጉዞ መርሐ ግብራት መሳተፍ ከፈለጉ ሳያመነቱ ይደውሉልንና አብረን እንጓዝ!!! እነዚህን ቅዱሳት መካናት ለመሳለም የምትሹ የኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ልጆች ሁሉ ቀድማችሁ ደውሉልንና አብረን በረከት እናግኝ! ለበለጠ መረጃ፦
0901070707 / 0911289877 / 0941960723
#ማኅበረ_ቅዱስ_ፊልጶስ_ወአቡነ_ሳሙኤል_ዘዋልድባ
@negeretewahido

❖ ብዙዎች የበረከቱ ተሳታፊ ይሆኑ ዘንድ ጦማሩን Share, Like, Tag & Comment አድርጉት፤ የቅዱሳት መካናትን የቃልኪዳን በረከት እንዲያገኙ ለሌሎች ምክንያት መሆን በራሱ ልዩ በረከት ያሰጣልና Share & Tag በማድረግ ለወዳጆችዎ ያካፍሉት።
"ገዳምህን የረገጠ" ብቻ ሳይሆን "ገዳምህን ለሌሎች ያሳዬ ...እምርልሃለሁ!" ተብሎ ቃል የተገባላቸው ቅዱሳን እንዳሉን ገድለ አቡነ ዘርዓ ብሩክን ያስታውሱ!!!

በቴሌግራም ይቀላቀሉን
@waldiba
@waldiba
@waldiba

የዩቲዩብ ቻናላችንን « መኮሬታ Mekoreta Tube »ን በሚከተለው ሊንክ ከፍተው Subscribe & Join ያድርጉ።
https://m.youtube.com/channel/UCUBStsekCniQtATyZDdFqQQ
534 viewsእልመስጦአግያ ዘሐዋርያት, edited  03:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 06:36:55 ★ ከ18ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ወዲህ ግን ታሪክ ተለውጦ የአካባቢው ሰላም አስተማማኝ እየሆነ በመምጣቱ በርከት ያሉ አብያተ ክርስቲያናት እየተተከሉ መንፈሳዊ አገልግሎቱና የስብከተ ወንጌል እንቅስቃሴም ውጤታማ እንደነበር የታሪክ መዛግብት ያስረዳሉ። የደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳምም የተተከለው በዚህ ዘመን ነው። ስለ አተካከሉም ሁለት ዓይነት ታሪኮች ይነገራሉ።

፩ኛ ግራኝ አህመድ በወረረና ወደ ሰሜን በገሠገሠ ጊዜ በአንጻሩ ደግሞ በሰሜን አካባቢ ምናልባትም ከደቡብ ጎንደር ታቦታትን፣ ልዩ ልዩ ንዋያተ ቅድሳትን ይዘው የተሰደዱ ካህናት በእግዚአብሔር ፈቃድ ቁልቢ የተባለው ቦታ ይደርሳሉ፤ የካህናቱም ስም፦
1. መልዓከ ገነት መብረቁ፣
2. መምህር የማነ አበበ፣
3. አባ ተከስተ ሥሉስ ይባላሉ።
እነዚህ አባቶች ቁልቢ ገብርኤል ደርሰው ቦታውን ሲጎበኙ ከተነጠፈ ድንጋይ ላይ ጽሑፍ ያገኛሉ። ጽሑፉም ታቦተ ቅዱስ ገብርኤል በስውር ቦታ መቀመጡን፣ ልዩ ልዩ ተአምራት እንደሚፈጸምበት፣ ወደፊትም ታላቅ ቤተ መቅደስ እንደሚሠራ አባ ሌዊ ታቦቱን ወደ እዚህ ቦታ እንዴት እንዳመጡት የሚገልጽ ነበር። እነርሱም ይህንን ታሪክ ይዘውት በነበረው መጽሐፈ ቀሌምንጦስ ኅደጉ ላይ (footnote) ጻፉት። ከቁሉቢ ሲመለሱም መጽሐፉን በዝዋይ ደሴት አስቀመጡት።

★ የሐረር ገዥ የነበሩት ልዑል ራስ መኮንን ከዝዋይ ደሴት መጽሐፈ ቀሌምንጦስ አስመጥተው ሲያነብቡ የቅዱስ ገብርኤልን ታሪክ በማግኘታቸው ቤተ ክርስቲያን በስሙ ለመመሥረት ተነሳሱ። ልዑሉ በአካባቢው አየር ንብረት ተማርከው በቦታው ቤት ሠርተው መኖር ጀምረው ነበር። ልዑል ራስ መኰንን ቁልቢ ገብርኤልን ከመትከላቸው በፊት ቦታው የአከባቢው ጎሳዎች የግጭት መነሃርያ ማለትም የአካባቢው ሕዝብ ባለመግባባት የሚዋጋበት ቦታ ነበር።

★ ልዑሉ፦ "በአካባቢው ሰላም ካወረድህ በዚህ ቦታ በስምህ ቤተ ክርስቲያን አሠራለሁ!" ብለው ለቅዱስ ገብርኤል ተሳሉ። ስእለታቸው በመፈጸሙ የቅዱስ ገብርኤል ታቦት የት እንደሚገኝ ሲያፈላልጉ ሰሜን ቡልጋ ውስጥ ከአዠጉጉ ካህናተ ሰማ ጋር አባ ዱባለ የተባሉ ካህን ያስቀመጡት ታቦተ ቅዱስ ገብርኤል መኖሩ ተነገራቸው። ልዑል ራስ መኮንን የካቲት 20 ቀን 1879 ዓ.ም መልእክተኛ ወደ ጠቅላይ ቤተ ክህነት እና ወደ ዓጼ ምኒልከ በመላክ ካስፈቀዱ በኋላ ለአባ ዱባለ መልእክት ላኩባቸው። አባ ዱባለም ታቦተ ቅዱስ ገብርኤልን ከሐረር በተላኩ ካህናት አማካኝነት ለልዑል ራስ መኮንን ላኩ፤ ልዑል ራስ መኰንንም ከነሠራዊቶቻቸው ሸንኮራ ድረስ ሄደው ታቦቱን ተቀበሉ። ካህናቱም ከነሠራዊታቸው ታቦቱን ተሸክመው ጉዞ ጀምረው የካቲት 21 ቀን 1884 ዓ.ም ወደ ቁልቢ ደረሡ።

★ ልዑል ራስ መኮንን ቦታውን በአካባቢው ከነበሩ ባላባቶች በ40 የቀንድ ከብት ገዝተው በ1883 ዓ.ም የተጀመረው የመቃኞ (ጊዜያዊ ማረፊያ) ቤት ሥራው ተሠርቶ ሲጠናቀቅ ሐምሌ 19 ቀን 1884 ዓ.ም ቅዳሴ ቤቱ ለመጀመሪያ ጊዜ እንዲከበር አድርገዋል። በዚሁ ዕለት የዋናው ሕንፃ ቤተክርስቲያን መሠረት ተጥሎ ታኅሣሥ 19፣ 1888 ዓ.ም ሥራው ተጠናቅቆ በግብጻዊው ሊቀ ጳጳስ አቡነ ማቴዎስ ተባርኮ ታቦቱ ገብቷል። ራስ መኰንን መጋቢት 9 ቀን 1889 ዓ.ም ወደ አዲስ አበባ ሲሄዱ እዚህ ቦታ ላይ በድንገት ስለታመሙ በዕለቱ ሥጋወደሙ ተቀብለውበታል።

፪ኛ ልዑል ራስ መኮንን በአካባቢው ቤተ ክርስቲያን ለማሠራት ሲያስቡ ምን ዓይነት ቤተ ክርስቲያን ይተከል የሚለውን ለማወቅ በጾምና በጸሎት በሱባዔ በነበሩበት ወቅት ከአሰቦት ደብረ ወገግ ቅድስት ሥላሴና አባ ሳሙኤል ገዳም ከተሰወሩ ቅዱሳን መካከል አንዱ በመገለጥ "መተከል ያለበት ቅዱስ ገብርኤል መሆኑን ተናግረው ታቦቱም የሚገኘው ከላይ ስሙ በተጠቀሰው ቦታና አባ ዱባለ በተባሉ መነኩሴ ዘንድ እንደሆነ ተናግሮ ተሰወራቸው።" የሚለው ነው።

★ በአጠቃላይም ከላይ የተጠቀሱትን ሁለቱን ስለ ቅዱስ ገብርኤል ታቦት አመጣጥ የሚያወሱ ታሪኮችን ለማያያዝ መጀመሪያ ከአክሱም ወደ ዝዋይ፣ ከዝዋይ ወደ ቁልቢ ዳግመኛም ከቁልቢ እንዴት ወደ ቡልጋ ተመልሶ እንደሄደ የሚተርክ ጽሑፍ ባናገኝም ታቦቱ በስውር (በእግዚአብሔር ጥበብ) ወደ ቡልጋ እንደመጣ ይነገራል፡፡ ኋላ ተመልሶ ከቡልጋ ወደ ቁልቢ በልዑል ራስ መኮንን አማካኝነት እንደመጣ ግን መረጃው ይገልጻል። ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ታቦቱ በቁሉቢ ይገኛል። በመጀመርያ ሲተከል በገጠር ቤተ ክርስቲያን ሥሪት ሲሆን በኋላ ግን በስእለት ሰማኢነቱ በመላ ኢትዮጵያ እየታወቀ ስለ መጣ ደብር ወገዳም ሆኗል፡፡

†★† #ትንቢትና_ተግባር፦
★ ከ1888-1954 ዓ.ም ድረስ በጽድና በዝግባ ከተሰራ ቤተመቅደስ ሲገለገል ቆይቶ ስእለት ሰሚነቱ እየታወቀ፣ ስሙ እየገነነ፣ ተአምራቱ እየበዛ በመምጣቱ፣ የሕዝቡ ቁጥርም በመጨመሩና በጽድና በዝግባ የተሰራው ቤተ መቅደስ አነስተኛ በመሆኑ ሰፊ አገልግሎት ለመስጠት እንዲያስችለው ታስቦ ከስእለት በተገኘው ገንዘብ ከ1954-1957 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ ለዓይናችን ድንቅ ሆኖ የሚታየው ሕንፃ በዘመናዊ ፕላን ተሠርቶ በተገቢው ሁኔታ በመጠናቀቁ ታቦተ ሕጉ ወደ አዲሱ ቤተ መቅደስ በሚገባበት ጊዜ ብፁዕወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ፓትርያርክ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ ንጉሥ ዓጼ ኃይለ ሥላሴና ክቡራን ሚኒስትሮች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ምእመናን ተገኝተዋል።

†★† #ቁሉቢ_ገብርኤል_አሁን †★†
★ በክብረ በዓሉ ሕዝበ ክርስቲያኑ፣ ክርስትናን ያልተቀበሉ የውጪ አገር ዜጎችም ሁሉ ይታደማሉ። ስእለት ያለባቸውም ሆነ ሌሎች ምእመናን ከድሬዳዋ፣ ከሐረር፣ ከአሰበ ተፈሪ ጀምሮ የእግር ጉዞ ያደርጋሉ። በተለይ የሐሮማያ እና የድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የሚያደርጉት የጋራ የእግር ጉዞ በእግርም በመኪናም የሚሄደውን ዓይን ይማርካል። ከ2000 ዓ.ም በፊት በገዳሙ ዙሪያ ሥጋዊ እንቅስቃሴ መብል፣ መጠጥ፣ ጭፈራ እና ስርቆት እንደነበረ በቦታው የተገኘ ሰው የሚያስታውሰው እውነት ነው። አሁን ግን እንዲህ ዓይነት አስነዋሪ ነገር ይቅርና ማንኛውም እንቅስቃሴ ሥርዓት እንዲይዝ ተደርጓል።

★ መንፈሳዊ አገልግሎቱን በተመለከተ፦
በየቀኑ የቅዳሴ ሥርዓት ይከናወናል።
የሠርክ ጉባኤ ይካሄዳል።
ገዳሙ ለጎብኚዎች ሁልጊዜ ክፍት ነው።
የካህናት ስልጠና ይካሄድበታል።
የአብነት መምህራን ይገኛሉ።
በአካባቢው ለሚኖረው ሕዝብ ዘመናዊ ትምህርት ቤት ተሠርቶና መንግስት ተረክቦት አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል። የእግዚአብሔርን ሕዝብ በቀንም በሌሊትም የሚያገለግል፣ በእግዚአብሔር ፊት ለአማላጅነት ለተልዕኮ የሚቆም ቅዱስ ገብርኤል ሁላችንንም ይጠብቀን። የእግዚአብሔር ቸርነት የቅዱስ ገብርኤል አማላጅነት አይለየን። አሜን!!!

★★★ ምንጮች፦
የቤተ ክርስቲያን መረጃዎች፦ ዲ/ን ዳንኤል ክብረት፣ ማኀበረ ቅዱሳን 1999 ዓ.ም ገጽ 203
ፈለገ ጥበብ መጽሔት፦ በሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ፣ በየ3ወር የሚታተም ሐምሌና ነሐሴ 3ኛ ዓመት፣ ቁጥር 9፣ 1993 ዓ.ም ገጽ 33
@negeretewahido
472 viewsእልመስጦአግያ ዘሐዋርያት, edited  03:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 06:36:55 መንፈሳዊ የንግሥ ጉዞ ወደ ቁሉቢ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም
*** መነሻ፦ ሐምሌ 16 እና 17 ጠዋት 11:00
*** መመለሻ፦ ሐምሌ 20
★ ውስን ወንበሮች ብቻ ስለቀሩን ይህንን ቅዱስ ቦታ ለመሳለም የምትሹ ያልተመዘገባችሁ የኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ልጆች ሁሉ ደውሉልንና አብረን እንጓዝ!
★ ብዙዎች የበረከቱ ተሳታፊ ይሆኑ ዘንድ ጦማሩን Share, Like, Tag & Comment አድርጉት፤ የነዚህን ቅዱሳት መካናት የቃልኪዳን በረከት እንዲያገኙ ለሌሎች ምክንያት መሆን በራሱ ልዩ በረከት ያሰጣልና Share & Tag በማድረግ ለወዳጆችዎ ያካፍሉት።

"ገዳምህን የረገጠ" ብቻ ሳይሆን "ገዳምህን ለሌሎች ያሳዬ ...እምርልሃለሁ!" ተብሎ ቃል የተገባላቸው ቅዱሳን እንዳሉን ገድለ አቡነ ዘርዓ ብሩክን ያስታውሱ!!!

#ጥንታዊው_ቁሉቢ_ቅዱስ_ገብርኤል
→ ዘወትር ብዙ ድንቅ ገቢረ ተአምራት የሚፈጸምበት መካነ መንክራት፤
→ በቅዱስ ገብርኤል ምልጃ ተማምነው በመድኃኔዓለም ቸርነት አምነው የለመኑት በጎ መሻት ሁሉ ፈጥኖ የሚፈጽምበት የብዙዎች መካነ ጸሎት፤
→ ጥንታዊውን ተአምረኛ ታቦተ ቅዱስ ገብርኤል በ፱ኛው መ/ክ/ዘ ከዝዋይ ወደ ቦታው ይዘው የመጡትና በቦታው ላይ ለብዙ ጊዜ ተጋድሎ ያደረጉት የታላቁ ጸሎተኛ አባት የአባ ሌዊ ዘገዳመ ሲሐትና የሌሎችም ቅዱሳን የቃልኪዳን በረከት የሚገኝበት መካነ ቅዱሳን፤
→ በርካታ ስውራን ዘወትር የሚጸልዩበት መካነ ግኁሣን፤
→ ከጥንት ነገሥታትና ሹማምንት ጀምሮ በርካቶች በቦታው ላይ የተሳሉት ስዕታቸው እየሰመረላቸው "እሰይ ስዕለቴ ሰመረ!" እያሉ መባቸውን በደስታ የሚያገቡለት ስዕለት ሰሚ ነው።

★ ወደ ስዕለት ሰሚው ተአምረኛው ቁሉቢ ቅ/ገብርኤል ገዳም የምናደርገው የነገው የንግሥ ጉዟችን ሊሞላ ጥቂት ወንበሮች ብቻ ናቸው የቀሩን። ስለሆነም ከማኅበራችን ጋር ተጉዘው "በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ" እንዲሉ በአንድ ጉዞ ሌሎች ተጨማሪ ገዳማትንም ትሳለሙ ዘንድ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። #ኑ_አብረን_እንጓዝ!!!
@negeretewahido

#የቁሉቢ_ደብረ_ኃይል_ቅዱስ_ገብርኤል_ገዳም፦
★ "ቁሉቢ" ማለት በኦሮምኛ ቋንቋ ሽንኩርት ማለት ነው። በቦታው ላይ በብዛት ሽንኩርት፣ ድንችና ሌሎች አትክልቶች የሚመረትበትና የሚሸጥበት ስለ ነበር “ቁሉቢ” የሚለውን ስያሜ አግኝቷል። ስዕለት ሰሚው ደብረ ኃይል ቁሉቢ ቅ/ገብርኤል ገዳም ከአዲስ አበባ በስተምሥራቅ 461 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ጋራ ሙለታ የሚገኝ ሲሆን አመሠራረቱን በተመለከተ በብዙ ሊቃውንት የሚተረከው የሚከተለው ነው፡፡

★ መዝሙረኛው ዳዊት "ለእግዚአብሔር የሥራ ጊዜ አለው" (መዝ ፻፲፰፥ ፻፳፮) በማለት እንደተናገረው አንድ ሥራ ከመሰራቱ በፊት መቼ እንደሚሠራና እንዴት እንደሚሠራ በሰው ልብ ይታሰባል፤ ይታቀዳል። በሰው ዘንድ የታሰበውና የታቀደው እግዚአብሔር ካልፈቀደ ሳይፈጸም ይቀራል። ለዚህም ነው "የልብ ዝግጅት ከሰው ነው የምላስ መልስ ግን ከእግዚአብሔር ነው" ተብሎ የተነገረው፤ "ሰው ያስባል እግዚአብሔር ይፈጽማል" እንዲሉ። የሰውን አሳብ ለሰው ትተን ስለ እግዚአብሔር አሳብ ስንናገር እግዚአብሔር በልብ የመከረውን፣ በቃል ያስነገረውን እርሱ በወደደና በፈቀደ ጊዜ ያከናውናል። ይህንንም የሚከለክልና የሚቃወም ማንም ፍጥረት የለም።

★ ስለደብረ ኃይል ቁሉቢ ቅ/ገብርኤል ገዳም ገናና መሆን አስቀድሞ በመንፈሣዊ አባቶች ትንቢት ተነግሮ ነበር። ከዮዲት ጉዲት መውደቅ በኋላ የተነገረው ትንቢት ከአንድ ሺህ ዓመታት በኋላ በ19ኛው መቶ ክ/ዘመን መፈፀሙን ስናስተውል እግዚአብሔር ሥራው ግሩም ድንቅ ነው ከማለት በስተቀር ሌላ ምን ማለት እንችላለን?

#ትንቢት፦
★ በ9ኛው መቶ ክ/ዘመን (ከ842-892 ዓ.ም) ዮዲት ጉዲት በጠላትነት ተነሳስታ ለ40 ዓመታት ያክል አብያተ ክርስቲያናትን ስትደመስስ፣ ቅዱሳት መጻሕፍትን ስታቃጥል፣ ንዋየተ ቅድሳትን ስትዘርፍ በዘመኑ የነበረው ሕፃኑ የአክሱም ንጉሥ አንበሳ ውድም በአክሱም አካባቢ የነበሩትን ታቦታትና ንዋየተ ቅድሳት በመያዝ ወደ ደቡብ ኢትዮጲያ (አሁን በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ትገኛለች) ዝዋይ እንደመጣ የታሪክ ድርሳናት ይመሰክራሉ።

★ የዮዲት ጉዲት ኃይል ሲበረታ ሕፃኑ ንጉሥ አጼ አንበሳ ውድም ከአክሱም ሸሽቶ ወደ ዝዋይ ከዚያም ወደ ሸዋ መጥቶ ሳለ ለዮዲት ጉዲት "ንጉሡ ሸዋ ውስጥ እየኖረ ነው ሠራዊቱንም በመንዝ እመጓ አካባቢ በጎድጓዳ ቦታ ደብቆ አስፍሯል" የሚል ወሬ ደረሳት። እሷም ወሬው እውነት መስሏት አንበሳ ውድምን ከነሠራዊቱ ለመደምሰስ ወታደሮቿን ጠቅልላ ወደተባለው ቦታ ላከቻቸው። ነገር ግን የአንበሳ ውድም ሠራዊት በእመጓ ተራሮች ላይ ከብቦ ተደብቆ ስለነበር የሷ ወታደሮች ትክክለኛ ባልሆነ መልእክት ተታለው በሰደድኩላ ሚካኤል በኩል ባለው ጎድጓዳ ቦታ በሙሉ ሲገቡ በድንጋይ ናዳ መፈናፈኛ አሳጧቸው። ጉዲት አንበሳ ውድምን እና ሠራዊቱን ሊገድል ወደ ሰደድኩላ የላከችው ሰራዊቷ በጠቅላላ አለቀባት፤ አፄ አንበሳ ውድምም ድል አደረጋት።

★ ከ40 ዓመት የስደት ቆይታ በኋላ አንበሳ ውድም ወደ አክሱም ተመልሶ የንዋያተ ቅድሳት ቆጠራ ሲደረግ በቅዱስ ገብርኤል የተሰየመው የቃል ኪዳኑ ታቦት በዝዋይ መቅረቱ ታወቀ። የቀረበትም ምክንያት ንጉሡ ከአክሱም ያመጣቸውን ታቦታት እንዲመልሱ ትእዛዝ ሲሰጥ የቅዱስ ገብርኤል ታቦት በፈቃደ እግዚአብሔር ከተቀመጠበት መነሳት ባለመቻሉ ነው።

★ ንጉሡም ኤርትራ ውስጥ ካለችዋና ብዙ ድንቅ ታሪክ ካላት ከጥንታዊቷ ደብረ ሲና ማርያም በመጡት አባ ሌዊ በተባሉ የበቁ አባት የሚመራ ልዑክ በመመደብ ታቦቱን እንዲያመጡ ወደ ዝዋይ ደሴት መልሶ ላካቸው። አባ ሌዊ ዝዋይ ደርሰው የሰባት ቀናት ሱባኤ ካደረጉ በኋላ የቅዱስ ገብርኤልን ታቦት ይዘው ወደ አክሱም ለመመለስ ጉዞ ሲጀምሩ መልአኩ ገብርኤል ተገልጦ "እኔ ወደማሳይህ ቦታ ታቦቱን ይዘህ ትሄዳለህ" በማለት ትእዛዝ ሰጣቸው።

★ አባ ሌዊም በቅዱስ ገብርኤል እየተመሩ የዛሬው ምሥራቅ ሐረርጌ ቁሉቢ የተባለው ቦታ ደረሱ። አባ ሌዊ ታቦቱን ከዚህ ሥፍራ ማኖር እንዳለባቸው፣ ለአባ ሌዊ ጸሎተ በዓታቸው ይሆን ዘንድ የተፈቀደላቸው ቦታ ይህ እንደሆነና የሚያርፉትም በዚሁ ሥፍራ እንደሆነ፣ ታቦቱ በኋለኛው ዘመን በዚህ ቦታ ብዙ ድንቅ ሥራ (ገቢረ ተአምር) እንደሚያደረግ፣ ቤተ ክርስቲያንም በስሙ እንደሚሠራ መልአኩ ነግሯቸው ተሰወረ። ሰብአ ሰገልን ይመራ የነበረው ኮከብ (መልአክ) ቤተልሔም ዋሻ ሲደርሱ እንደተሰወረባቸው።

†★† #የአባ_ሌዊ_ዕረፍት፦
★ አባ ሌዊ ከ130 ዓመታት ዕድሜ በኋላ በንጉሥ ግርማ ሥዩም ዘመነ መንግሥት (ከ1070-1084ዓ.ም) ታኀሣሥ 14 ቀን በክብር ዐርፈዋል። የቅዱሳን ሞታቸው ሕይወታቸው፣ ዕረፍታቸውም በእግዚአብሔር ፊት የከበረ ነውና (መዝ ፻፲፭፥ ፮) እንዲል ። በረከታቸው ይደርብን።
@negeretewahido

†★† #የቁሉቢ_ገብርኤል_አመሠራረት †★†
★ ከ16ኛው እስከ 19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ድረስ በምሥራቁ የአገራችን ክፍል የነበረው አስተዳደር ሰላም የጠፋበት፣ ኢአማንያን የበዙበት፣ ክርስቲያኖች በቁጥር እጅግ ያነሱበት፣ ስብከተ ወንጌል የተዳከመበት እንደነበር የሚታወቅ እውነት ነው። በመሆኑም በዚህ አካባቢ ስብከተ ወንጌል ማስፋፋት፣ አብያተ ክርስቲያናትን መትከል የማይቻልበት ሁኔታ ነበር።
722 viewsእልመስጦአግያ ዘሐዋርያት, edited  03:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 00:15:42 በፍፁም የማይቀርበት ልዩ የንግሥ ጉዞ ወደ ታላቁ #ማኅበረ_ሥላሴ_ገዳምና_ተአምረኛው_በርሚል_ጊዮርጊስ
❖ በርካታ ጥንታዊ ገዳማትና አድባራትን የምንሳለምበት እና ታሪካዊ ቦታዎችን የምንጎበኝበት የ10 (11) ቀናት ልዩ የንግሥ ጉዞ ነው።
*** መነሻ፦ ሐምሌ 3 (4) ጠዋት 11:30
*** መመለሻ፦ ሐምሌ 13
★ ውስን ወንበሮች ብቻ ስለቀሩን ይህንን ቅዱስ ቦታ ለመሳለም የምትሹ ያልተመዘገባችሁ የኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ልጆች ሁሉ ደውሉልንና አብረን እንጓዝ!

★ ብዙዎች የበረከቱ ተሳታፊ ይሆኑ ዘንድ ጦማሩን Share, Like, Tag, Comment & Forward... አድርጉት፤ የነዚህን ቅዱሳት መካናት የቃልኪዳን በረከት እንዲያገኙ ለሌሎች ምክንያት መሆን በራሱ ልዩ በረከት ያሰጣልና Share & Tag በማድረግ ለወዳጆችዎ ያካፍሉት።

"ገዳምህን የረገጠ" ብቻ ሳይሆን "ገዳምህን ለሌሎች ያሳዬ ...እምርልሃለሁ!" ተብሎ ቃል የተገባላቸው ቅዱሳን እንዳሉን ገድለ አቡነ ዘርዓ ብሩክን ያስታውሱ!!!
@negeretewahido

✞❖✞ ይህ ልዩ የንግሥ ጉዞ መርሐ ግብር፦
በጎርጎራ የሚገኙ የጣና ገዳማትን ያካተተ ሲሆን በሐይቁ ላይ የጀልባ ጉዞን ጨምሮ የ10 (11) ቀናት ቆይታ ይኖረናል።
✞ በዚህ ጉዟችን በቅዱሱ ሐይቅ ላይ የሚገኙ በርካታ ቅዱሳት መካናትን እንሳለማለን።
✞ ምዕራብ ጎንደር ቋራ ደለጉ ተጉዘን በርሚል ጊዮርጊስ በመሄድ ለ30 ደቂቃ ነፍስ ከሥጋ ለይቶ ሲዖልንና ገነትን ካሳየ በኋላ የሚመልሰውን አስደናቂ ፈዋሽ ጠበል እንጠመቃለን።
→ የጉዞ ዋጋ ማረፊያ ቤትን ጨምሮ 4000 ብር

❖ እንደ እግዚአብሔር መልካም ፈቃድ በጉዟችን የምንሳለማቸው ገዳማትና የምንጎበኛቸው መካነ ቅርሶች፦
• ታላቁ ማኅበረ ሥላሴ ገዳም፣
• ደብረ ሊባኖስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ገዳም፣
• ባህርዳር ቅዱስ ጊዮርጊስ፣
• ጥንታዊው ዛራ ሚካኤል፣
• ታሪካዊቷ ጎንደር ቁስቋም፣
• በርካታ የጎንደር ጥንታዊ አድባራትን (ርእሰ አድባራት አደባባይ ኢየሱስ፣ ታሪካዊቷ ግምጃቤት ማርያም፣ ተአምረኛዋ በዓታ ለማርያም፣ ጥንታዊው ደብረ ብርሃን ቅ/ሥላሴ፣ መንበረ መንግሥት መድኃኔዓለም፣ አጣጣሚ ቅ/ሚካኤል፣ ቅ/ሩፋኤል ወአቡነ ሐራ ድንግል፣ አደባባይ አቡነ ተክለ ሃይማኖት፣ ፊት በር አደባባይ ቅ/ጊዮርጊስ፣ ታሪካዊው ጎንደር ቅ/ዮሐንስ መጥምቅ፣... ወዘተ እንሳለማለን፤ በጎንደር ፋሲለደስ ጊቢ የሚገኙትን ታሪካዊዎቹን አብያተ መንግሥታት እንጎበኛለን።)፣
• ታሪካዊው ጣራ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ወአቡነ ገላውዲዎስ የአባቶች ገዳም፣
• ተአምረኛዋ ጣራ ቅድስት ማርያም ገዳም፣
• ተአምረኛው ወይን ዋሻ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ገዳም (ጠበሉ ወይን የመሰለ)፣
• ገዳመ ወንያት አቡነ ሐራ ድንግል ወቅ/ኪዳነ ምሕረት፣
• ጥንታዊውና ተአምረኛው መካነ ፈውስ ጎንድ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ወአቡነ እጨጌ ዮሐንስ አንድነት ገዳም፣
• ታሪካዊቷና ተአምረኛዋ ሠይፍ አጥራ ቅ/ማርያም፣
• ጥንታዊው ወንጪጥ [ወይን እንጨት] ቅ/ሚካኤል ወመድኃኔዓለም፣
• ጥንታዊው ሽንብጥ ቅዱስ ሚካኤል ገዳም፣
• ተአምረኛው አዴት ጺማ ሥላሴ አቡነ ዘርዓ ብሩክ፣
• ታሪካዊቷ ፍልሰታ ደብር ቅ/ማርያም ወቅ/ክርስቶስ ሠምራ፣
• ታሪካዊው አዴት መድኃኔዓለም፣
• ተአምረኛው ጎንጅ ደብረ ጥበብ ቴዎድሮስ አቡነ ግርማ ሥሉስ አንድነት ገዳም [የተአምረኛው ጻድቅ የአቡነ ግርማ ሥሉስ የቃልኪዳን ቦታና ሊቁ ተዋናይ ቅኔን ያስተማረበት]፣
• ጥንታዊቷና ታሪካዊቷ ርእሰ አድባራት ወገዳማት መርጡለ ማርያም አንድነት ገዳም፣
• ተአምረኛው ድማ ጊዮርጊስ ገዳም፣
• ታሪካዊው ሲኖዳ ቅ/ዮሐንስ፣
• ደብረ ጽሞና አቡነ ሲኖዳ ገዳም፣

#በጎርጎራ_በኩል_ሰባት_ጥንታዊ_የጣና_ገዳማት፦
• ታሪካዊቷ ጎርጎራ ደብረ ሲና ማርያም (አባ ኤስድሮስ በ1312 ዓ.ም የመሠረቷት)፣
• ጥንታዊው ማን እንደ አባ (ማንዳባ) መድኃኔዓለም ገዳም (አቡነ ያሳይ በ14ኛው መ/ክ/ዘ የመሠረቱትና መካነ ዕረፍታቸው) እንድሁም አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ በጣና ሐይቅ ላይ ለ12 ዓመታት ተጋድሎ ያደረጉባት መካነ ጸሎታቸው እና የአባ አትማረኝ መካነ ጸሎት ዋሻ፣
• ብርጊዳ ቅድስት ማርያም የአባቶች ገዳም (አቡነ ቶማስ በ1314 ዓ.ም የመሠረቷትና ያረፉባት)
• አንጋራ አቡነ ተክለ ሃይማኖት የአባቶች ገዳም (በአቡነ እንድርያስ በ1326 ዓ.ም የተመሠረተች)
• ጫንቋ ቅ/ልደታ ለማርያም የእናቶች ገዳም (አቡነ ቶማስ በ13ኛው መ/ክ/ዘ የመሠረቷት)
• ደብረ ገሊላ ኢየሱስ የአባቶች ገዳም (ታላቁ ጻድቅ አቡነ ዘካርያስ በ13ኛው መ/ክ/ዘ የመሠረቷትና ያረፉባት)
• ጀበራ ቅድስት ማርያም የእናቶች ገዳም (በ1327 ዓ.ም በአጼ ዐምደ ጽዮን ዘመነ መንግሥት የተመሠረተች) በጀልባ ተጉዘን እንሳለማለን።

❖★ ማሳሰቢያ፦ ጊዜያችንን በአግባቡ ከተጠቀምን በሕይወታችሁ የማትረሱትና ግሩም በረከት የምታገኙበት አንድ ተአምረኛ ገዳም ሰርፕራይዝ ይኖራል።

፪ኛ #ቁሉቢ_ቅዱስ_ገብርኤል_ገዳም
* በዚህ ጉዟችን ጅጅጋ ከተማ ገብተን የዘመናችን መካነ ሰማዕታት የሆነችዋን ቅድስት ኪዳነ ምሕረትና ቅ/አማኑኤልን እንዲሁም ታሪካዊውን ደ/ኃ ቅዱስ ሚካኤል አብያተ ክርስቲያናትን፣ በሐረር ከተማ ውስጥ ደግሞ ታሪካዊውን ጀጎል መድኃኔዓለም እና ጥንታዊውን ቅ/ሥላሴን እንሳለማለን።
* መነሻ ሐምሌ 16 እና 17 ከሌሊቱ 11:00
* መመለሻ ሐምሌ 20
* የጉዞ ዋጋ ማረፊያ ቤትን ጨምሮ በ16 ለሚነሣው 1700 ብር በ17 ለሚነሣው 1500 ብር
☞ @negeretewahido

#መነሻ_ቦታዎች፦ አራዳ ቅ/ጊዮርጊስ፣ መስቀል አደባባይ ቅ/እስጢፋኖስ እና መገናኛ

#የምዝገባ_ቦታዎች፦
1) ቀጨኔ መድኃኔዓለም አካባቢ፦፦
ማትያስ የመኪና ዕቃ መሸጫ፣
ማርሶሊ ፎቶ ቤት፣

2) አራዳ ጊዮርጊስ አካባቢ
ገኒ የወንዶች ፀጉር ቤት
መሲ ሕትመትና ማስታወቂያ

3) ባላችሁበት አካባቢ ለመመዝገብ (ትኬት ለመቁረጥ)
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክና በአዋሽ ባንክ ሁሉም ቅርንጫፎች በካሽ ወይም በሞባይል ባንኪንግ በሚከተሉት የመምህር አንተነህ ውብሸት አካውንቶች አስገብታችሁ ደረሰኙን የጉዞው ቀን ይዞ መምጣት ወይንም Screenshot አድርጋችሁ በቴሌግራም ልትልኩልን ትችላላችሁ።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000099794899
አቢሲኒያ ባንክ 73439825
አዋሽ ባንክ 01320104564900

#ለመንፈሳዊ_ጉዞዎቹ_የሚያስፈልጉ_ነገሮች፦ የቀበሌ መታወቂያ (ፓስፖርት)፣ ለብርድ የሚሆን ወፍራም ጃኬት፣ ለእግር መንገድ የሚሆኑና ተቀያሪ ጫማዎች፣ ሌሊት የሚለበስ ስሊፒንግ ባግ / ወፍራም ጋቢ/ ወፍራም ወይባ/ ፎጣ/ ቀለል ያለ ብርድ ልብስ/፣ ክርስቲያናዊ አለባበስ፣ ጃንጥላ፣ የእጅ ባትሪ፣ ሰዓት አክባሪነት፣ ታጋሽነት፣ የወጡበትን መንፈሳዊ ዓለማ ለማሳካት በጋራ መትጋት...

✥ ለበለጠ መረጃ፦
0901070707
0911289877
#ማኅበረ_ቅዱስ_ፊልጶስ_ወአቡነ_ሳሙኤል_ዘዋልድባ
☞ @negeretewahido

✥✞✥ በዚህ መንፈሳዊ Page ላይ የሚተላለፉ መንፈሳዊ ጦማሮች ለእርስዎም ለሌሎችም እንዲደርሱ ፔጁን Like / Follow ሌሎችንም ወደ ፔጃችን ይጋብዙ።

በቴሌግራም ይቀላቀሉን
☞ @waldiba
☞ @waldiba
☞ @waldiba

የዩቲዩብ ቻናላችንን « መኮሬታ Mekoreta Tube »ን በሚከተለው ሊንክ ከፍተው Subscribe & Join ያድርጉ።
https://m.youtube.com/channel/UCUBStsekCniQtATyZDdFqQQ
8.4K viewsእልመስጦአግያ ዘሐዋርያት, edited  21:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-28 18:07:49 #ሕንፀታ_ቤታ_ለማርያም_ድንግል
በዚህች ዕለት ጌታችን 3 ድንጋዮችን (፫ቱ አዕባን) አለዝቦ በእናቱ በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስም የመጀመሪያዋን ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን በፊልጵስዩስ የሰራበትና በውስጧም ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስን ተራዳዒ (ንፍቅ) ካህን አድርጎ ቀዳሜ ሰማእት ቅዱስ እስጢፋኖስን ደግሞ ቀዳሽ ዲያቆን አድርጎ እመቤታንን መንበር ሆና የቀደሰበት ቅዱስ ቀን ነው።

ዳግመኛም በዚሁ ዕለት በጥንቷ የኢትዮጵያ ክፍል በአሁኗ ሃገረ ኤርትራ በምትገኘው ታሪካዊቷ መንበረ ጽዮን በጥንት ስሟ ገዳመ ሲሐት ትባል በነበረቺዋና ለግኁሣን የበረሃ ባሕታዊያን ጎቦ ሰንበት በሆነቺዋ በጥንታዊቷ ደብረ ሲና ማርያም ቦታዋን ጌታችን በኪደተ እግሩ ዳግም ሊባርካት ቢገለጥ በገዳሟ ካሉት 6666 ድንጋዮች (በጌታ ግርፋት ልክ) አንደኛዋ የዋሻ ቅርጽ ያላት ድንጋይ ከምድር 1ክንድ ከስንዝር ከፍ ብላ ስለተቀበለቺው ባርኳት በውስጧ ገብቶ በፊሊጵስዮስ የቀደሰውን ቅዳሴ በዚህም ደገመው። ድንጋይዋም እስከ ዕለተ ምጽዓት በአየር ላይ እንደተንሳፈፈች እንድትኖር በቃሉ አጽንቷት ለክብሩ መገለጫ ዛሬም እንደተንሳፈፈች አለች።

በዚች ገዳም በስደቱ ጊዜም ብዙ ድንቅ ስራ ሰርቶባታል። በአጼ አልዓሜዳ ዘመነ መንግሥት በ483ዓ.ም ተሰዓቱ ቅዱሳን ቦታዋን ከረገጡ በኋላ በተፈጸመላቸው ድንቅ ተአምር ደብረ ሲና አሏት። የአቡነ አረጋዊ የሕፃንነቱ የእግሩ አሻራ ጭምር ከቤተክርስቲያኑ በስተምዕራብ አቅጣጫ ባለ ትልቅ ድንጋይ ላይ ይገኛል።

በ892 ዓ.ም ታቦተ ቅዱስ ገብርኤልን ከዝዋይ ደብረ ጽዮን ይዘው ለመምጣት በአጼ አንበሳ ውድም ከተመረጡ በኋላ በፈቃደ እግዚአብሔር በቅዱስ ገብርኤል መሪነት ታቦቱን ይዘው ሄደው ተአምረኛው ቁልቢ ገብርኤል ገዳምን መስርተው በቦታው ላይ ለብዙ ዘመናት ተጋድሎ ፈጽመው ያረፉት አባ ሌዊ ከዚች ታላቅ ገዳም የተገኙ ደገኛ ጻድቅ መነኮስ ናቸው።

በሰሜን ጎንደር ሃገረ ስብከት ደንቢያ ወረዳ ጎርጎራ ከተማ ላይ የምትገኘው ጥንታዊቷ ደብረ ሲና ማርያም ደግሞ በ1312 ዓ.ም አባ ኤስድሮስ በተባለውና የታችቤት ትርጓሜን በመሠረተው በላዔ መጻሕፍት ሊቅ መናኝ ተመሠረተች። በርካታ ሊቃውንትን ያፈራው ይህ ታላቅ ሊቅ መናኚም የጣና ሐይቅ ስርጉድ (የልብ ቅርጽ ጫፍ) በተሰኘቺው ጎርጎራ ወደብ ላይ የምትገኘውን ይህችን ድንቅ ገዳም ተጋድሎ አድርጎባታል።

ይህ ሊቁ አባታችን መጀመሪያ ጉባዔ ተክሎ በርካታ ደቀመዛሙርትን በመጽሐፍት ትርጓሜ አስተምሮ ምስክርነት ሰጥቷቸው ለአገልግሎት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል ከተበተኑ በኋላ በጣና ቂርቆስና በሌሎች የጣና ገዳማት የሚገኙ 300 ጥንታዊያን የብራና መጻሕፍትን መርምሮ አጥንቶ ሲጨርስ እንደገና ደቀመዛሙርትን ከየቦታው አስጠርቶ፦ «ልጆቼ ልናጠናው የሚገባ የቀረን ትርጓሜ ስላለ ኑ!» ብሎ አስተምሮ መርቆ ላካቸው እነዚህ እንደገና ከመምህራቸው ተምረው የሄዱት ሊቃውንትም በየክፍለ ሃገሩ ተዘዋውረው የታች ቤት የመጻሕፍት አንድምታ ትርጓሜን እንዳስተማሩ ይገለጻል።
2.9K viewsዘዋልድባ 0901070707, edited  15:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-28 15:43:21
1.9K viewsእልመስጦአግያ ዘሐዋርያት, 12:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-27 12:12:56
2.7K viewsእልመስጦአግያ ዘሐዋርያት, 09:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-21 13:28:53
3.1K viewsእልመስጦአግያ ዘሐዋርያት, 10:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ