Get Mystery Box with random crypto!

ሰማይ እና ምድር በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡ 41፥11 ከዚያ | ወሒድ የንጽጽር ማኅደር

ሰማይ እና ምድር

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

41፥11 ከዚያም ወደ ሰማይ እርሷ ጭስ ኾና ሳለች አሰበ፡፡ ለእርሷም ለምድርም «ወዳችሁም ኾነ ወይም ጠልታችሁ ኑ» አላቸው፡፡ «ታዛዦች ኾነን መጣን» አሉ፡፡ ثُمَّ اسْتَوَىٰ إِلَى السَّمَاءِ وَهِيَ دُخَانٌ فَقَالَ لَهَا وَلِلْأَرْضِ ائْتِيَا طَوْعًا أَوْ كَرْهًا قَالَتَا أَتَيْنَا طَائِعِينَ

አምላካችን አሏህ ሰማይን ጭስ"gas" አርጎ ከፈጠራት በኃላ በጭስ ደረጃ እያለች ለእርሷ እና ለምድር፦ "ወዳችሁም ኾነ ወይም ጠልታችሁ ኑ" አላቸው፥ እነርሱም፦ "ታዛዦች ኾነን መጣን" አሉ፦
41፥11 ከዚያም ወደ ሰማይ እርሷ ጭስ ኾና ሳለች አሰበ፡፡ ለእርሷም ለምድርም «ወዳችሁም ኾነ ወይም ጠልታችሁ ኑ» አላቸው፡፡ «ታዛዦች ኾነን መጣን» አሉ፡፡ ثُمَّ اسْتَوَىٰ إِلَى السَّمَاءِ وَهِيَ دُخَانٌ فَقَالَ لَهَا وَلِلْأَرْضِ ائْتِيَا طَوْعًا أَوْ كَرْهًا قَالَتَا أَتَيْنَا طَائِعِينَ

አሏህ ሰማይ እና ምድርን «ኑ» ሲላቸው እነርሱም፦ «ታዛዦች ኾነን መጣን» ማለታቸው የሚያስቅ እና የሚያሳልቅ ከሆነ እንግዲያውስ ያህዌህ በባይብል ምድርን እና ሰማያትን ሲጠራቸው በአንድነት እንደሚቆሙ ይናገራል፦
ኢሳይያስ 48፥13 እጄም ምድርን መሥርታለች ቀኜም ሰማያትን ዘርግታለች፥ በጠራኋቸው ጊዜ በአንድነት ይቆማሉ። אַף־יָדִי֙ יָ֣סְדָה אֶ֔רֶץ וִֽימִינִ֖י טִפְּחָ֣ה שָׁמָ֑יִם קֹרֵ֥א אֲנִ֛י אֲלֵיהֶ֖ם יַעַמְד֥וּ יַחְדָּֽו׃

"በአንድነት" ለሚለው የገባው ቃል "የሕዳው" יַחְדָּֽו ሲሆን "አንድ ላይ"together" ማለት ነው፥ የሚጠራቸው መቼ ነው? በአንድ ላይ ሲቆሙ የሚቆሙት አየር ላይ ነው ወይስ ሥፍራ አላቸው? እንኳን ሰማይ እና ምድር ከዋክብትም ሲጠራቸው፦ "ፈጣሪያችን ወደ አንተ መጣን" ይላሉ፦
መጽሐፈ ባሮክ 3፥29(1980 ዕትም) "ይጠራቸዋል እርሱን የሚመስል ሌላ የለምና "ፈጣሪያችን ወደ አንተ መጣን" ይላሉ።
Book of Baruch 3፥35 when he calls them, they answer፦ "Here we are" they shine to delight their Creator"

"ወሒድ ይህ እኮ ፈሊጣዊ አገላለጽ"idiomatic expression" ነው" ካላችሁ እንግዲያውስ "ኢስጢላሕ" اِصْطِلَاح ማለት "ፈሊጣዊ አገላለጽ" ማለት ነውና አሏህ ሰማይ እና ምድርን «ኑ» ሲላቸው እነርሱም፦ «ታዛዦች ኾነን መጣን» ማለታቸው የሚያስቅ እና የሚያሳልቅ ነገር ሳይሆን ኢስጢላሕ ነው። ቢያንስ ቢያንስ የራሳችሁ መጽሐፍ አታነቡምን? አለዚያ እንደዚህ በሰፈራችሁት ቁና መሰፈራችሁ አይቀርም። አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም